>

በቃ ንግስና ሲጀምር እንዲህ ነው i!¡ (አሌክስ አብርሃም) 

በቃ ንግስና ሲጀምር እንዲህ ነው i!¡

(አሌክስ አብርሃም)
ትንቢት ይፈፀም ዘንድ ግድ ነው¡!¡ 
 
የቀድሞው ጠቅላይ ሚንስትር መለስ ዜናዊ ራሳቸው የህክምና ትምህርታቸውን  አቋርጠው ወደትግል ከገቡ በኋላ ነው   ጠ/ሚ የሆኑት  …ንግስና ሲጀማምር እንደዚህ ነው i ግፋ ! ራሱ ኢንተርቪው ላይ የነበረህ ግርማሞገስና የአነጋገር ጥበብህ ንጉስ እንደምትሆን የሚያረጋግጥ ነበር! በተለይ  ህልም ያልከው ነገር በጣም ወሳኝ እና ለብልሆች ብቻ የሚገለጥ ታላቅ  ነገር ነው …
አየህ ብዙ የአፍሪካ መሪዎች ህልም ያልማሉ …ለምሳሌ በቀን ሶስት ጊዜ ህዝቡ ጥግብ ብሎ ሲበላ ያልማሉ …በላ አልበላ ሌላ ነገር ነው!! አገራቸው በመጭው 15 ዓመት ኤሮፕና አሜሪካ ስትሆን ያልማሉ …ሆነች አልሆነች የራሷ ጉዳይ ነው ! አርሶ አደሩ ባለወፍጮ ቤት ባለ መኪና ሲሆን ያልማሉ …. ወጣቶች በመሃበር ተደራጅተው ሚሊየነር ሲሆኑ ያልማሉ ….ብዙ ነገር  ያልማሉ …ህልም በአንተ አልተጀመረም !!
ከሞላ ጎደል የንግስና መስፈርትህን አሟልተሃል i አሁን የቀረህ  አንድ ሁለት ነገር ነው ‹‹የበጎ አድራጎት ስራ እየሰራህ ፎቶ መነሳት›› እና ለተወሰነ ጊዜ ጫካ መግባት አልያም ከህዝቡ ዞር ማለት  …
 
ትንቢት ይፈፀም ዘንድ ግድ ነው¡!¡ 
    እንደ ጠቅ/ሚ  ዓብይ አህመድ ብልጥ መሪ የትም  የለም !!…ስምንተኛው ንጉስ አገጩ ትንሽ ለየት እንደሚል ቀድሞ የተፃፈውን  ትንቢት  አንብቧል !  …ማንነቱን ለማወቅ ያልፈነቀለው ድንጋይ የለም ! ታስታውሳላችሁ መቸም … ፍቅር አስመስሎ እንዲህ የቀረቡትን ሁሉ በሰላዮቹም በራሱም በኩል አገጫቸውን ሲፈትሽ ነበር ! (የፎቶ ማስረጃ አለ ዝም ብየ አላወራም ወገኖቸ) ዶ/ር ዓብይ  በጣም ነበር አገጭ የሚፈትሸው !
ስለትንቢቱ ልንገራችሁ (መቸም አትሰሙ)  ብዙ ሰው ሸህ ሁሴን ጅብሪልን ነው የሚያውቀው …እሳቸው ከመወለዳቸው ከ150 ዓመት በፊት እንግጭላ የምትባል  ገጠር ውስጥ የኖሩ አንድ ታላቅ ሰው የተናገሩትን መሬት ጠብ የማይል ትንቢት ብዙ የሰማችሁ አይመስለኝም  ! አሁን የምታናንቁት ልጅ እንደሚነግስ ቀድመው ተናግረዋል !ቻሉት እንግዲህ ! በነገራችን ላይ ሰውየው ከተናገሩት 27 ታላላቅ ትቢት   24 ቃል በቃል ተፈፅሟል (ሙሉውን ቀስ በቀስ እለጥፍላችኋለሁ) ለዛሬ ይሄንኛውን ብቻ ላካፍላችሁ ! ገፅ 24 ላይ እንዲህ ይላል …
መንግስቱ በሸሸ በሰላሳ ዓመቱ
ወረርሽኝ  ቲስፋፋ በመላ ዓለሚቱ
ከሸዋ በሚዘልቅ  ልጅ እግር ንጉስ
ይነግሳል አይነግስም አገር ሲታመስ
መልኩም እዩኝ አይል ድራቡም  መናኛ
ንግስናው ድንገት ነው ሰልፉም ስምንተኛ !
ብቻውን ይዘልቃል የለውም ጓደኛ
ልብስን ቀደው ጥለው  ጠጉርን ቢነጩ
በየደረሱበት  ጠልተውት ቢንጫጩ
መንገሱ ማይቀር ነው (( ዘለግ ያለ አገጩ ))
ራዲዮው ሁሉ ይፈራል መናገር
እንደው በየጓዳው ህዝቡ ሲደናገር
ጅል ያሉት ልጅ እግር ይረከባል አገር !
(((ሰባተኛው ንጉስ  ቀልድ እያስመሰለ
ያላፊ አግዳሚውን አገጭ ቢመረምር
አይቆምም ልጅግሩ ይነግሳል በታምር !)))
ያኔ አገረ ጦቢያ ትሆናለች ጥጋብ
ዳቦ በየቤቱ ይሆናል እንደካብ
ላምባ  በየቦታው እንደምንጭ ይፈልቃል
አለም ተያለበት ገርሞት ይደነቃል !
መላው የጦቢያ ልጅ አገጩ እስኪረዝም በደስታ ይስቃል!
ያኔ አገጫም መሆን  ቆንጆ ያማልላል
 በውን ባይሳካ በህልም ይታለማል
መላው ያበሻ ሰው በወፕራሲዮን አገጭ ያስረዝማል
‹‹አገጯ››  እሚል ዘፈን ጧት ማታ ይዜማል!
እሱ በነገሰ ገና በአንድ  ወሩ
መሃላ ታይፈጥም ታይረጋ ወንበሩ
 ወረርሽኝ በሽታ ይጠፋል ታገሩ !
ያኔ ወዮላቸው ክፉ የተናገሩ ….🙂
Filed in: Amharic