ታላቁ የኢትዮጵያ ኅዳሴ ግድብ ውኃ መያዝ መጀመሩን የሚያሳዩ የሳተላይት ምስሎች ወጥተዋል!!! (አሜሪካ ድምጽ ራድዮ)

ታላቁ የኢትዮጵያ ኅዳሴ ግድብ ውኃ መያዝ መጀመሩን የሚያሳዩ የሳተላይት ምስሎች ወጥተዋል!!!

አሜሪካ ድምጽ ራድዮ

ስለ ሳተላይት ምስሎቹ ይዘት የተጠየቁት የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ የቀረበላቸውን ጭብጥ አላስተባበሉም፤ እንዲያውም “እንደዚያ መውሰድ ይቻላል” ብለዋል። በምስሎቹ ላይ ትንታኔ መስጠት ግን አስፈላጊ ነው ባለው እንደማያስቡ አክለው ገልፀዋል።
በአፍሪካ ኅብረት አስተባባሪነትና ታዛቢነት “ቀሪ” በተባሉ የቴክኒክና የሕግ ጉዳዮች ላይ እየተካሄደ ያለው የኢትዮጵያ፣ የሱዳንና የግብፅ ድርድር በመልካም ሁኔታ እየተካሄደ እንደሆነም አምባሳደር ዲና ተናግረዋል።
በሃገሮቹ መካከል መግባባትን ለመፍጠርና “የአፍሪካ ሃብት ጉዳይ በአፍሪካዊያን እንዲያልቅ” የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ወደ አፍሪካ ኅብረት መምራቱን ኢትዮጵያ እንደምትደግፈው አምባሳደር ዲና ጠቁመው መተማመንን ለመፍጠርና በግርጌ ሃገሮች ላይ ጉዳት ሳይደርስ ውኃው ለጋራ ልማት ሊውል የሚችልበት መግባባት ለመድረስ ይቻላል የሚል ተስፋ እንዳላቸውም ተናግረዋል።
ሦስቱ ሃገሮች ስምምነት ላይ ለመድረስ አስበው የጀመሩት ንግግር በታለመለት ጊዜ ያልቃል ብለው እንደሚያስቡም የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴሩ ቃል አቀባይ ገልፀዋል። https://bit.ly/3fs0k6p

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.