>
5:14 pm - Friday April 20, 1894

የአቶ ሙስጠፌ ቀጭን ትእዛዝ...! (ሙክታሮቪች ኡስማኖቭ)

የአቶ ሙስጠፌ ቀጭን ትእዛዝ…!

ሙክታሮቪች ኡስማኖቭ

 

* …የሶማሌ ክልል ርእሰ መስተዳድር አቶ ሙስጠፌ በዛሬው ዕለት ካቢኔያቸውን አስቸኳይ ስብሰባ ጠርተው በክልሉ የተፈጠረውን ሰላምና መረጋጋት ለማደፍረስ እየሰሩ ስላሉ አክራሪ ውኃብዮች በተመለከተ ካስተላለፉት ከረር ያለ መልእክት!!!
.
“ኢትዮጵያ የክርስትያኖች ብቻ መኖርያ በነበረችበት፥ ክርስትና ከቤተመንግስት እስከ መንደሮች በጥብቅ ተፅእኖ ስር ሀገሪቷን በሚያስተዳድርበት፣ ስልጣኔ ባልነበረበት በድሮ ጊዜ  እስልምናን በሠላምና በክብር እንግድነት የተቀበሉት የኢትዮጵያ ክርስትያኖች ናቸው። ዛሬ የእኛ ትውልድ “ወርቅ ላበደረ ጠጠር” እንደሚባለው አባቶቻችንን በክብር የተቀበለውን ህዝብ በሰይፍ መግደል፣ የእምነት ቤቱን ማቃጠል በመንግስታችን በኩል በህግ የሚያስጠይቅ ሲሆን በአላህ ፊት ደግሞ እጅግ አፀያፊ ተግባር ነው።
.
“እኔ ከአላህ የተላከውን የቅዱስ ቁርአን አስተምህሮ በመስጂድ ውስጥ የተማርሁት እስላም ማለት ሰላም መሆኑን ነው ። አላህ ወንጀልን ይፀየፋል፣ በቀልና ጥፋት ደግሞ ወንጀል ነው… ።
.
ቀድሞ በእኛ ክልል ብዙ አብያተ ክርስትያናት በአክራሪ ኃይሎች ሲቃጠሉ በመላው ኢትዮጵያ የሚገኙ ክርስትያናት በመስጅዶችና በእስልምና ተከታዮች ላይ ምን አደረጉ? በአሁኑ ሰአት በአማራ ክልል የተቃጠሉ መስጂዶችን ያቃጠሉ ክርስትያኖች ሳይሆኑ # የአክራሪ_እስልምና ክንፎች ናቸው። አላማውም በሀገራችን የተፈጠረውን ሰላም ለማደፍረስ ና የኃይማኖት ፀብ በመፍጠር ሀገርን በማተራመስ የክፉዎችን ተልእኮ ለመፈፀም ሆን ተብሎ የታቀደ ነው ።
.
ከዚህ በፊት በአማራ ክልል እኛ የምናውቀው በክልሉ ቤተክርስትያን ሲገነባ እስላሞች በገንዘብና በጉልበት ሲያግዙ፣ መስጂዶች ሲሰሩ ደግሞ ክርስትያኖች በገንዘብና በጉልበት ሲያግዙ ነው ። ክረስትያኖች ይህን ተግባር የሚፈፅሙበት ምንም አይነት ምክንያት የለም ።
ስለሆነም ከዛሬ ጀምሮ በክልላችን ውስጥ በክርስትያኖችና በቤተ እምነታቸው ላይ የሚፈፀም ማንኛውም ጥቃት ቢኖር የመጀመርያ ተጠያቂ የሚሆነው ይህ የክልላችን ከፍተኛ አመራር ነው ። ምክንያቱም ክልላችንን የሚያስተዳድረው መንግስት ሁሉም ነገር መዳፉ ውስጥ እንደሆነ ሁላችንም እናውቃለን ።
.
ስለሆነም በክልላችን ውስጥ ማንኛውም አይነት ጸረ ሰላም እንቅስቃሴ ከተፈጠረ ተመጣጣኝ ና ቆራጥ እርምጃ በመውሰድ ወንጀለኞችን ማስተማር ተቀዳሚ ተግባራችን ይሆናል ።
Filed in: Amharic