>

ወሬ ይሰጡሃል- አውርተህ ሳትጨርስ ከአፍህ ላይ ይነጥቁሀል...!!!! (ወሰን ሰገድ ገ/ኪዳን)

ወሬ ይሰጡሃል-አውርተህ ሳትጨርስ ከአፍህ ላይ ይነጥቁሀል…!!!!

ሰን ሰገድ ገ/ኪዳን
* ..”እነዚህ የታገዱት ሦስት ግለሰቦች በነበራቸዉ ኃላፊነት ልክ ለመስራት ዝግጁ ሲሆኑ በማንኛዉም ሰዓት መመለስ እንደሚችሉ ፓርቲዉ ወስኗል” ሲባል፤ ምን ማለት እንደሆነ ገብቶሀል? ወሬ ሰጡህ መልሰው ነጠቁህ ማለት ይህው አይደል…ይህችንም በቅጡ ሳታጣጥማት ሌላ ወሬ ባፍህ… እናም እነርሱ ስራቸውን ይሰራሉ… ተግባባን?!?
በመጀመሪያ በሆነ መንገድ ወሬ ይሰጡሃል፤ አንተ ያንን ወሬ ተቀብለህ ኡኡ ስትል ውለህ ኡኡ ስትል ታድራለህ። “ኡኡ” ብለህ ሳታበቃ መልሰው “ወሬአቸውን” ይነጥቁህና ሌላ ወሬ ያቀብሉሃል። አንተ ወሬ ቀለቡ የትናንቱን ወሬ ረስተህ፣ ይኼንንም ታራግበዋለህ።
.
ትናንት ሽመልስ ያወራው ወሬ ነው ብለው አቀበሉህ። አንተ ቀን ከሌት፣ ካለ እረፍት ወሬውን ስታራግበው ውለህ አደርክ። የሚፈለገው ይኼ ነው፤ በትናንትናው ጫጫታህ እየሳቁ ዛሬ ደግሞ ይኼንን ወሬ አቀበሉህ፦ እነ ለማ መገርሳ ተባረሩ አሉህ። ይኸው ወሬ አባረህ ይዘህ፤ በነገር እየነበረርህ ነው።
የሆነስ ሆነና፣ መባረር እና ማባረሩንስ እንደፍጥርጥራቸው። ግን ግን  …”እነዚህ የታገዱት ሦስት ግለሰቦች በነበራቸዉ ኃላፊነት ልክ ለመስራት ዝግጁ ሲሆኑ በማንኛዉም ሰዓት መመለስ እንደሚችሉ ፓርቲዉ ወስኗል” ሲባል፤ ምን ማለት ነው ብለህ ጠይቀሃል?!
ይህንን ያሉት መግለጫውን የሰጡት አቶ ፈቃዱ ናቸው። እና “ተባረሩ” የተባሉት ሰዎች ነገ ጠዋት “በነበረን ኅላፊንት ልክ ለመስራት ዝግጁ ነን” ቢሉ ይመለሳሉ ወይስ… ….?!
.
.
ለማንኛውም ወሬ ይሰጡሃል
መልሰው ወሬ ይነሱሃል
Filed in: Amharic