>

ሻሸመኔ ቅርቤ ነው፣ የሻሸመኔው ሟች ወንድሜ እኔኑ ራሴኑ ነው! (አሰፋ ሀይሉ)

ሻሸመኔ ቅርቤ ነው፣ የሻሸመኔው ሟች ወንድሜ እኔኑ ራሴኑ ነው!

አሰፋ ሀይሉ

 

“ሞታችንን የሌላ ሰው ሞት አናድርገው!
መቁሰላችንን የሌላ ሰው ቁስል አናድርገው!
የሞትንም እኛ;  የቆሰልንም እኛ ነን…!!!”
አስበዋለሁ፡፡ ደግሜ ደጋግሜ አስበዋለሁ፡፡ በተሰበረ ልብ፡፡ የዘር ማጥፋቱን፡፡ የዘር ማጥራቱን፡፡ የሰው ልጅ እርዱን፡፡ ጭፍጨፋውን፡፡ ቅጥቀጣውን፡፡ በሻሸመኔ፡፡ በባሌ፡፡ በሐረር፡፡ በወለጋ፡፡ በአርሲ፡፡ በዝዋይ፡፡ በናዝሬት፡፡ በጅማ፡፡ በሀገር በምድሩ ሁሉ የሚቀጠፈውን የሰውን ልጅ ነፍስ፡፡ የወገኔን ነፍስ፡፡ አስበውና ደጋግሜ – የቱንም ያህል ጭፍጨፋው ለእኔ ሩቅ ቢመስልም ግን – የቱን ያህል ደግሞ ለራሴ ቅርብ እንደሆነ አስበዋለሁ፡፡ ዋይታው ይሰማኛል፡፡ ሰቆቃው ያንገበግበኛል፡፡ እና በርቀት ሆኜ አጠገቡ እንዳለሁ ስጋት ይውጠኛል፡፡ የማላውቀው እልህ ይተናነቀኛል፡፡
ምናልባትኮ በምወዳት ሻሸመኔ ላይ እግር ጥሎኝ ተገኝቼ ቢሆን ኖሮ እኮ የምገደለው ሰው እኔ ነበርኩ – እያልኩ ደግሜ ደጋግሜ አስባለሁ፡፡ በምወዳት ሐረር ላይ ብገኝ ኖሮ ምናልባትም የቄሮ ሜንጫ ከሚያጠፋቸው ሰዎች አንዱ እኔው ራሴው ነበርኩ፡፡ እንደለመድኩት ወደ ሞጆ፣ መቂ፣ ዝዋይ እግር ጥሎኝ ብገኝ ኖሮ… ያለጥርጥር በዝዋይ የታረደው ወገኔ እኔው ራሴው ነበርኩ የምሆነው፡፡ የሞተው ወገኔ እኔው ነኝ፡፡ የቄሮው ጠላት እኔው ነኝ፡፡
እኔው ነኝ በዘሬ በዘር ማንዘሬ ኦርቶዶክስ ክርስትያኑ፡፡ እኔው ነኝ ታቦቴን በራሴ ላይ አንግሼ የምዞረው፡፡ እኔ ነኝ ዒላማው፡፡ አማራው እኔ፡፡ ኦርቶዶክሱ እኔ፡፡ የኢትዮጵያን ንፁህ ባንዲራ እንደ ነፍሴ የምወደው እኔ፡፡ አማርኛ ተናጋሪው እኔ፡፡ መጽሐፍ ቅዱሴን በሄድኩበት ይዤ የምገኝ እኔ፡፡ በፊደሌ የምኮራ እኔ፡፡ ባባቶቼ ጥበብ የምመካው እኔ፡፡ እኔኑ ነው ቄሮ ገጀራውን ስሎ ‹‹ነፍጠኛ›› እያለ በየመንገዱ የሚፈልገው፡፡ እኔኑ ነው አግኝቶ በቆንጨራው የጨቀጨቀኝ፡፡ እኔን የመሰለውን ነው የሚጠላው፡፡ የሚደማው፣ የሚገደለው፣ ቤቱ ንብረቱ የሚቃጠለው ሌላ ከእኔ የተለየ ሰው አይደለም፡፡
የሞተው ወንድሜ ከእኔ የተለየ የሠራው ጥፋት የለም፡፡ ጥፋቱ እንደ እኔ አማራ ሆኖ መገኘቱ ብቻ ነው፡፡ ኦርቶዶክስ ሆኖ ቤተክርስቲያን በመሳለሙ ብቻ ነው፡፡ ባለማተብ ሆኖ መገኘቱ ብቻ ነው ለጥቃት ያጋለጠው፡፡ በአባቶቹ አያት ቅድመ አያቶቹ የተሰጠውን መጠሪያ ስሙን ይዞ መገኘቱ ብቻ ነው ያስቀጠቀጠው፡፡ ሀገሩን፣ ባንዲራውን ወዳጅ፣ በሄደበት ለማጅ፣ ሀገር አቅኚ፣ በላቡ አዳሪ፣ ለሀገሩ ለወገኑ ሟች፣ ክብሩን ጠባቂ፣ ለእምነቱ ሟች ሆኖ በመገኘቱ ብቻ ነው በቄሮ እንደ ከብት እየታረደ ያለው፡፡
ዛሬ በቄሮ ቢላዋ የምትተለተለው አርሲ ላይ የምትገኝ እህቴ ጥፋቷ ኢትዮጵያዊ ኩራቷን ይዛ መገኘቷ ብቻ ነው፡፡ የአጋጣሚ ጉዳይ ሆኖ ነው እንጂ በህይወት እየኖርኩ ያለሁት፣ ምናልባትም አርሲ ላይ ወይ ሻሸመኔ ላይ ወይ ናዝሬት ላይ ተገኝቼ ብሆን ኖሮ.. እኔም ተቀጥቅጣ እንደተገደለችው እህቴ፣ እኔም ተቀጥቅጦ እንደሞተው ወንድሜ በኦሮሞ ዱላ ተቀጥቅጬ እገደል ነበር፡፡ እና ለዚህ ነው ሻሸመኔ ቅርቤ ነው የምለው፡፡ ለዚህ ነው የሻሸመኔው ሟች ወንድሜ እኔኑ ራሴኑ ነው ብዬ የምናገረው፡፡
እኔ የሆንኩትን ስለሆነ ነው ወገኔም የተገደለው፡፡ በእርሱ ላይ የተነጣጠረው አፈሙዝ በእኔም ላይ የተነጣጠረ አፈሙዝ ነው፡፡ እርሱ ማለት እኔ ነኝ፡፡ በቁም ያለሁት እኔ፣ በሞት የተለየኝን ወንድሜን ነኝ፡፡ ሞታችንን የሌላ ሰው ሞት አናድርገው፡፡ መቁሰላችንን የሌላ ሰው ቁስል አናድርገው፡፡ የሞትንም እኛ፡፡ የቆሰልንም እኛ ነን፡፡ ሌላ ሰው አይደለም፡፡ እየሞትን ያለነው እኛው ራሳችን ነን፡፡ እየተገደለ ያለው እኛኑ ሆኖ የተገኘ ሰው ነው፡፡
እኛነታችንን መቀየር ካልቻልን እኛ ለእኛ አዳኝ ሆነን ከመቆም በቀር አማራጭ የለንም፡፡ እኔ ለወገኔ፣ ወገኔ ለእኔ የምንነሳበት ቀን ሩቅ አይደለም፡፡ አይቀርም ቀን አለው፡፡ አንድ ቀን አለ፡፡ አንድ መስቀላችንን ከፊታችን አድርገን፣ የአድዋ አባቶቻችንን መስዋዕትነት የምንደግምበት አንድ ቀን አለ፡፡ ያ ቀን ሲጠራኝ አላለሳልስም፡፡ ማቄን ጨርቄን አልልም፡፡ የአባቴን ጀግንነት ለብሼ ለወንድሜ እነሳለሁ፡፡ የሞተች እህቴን ልፋረድ ፈጣሪን አምኜ እነሳለሁ፡፡ አንድ ቀን ፍትህን ፍለጋ፣ የቀን አራጆችን ልፋረድ ከወገኔ ጋር ‹‹ሆ!›› ብዬ እነሳለሁ፡፡
እስከዚያው ከሞተው ጋር እየሞትኩ ያለሁት እኔ በቁሜ ያለሁት ነኝና በራሴው ሞት ስለ ሞቴ ከልቤ አነባለሁ፡፡ በወገኔ ደም እሰቃያለሁ፡፡ የተወጋው ወገኔ ህመም የእኔንም አካል ያንገበግበኛል፡፡ የተቃጠለው ወገኔ እኔንም ውስጤን ያቃጥለኛል፡፡ የሚቃጠለው አመድ ሆኖ አይቀርም፡፡ አመድ የሆነው የወገኔ አጥንት – በእኔ፣ በእኛ፣ በወገኖቹ ልብ ውስጥ ታላቅ የጀግንነት ምሰሶን ያቆማል፡፡
ቀን አለው ለሁሉም፡፡ አንዲት የቁርጥ ቀን አለች፡፡ ለዚያች ማቄን ጨርቄን ለማልልባት ቀን በህይወት ያብቃኝ፡፡ አንድ ሜንጫ፣ አንድ ገጀራ፣ አንድ ቆመጥ፣ አንድ ዲሞትፈር ሳልማርክ እንዳልመለስ ፈጣሪዬን እለምነዋለሁ፡፡ የቴዎድሮስን መንፈስ በላዬ እንዲዘራብኝ እለምነዋለሁ አምላኬን፡፡ የራስ መኮንንን፣ የአሉላን፣ የበላይን፣ የራስ ደስታን፣ የባልቻ ሳፎን፣ የሀብተጊዮጊስን፣ የሰማዕቱን የቅዱስ ጊዮርጊስን መንፈስ በሁለመናዬ እንድትዘራብኝ አማላጂቱን ንፅህት ድንግል እመቤቴን እለምናታለሁ፡፡
ቀን አለው አንድ ቀን፡፡ አይቀርም፡፡ በአንዱ ቀን ፍትህን ልንፋረድ የምንነሳበት፡፡ እስከዚያው እየታረድን፣ እየሞትን፣ እየደማን፣ በህመም እያቃሰትን፣ በድህነት አሳራችንን እየበላን እንኖራለን ከሰው ከወገን እንዳልተፈጠርን፡፡ ሀገር እንደሌለን፡፡ መሪ እንደሌለን፡፡ ሰው እንዳልሆንን፡፡ ከሰው እንዳልተፈጠርን፡፡ በገዛ ሀገራችን ባይተዋር ሆነን፡፡ እንኖራለን ቀኑ እስኪደርስ፡፡ ግድየለም ወገኔ ቀን አለው፡፡ ቀን አለው ሞታችን፡፡ ቀን አለው ሀዘናችን፡፡ ቀን አለው ማንነታችን አራጆቻችንን እንደ ፀሐይ ጮራ የሚያቀልጥበት፡፡
እስከዚያው እስከማይቀረው ቀናችን አጥብቀን ልብን እንግዛ፡፡ ያባቶቻችንን የጀግና ትንፋሽ እንሳብ፡፡ ቀልባችንን ዕቃችንን ሁለመናችንን እንሰብስብ፡፡ ማቃችንን አውልቀን የአባቶቻችንን ልብስ ለብሰን የምንነሳበት ቀን ሩቅ እንዳይደለ እንመን፡፡ ኢትዮጵያ እጆቿን ወደ እግዚአብሔር ዘርግታለች፡፡ አምናለሁ ለሺህ ዓመታት ኤሎሄ ብለን የተደፋንለት፣ የቀደስንለት፣ የምንመካበት ፈጣሪ አምላካችን – በዚያች በመጨረሻዋ ቀን በአራጆች ፊት እንደማይተወን፡፡
አይቀርም፡፡ አንድ ቀን ከሞታችን እንነሳለን፡፡ አንድ ቀን ከቁስላችን እናገግማለን፡፡ አንድ ቀን ስቃያችን ጀግንነት ወደሞላበት ወኔ ይቀየራል፡፡ ለቅሷችን ወደ ሆታ ይቀየራል፡፡ አይቀርም አንድ ቀን፡፡ ይኼው ነው በህይወት እስካለሁ የማምነው፡፡ ይኼው ነው በቁሜ ሳለሁ ደሙ እንደ ውሃ ከሚፈሰው ወገኔ ጋር በእንባ ታጅቤ አብሬ በመንፈስ እየደማሁ የምፅፈው የማይናወጽ ኢትዮጵያዊ ቃሌ፡፡ ኢትዮጵያዊነት አይበገሬነት ነው፡፡ እምቢኝ ለሀገሬ፣ እምቢኝ ለወገኔ፣ እምቢኝ ለነጻነቴ፣ እምቢኝ ብለን የምንነሳባት ቀን ሩቅ አይደለችም፡፡ ሀገሬ የደሃ ጎጆዬ – ብረሳሽ ቀኜ ትርሳኝ፡፡ እናት ኢትዮጵያዬ – ለዘለዓለም ኑሪ፡፡
“ለውጥ ለውጥ አትበለኝ
ተው አንተ ነውጠኛ፣
በሰው ደም መቀለድ
አይገባንም እኛ!”
“የፍቅር ልብ አስተሳስሮን
አንድ ሆነን ስንቆም እኛ፣
ይብላኝለት ለደም አፍሳሽ
ይብላኝለት ለዘረኛ!”
ዘለዓለማዊ ክብርና ምስጋና በሠማይ ላለ አምላካችን ለአብ፣ ለወልድ፣ ለመንፈስ ቅዱስ ይሁን፡፡ ዘለዓለማዊ ውዳሴ ከሴቶች ሁሉ ለተለየች ለጭንቅ አማላጂቱ ለእመቤታችን ለንፅህት ቅድስት ድንግል ማርያም ይሁን፡፡
እናት ኢትዮጵያ – በአይበገሬ ልጆቿ ፀንታ – ለዘለዓለም በፍቅር ትኑር!
ፈጣሪ ኢትዮጵያን – እና ኢትዮጵያን ብለው የቆሙትን ሁሉ – አብዝቶ ይባርክ!
Filed in: Amharic