>

"እኔም አፋር ነኝ".... በሚል ባልደራስ እንደ ፓርቲ የመጀመሪያው በመሆን ለአፋር ወገኖቹ እረዳታ ለገሰ...!!!

“እኔም አፋር ነኝ”…. በሚል ባልደራስ እንደ ፓርቲ የመጀመሪያው በመሆን ለአፋር ወገኖቹ እረዳታ ለገሰ…!!!

ወግደረስ ጤናው
ባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ  ፓርቲ እንደሚታወቀው ከፓለቲካ ስራው ባልተናነስ በሰብአዊና የበጎ አድራጎት ስራው እንደ ፓርቲ ወደር የለውም።
ባልደራስ….  ለጭቁኖች ለተገፉትና ለታፈኑት  ድምፅ  ነው!
  ~ዜጎች በማንነታቸው ምክንያት ከቀያቸው ሲፈናቀሉና ቤታቸው በመንግስት ያለአግባብ ሲፈርስ ፊት ለፊት ቆሞ ይሞግታል።
~ ታሪካዊ ቅርሶች እንዳይፈርሱና ትውፊቶቻችን እንዲጠበቁ አብክሮ ይሰራል።
~ ለተቸገሩ ወገኖቻችን ከውጭም ከአገር ውስጥም የገንዘብም ሆነ የቁሳቁስ ዕርዳታዎችን በማሰባሰብ ይለግሳል።
ባልደራስ ከዚህ ቀደም ይሰራው በነበረው ስራ ሳይገታ ዛሬም…. በቅርቡ በአፋር ክልል በወገኖቻቸን ላይ በደረሰው የተፈጥሮ አደጋ ለተጎዱ ወገኖቻችን አለኋችሁ በማለት እንደ ፓርቲ የመጀመሪያው በመሆን የምግብ ዕርዳታ አድርጓል።
ፓርቲው ካዛንቺስ በሚገኘው ” ቶፊቅ መስጅድ” ድረስ በመገኘት እረዳታውን አድርሷል።
የዕርዳታው አስተባባሪዎች ባልደራስ እንደ ፖለቲካ ፓርቲ ቀዳሚ በመሆን ላደረገው ሰብአዊ ድጋፍ ያላቸውን ከፍተኛ ምስጋና ገልፀው በቀጣይም ከጎናቸው እንዲቆም ጥሪ አቅርበዋል።
!
ድል ለዴሞክራሲ!
ባልደራስ 2012!
Filed in: Amharic