>

ያበደው ብእረኛው ሳይሆን ባለ እርሳሶቹ ናቸው  ....!!!! (ዳዊት ስሜ)

ያበደው ብእረኛው ሳይሆን ባለ እርሳሶቹ ናቸው  ….!!!!

ዳዊት ስሜ

* የእስክንድር ነጋ እውነት እንደ ማለዳ ጸሀይ ክፍት እያለ እያንጸባረቀ ነው ! 
እስክንድር ነጋ ወደ እስር ቤት ከገባ ግዜ ጀምሮ የተለያዩ ወዳጆቹ ሆነ የኢትዮጵያ ህዝብ እስክንድር በታገለው ደረጃ ለእሱ ድምፅ ማሰማት እንደ ሀፍረት ተቆጥሮ እንደ ፅንፈኛ እንደ ነብሰገዳይ ተቆጥሮ በሚያሳዝን ሁኔታ ይታሰር ወደሚል ድምዳሜ በመድረስ እስክንድርን ያለሀጢያቱ እስር ቤት እንዲቆይ በእበላ ባዮች፣ በእወደድ ባዮች ተፈርዶበት ነበር !
እስክንድር ነጋ እውነት ስላለ ብቻ ትናንት እሱ ሲታሰር ሲያጨበጭቡ የነበሩት እነ ኢዜማ ሳይቀር ከረፈደም ቢሆን ድርጅቱ ባልደራስ ወጥቶ ወርዶ፤ ጊዜ ገንዘብ ጉልበት ከዛም በላይ እስከ እስር ያበቃቸውን ውድ ዋጋ የከፈሉበትን  የህዝብ አጀንዳ በመንጠቅም ቢሆን ለአደባባይ አብቅተዋል ::
በጣም የሚያሳዝነው እስክንድርን ለብዙ አመታት የሚያውቁት እነ ታማኝ በየነ እነ ሲሳይ አጌና እነ አንዷለም አራጌ ስለ እስክንድር ድምፃቸውን ሳያሰሙ በአላማ ፍፁም የማይገናኜው ጃዋር መሀመድ “…ብቻውን አጀንዳ ቀርፆ እውነትን ይዞ
የመንግስትን አስተዳደር ያንቀጠቀጠ ፓለቲከኛ ነው ፣ መንግስት በእስክንድር ላይ የሚያደርገውን አፈና ሊያቆም ይገባል!” በማለት ስለ እስክንድርና ስለ እውነተኛነቱ እንዲህ የሚል ምስክርነቱን  ሰጥቷል ::
እስክንድር ጋር እውነት ስላለ አይደለም በአላማ አንድ የሆነ ሰው ቀርቶ በሀሳብ ተቃራኒ የሆነ ሰው እንኳ የሚመሰክርለት እንደ ብዙዎቹ ፓለቲከኞች ነጋዴ ሳይሆን እውነተኛ የህዝብ ተቆርቋሪ ለህዝብ መብት እና ዲሞክራሲ የሚታገል የህዝ ልጅ ነው ::
እስክንድርን ወደ አንድ ፅንፍ ለመክተት ብዙ ተሞክራል ! እስክንድር ግን ኢትዮጵያዊ ነው እስክንድር ትናንት የመጣ ታጋይ አይደለም ብዙ ብዙ ዋጋ የከፈለ በኢትዮጵያዊነቱ በፍፁም የማይደራደር አንባገነንነትን የማይቀበል እውነትን አጥብቆ የያዘ ሁሌም እውነት ነፃ የምታወጣው የዲሞክራሲ ታጋይ ነው – እስክንድር ነጋ !
በሚገርም ሁኔታ እየተከታተለ የታከለ ኡማን አስተዳደር ሴራ ሲያጋልጥ ሲቃወም “እስክንድር ወደ እብደት እያመራ ነው” የሚል ትችቶች በብዛት ይደመጡ ነበር ! ነገር ግን እውነትና ንጋት እያደር ይጠራል ነውና እብዱ ማን እንደሆን በተግባር
 አስመስክሯል !
እስክንድር እንደ ጃዋር መሀመድ ዲያስፖራው  ወጥቶ በተለያዩ አለማት ኤምባሲ ወሮ ድምፅ ባያሰማለትም የአዲስ አበባ ህዝብ “ፍትህ ለእስክንድር ” ብሎ ድምፅ ባያሰማም፤ መንጋ ኖሮት በሜጫ በገጀራ ሆ ባይባልልትም በያዘው እውነት አንድ ብቻውን መንግስትን አሸንፎ ከእሱ ጋ እውነት እንዳለ ሲቃውሙት ነበሩትን ጭምር ማሳመን የቻለ ብርቱ የዲሞክራሲ ታጋይ ነው !
እስክንድር ነጋ ከማንኛቸውም የፓለቲካ ፓርቲዎች ይልቅ ብልፅግና ውስጥ ያለ የሴራ ድብቅ አጀንዳዎችን ቀድሞ የተናገራቸው ነገሮች ሁሉ አንድ ባንድ ነጥብ በነጥብ ሲተገበሩ አይተናል ! ታዲያ እስክንድርን ነጋን ማክበር ማድመጥ ስለ
እስክንድር ፍትህን መጠየቅ አይገባም ወይ ?
ፍትህ በገጀራ ሳይሆን በብእር ለታገለው እስክንድር ነጋ
Filed in: Amharic