>

"እርቅ ሌላ ፍትህ ሌላ" (ብርሀኑ ተክለያሬድ)

“እርቅ ሌላ ፍትህ ሌላ”

ብርሀኑ ተክለያሬድ

 

ከሰሞኑ የኢትዮጵያዊነት ሚዛን ተዛባ ባይ ግለሰቦች “የቀኙ ከግራው አጋድሏል” በሚል የአቅጣጫ መዛኝነት ካባ ‘ሁሉም የፖለቲካ እስረኞች ይፈቱ’ የምትል በእርቅ ስም ወንጀለኞችን ከፍትህ የማስመለጥ እቅድ ያለው የአባይ(ላልቶ) ሚዛን ተንታኝነትን በግርምት እየተመለከትን ነው።
ጉዳዩን የአክቲቪስቶች የሞቅታ ሀሳብ አድርጎ መመልከት በቀጣይ ከምንገባበት ቀውስ የሚያድነን አይደለም።ይህን የሚሉ አካላት ትናንት ¨ጃዋር ይታሰር ¨ለማለት የቀደማቸው ያልነበሩና ሊሆን ያለውን ቀድመው “የሚተነብዩ” ውስጥ አወቆች መሆናቸውን ስንመለከትና ከነገሩ ጀርባም የህዝቡን ትርታ ለማዳመጥ የወደዱ ቱባ መሪዎች መኖራቸውን ስንጨብጥ ነገሩ አንድም የስሜት ሳይሆን የስሌት መሆኑን አንድም አይን ያወጣ የቤትና የመሬት ሌብነቱን አጀንዳ ለማስቀየር የሚደረግ የቀቢፀ ተስፋ ሙከራ መሆኑን እንረዳ ዘንድ ግድ ይለናል።
እርቅ መልካም ነው የበደለ ይቅርታ ጠይቆና ክሶ የተበደለም ተክሶ በጋራ መኖርን የመሰለ ነገር የለም። ይሁንና በእርቅ ስምና በተንጋደደ የሚዛን ማስጠበቅ ስሌት ስም ወንጀለኞችን የማስፈታት ዳር-ዳርታ በሰማእታትና በቤተሰቦቻቸው ቁስል እንጨት መስደድ ነው። አይን ያወጣ “የአስከሬን ላይ ቁማርተኝነት” ነው።
ከሁሉም በፊት ህግ ይከበር
Filed in: Amharic