>

አንቺ አዲስ አበባ! ማየትሽን ተውሽ ወይ? (ኤርሚያስ ለገሰ ዋቅጅራ)

አንቺ አዲስ አበባ! 

ማየትሽን ተውሽ ወይ?

ኤርሚያስ ለገሰ ዋቅጅራ

፩:- በ1992 ዓ.ም. ከኦህዴድ አሊ አብዶ መጥቶ በምክር ቤት የመክፈቻ ዲስኩር ላይ ” ከመሬት ጋር የተያያዙ እንቅስቃሴዎች ለጊዜው ታግደዋል። የካቢኔው ቁልፍ ስራ ህገ-ወጥ የመሬት ወረራን መግታት ነው” አለ። በሶስት አመት ውስጥ ሁለት መመሪያ በማውጣት ህገ-ወጥ የመሬት ወረራውን ህጋዊ አደረገ።
፪:- በ1995  ከህውሓት አርከበ እቁባይ መጥቶ ” የመሬት እንቅስቃሴዎችን ለጊዜው አግጃለሁ፣ የመጀመሪያ ስራዬ ከመሬት ጋር የተያያዘ ህገ-ወጥ ወረራና ዝርፊያን ማስቆም ነው” አለ። ከአመታት በኃላ በካቤኔ መመሪያ አውጥቶ ህገ-ወጥ የመሬት ወረራውን ህጋዊ አደረገ።
፫:- በ2000 ከኦህዴድ ኩማ ደመቅሳ መጥቶ” የመሬት እንቅስቃሴዎችን ለጊዜው አግጃለሁ፣ የቅድሚያ ትኩረቴ ከመሬት ጋር የተያያዘውን ሕገ-ወጥ ወረራና ዝርፊያ አደብ ማስገዛት ነው” አለ። ከአመታት በኃላ መመሪያ በማውጣት ህገ-ወጥ ወረራውን ህጋዊ አደረገ።
፬:- በ2004 ከኦህዴድ ድሪባ ኩማ መጥቶ ” የመሬት ባንክ አቋቁሜያለሁ፣ ሁሉም መሬት ወደ ባንኩ ስለሚገባ ሕገ-ወጥ የመሬት ወረራ አይኖርም” አለ። ህገ-ወጥ ወረራው ተባብሶ ቀጠለ።
፭:- በ2010 ከኦህዴድ ታከለ ኡማ መጥቶ” ህገ-ወጥ የመሬት ወረራ በእኔ ዘመን አይኖርም! የከንቲባነት ስራዬን እንደ ሼህ አላሙዲን ያሉ ለረጅም አመታት ባዶ መሬት አጥረው የያዙትን በመቀማት በመሬት ባንክ በማስገባት ጀምሬያለሁ” አለ። ከአመት በኃላ የተቀማው ባዶ መሬት ተመለሰ። በምትኩ ለአዲስአበቤ ዳቦ ቤት ተከፈተ። የመሬት ወረራው በከተማዋ ታሪክ ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ ተጠናክሮ ቀጠለ።
፮:- በ2012 ከኦህዴድ አዳነች አቤቤ መጥታ ” የመሬት እንቅስቃሴዎችን ለጊዜው አግጃለሁ፣ የቅድሚያ ትኩረቴ ከመሬት ጋር የተያያዘውን ሕገ-ወጥ ወረራና ዝርፊያ በመቀልበስ መሬቱን ወደ ባንክ ማስገባት ነው” አለች። እነሆ! አሁንም የመሬት ወረራው ተጠናክሮ ቀጥሏል።
በምስለኔ-መተዳደር-ይቁም!
የአዲስ-አበባ-ክልልነት-ጥያቄ-ይመለስ!
Filed in: Amharic