>

"በዜጎች ላይ የሚፈፀሙ ኢሰብዓዊ እና ማንነትን መሰረት ያደረጉ የማያባሩ ጥቃቶችን መንግስት ሊያስቆም ይገባል!!!" (ቴዎድሮስ ካሳሁን - (ቴዲ አፍሮ))

“በዜጎች ላይ የሚፈፀሙ ኢሰብዓዊ እና ማንነትን መሰረት ያደረጉ የማያባሩ ጥቃቶችን መንግስት ሊያስቆም ይገባል!!!”
ቴዎድሮስ ካሳሁን – (ቴዲ አፍሮ)

በቅድሚያ የከበረ ሰላምታዬን እያቀረብኩ በተለያዪ የሀገራችን ክፍሎች በተደጋጋሚ ጊዜ በዜጎች ላይ አላግባብ የሚፈፀሙ ኢሰብዓዊ እና ማንነትን መሰረት ያደረጉ የማያባሩ ጥቃቶች ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እጅግ ባልተገባ መንገድ ተስፋፍተው መቀጠላቸውን ተያይዞ የዜጎችን ሰላምና ደህንነት በዋናነት መጠበቅ ያለበትና ይህ ጉዳይ በቀጥታ የሚመለከተው የመንግሥት አካል ለጉዳዩ አስፈላጊውን ትኩረት ሰጥቶ አግባብ ያለዉ መንግስታዊ ሀላፊነቱን እንዲወጣና መሰል ጥቃቶች ዳግመኛ እንዳይፈፀሙ የሚጠበቅበትን የቅድመ ጥንቃቄ እንዲያደርግ በጥብቅ ለማሳሰብ እወዳለሁ።
በዚህ አጋጣሚ በነዚህ ጥቃቆች ህይወታቸውን ላጡ ወገኖች ፈጣሪ ነፍሳቸውን እንዲምር እና ለወዳጅ ዘመዶቻቸው መፅናናት እንዲሆንላቸው ከልብ እመኛለሁ።
ፍቅር ያሸንፋል!
ቴዎድሮስ ካሳሁን 
(ቴዲ አፍሮ)
Filed in: Amharic