ስለ ኢትዮጵያችን – አጫጭር መረጃዎች !!
ዘመድኩን በቀለ
* በአቢይ (አብዱ) አሕመድ ና ሽመልስ አብዲሳ ጉብኝቱ ማግስት ሰላም የነበሩት አፋርና ሶማሌ ጦርነት ገጥመዋል። የተተራመሰች ኢትዮጵያን ትፈጥርና የተረጋጋች ኦሮሚያን ትገነባለህ ነው ጨዋታው። ይሳካ ይሆን? ለማንኛውም 17 ኢትዮጵያውያን የኢሳ ጎሳ አባላት በዚህኛው ግጭትመገደላቸው ነው የተነገረው። ነፍስ ይማር።
ሞትና ችግር፣ ሰቆቃም ቸርቻሪው የኢትዮጵያ በላኤሰቡ አቢይ (አብዱ) አሕመድ የሶማሌ ክልልን ለመጎብኘት በሚል ሰበብ ባልተጻፈ ሕግ Akka ምክትል ጠቅላይ ሚንስትሩ የሆነውን ሽመልስ አብዲሳን ይዞ ሶማልያ ክልል ገብቷል። የሶማልያ ክልል እረፍትና አንጻራዊ ሰላም ማግኘት እነ አባ ገዳ አቢይ አሕመድን በስጩ ሳይልባቸው አልቀረም። አቢይ ባለበት ስፍራ ሁሉ ሽመልስ አብዲሳ ይገኛል። ይሄ ግድ ነው። ከሽመልስ በቀር ከኢሳይያስ አፈወርቂ ጋር እንዲገናኝ የሚፈቀድለት ሌላ የክልል ፕሬዘዳንትም አይገኝም።
•••
እናንላችሁ ይህ በእንዲህ እንዳለ በጉብኝቱ ማግስት ዛሬ ሰላም የነበሩት አፋርና ሶማሌ ጦርነት ገጥመዋል። ግጭትም ውስጥ ገብተዋል ተብሏል። ከቀጣሪዎችህ በተቀበልከው የቤት ሥራ አማካኝነት የተተራመሰች ኢትዮጵያን ትፈጥርና የተረጋጋች ኦሮሚያን ትገነባለህ ነው ጨዋታው። ይሳካ ይሆን? ለማንኛውም 17 ኢትዮጵያውያን የኢሳ ጎሳ አባላት በዚህኛው ግጭትመገደላቸው ነው የተነገረው። ነፍስ ይማር።
•••
በሌላ በኩሉ በወለጋ ሆሮ ጉዱሩ ወረዳ ዛሬም ሁለት የወሎ ዐማራ እስላሞች በአብይ አህመድ የውክልና ሸማቂ ቡድን ተረሽነው ተገድለዋል። ወሎ የኦሮሞ ነው እያሉ ወሎዬ እስላሞችን እየፈጇቸው ነው። ባለፈው ሳምንት ጉራፈርዳ ውስጥ በሶላት ላይ የነበሩ እስላሞች ተረሽነው በግሬደር በታረሰ የጅምላ መቃብር ውስጥ መቀበራቸው አይዘነጋም። ተረሻኞቹ አሙሩ ሼኽ ኢብራሂም ገንዘቤ እና ሼኽ የሱፍ ሙሐመድ የተባሉ ዐማሮች መሆናቸውም ተነግሯል። ሁለቱን ሟቾች ቀብረው ሲመለሱ ደግሞ ሙሐመድ አሊ፣ ሃሚድ ዳምጤ፣ ሙሳ ክብረት እና ባየ ኑሩ የተባሉ ዐማራዎች በኦነግ ሸኔ ጥይት ተተኩሶባቸው ቆስለው መተኛታቸውን ጊዮን ሚዲያ ሴንተር ዘግቦታል።
•••
በሰሜን በኩል ደግሞ ህወሓት፣ ብልጽግናና በድኑ ብአዴን አንድ ላይ አብረው የጎንደር ዐማራ በጸሎትም በትምህርትም ተመካክሮ ሰላም ውሎ ማደሩ የበሰጫቸው ጉደኞች ጎንደርን ቅማንትና ዐማራ በማለት ዳግም ሊያተራምሱ መዘጋጀታቸውን ራሳቸው የህወሓት ተከፋይ ካድሬዎች እየዘገቡት ይገኛሉ። ህወሓት ስንቋንና ቀለቧን አንበጣ ስለጨረሰባት ዐይኗን ወደ ጎረቤት ዐማራ ማማተሯ ግድ ነው የሚሉም አሉ። ምሥራቅ ዐማራ በአንበጣና በግሪሳ ወፍ እህሉ እየወደመ ነው። ትግራይም እንደዚያው። መጪው ጊዜ ከምር ደስ አይልም። ኤርትራ፣ ዐማራና ትግሬን ዐቢይ አህመድ ሳያቆሳቁሳቸው የሚቀርም አይመስልም።
•••
•••
በሌላ በኩል ፕሬዘዳንት ትራምፕ “ ኢትዮጵያ የፈረመችውን ውል ታክብር” ያሏትን ቃል በማስታወስ ዘግይቶም ቢሆን ኢትዮጵያ የፈረመችው ምን ዓይነት ውል ነው የሚል ጥያቄ መነሣት ጀምሯል። ዐቢይ አህመድ ከኢሳይያስ አፈወርቂ፣ ከሳኡዲ አረቢያና ከግብጽ እንዲሁም ከቢልጌ ስ፣ ከጆርጆ ሳሮና ከፈረንሳይ ከተባበሩት አረብ ኤምሬትስ ጋር በግሉ ሲፈራረም የከረመው ነገር ምንድነው? በኢትዮጵያ ስም ከአረቦቹ የተቀበለውስ ብር የት ገባ? የሚል ጥያቄ ማንሳት የጀመሩም አሉ። ያም ሆነ ይህ ቆይቶም ቢሆን መሃል ሰፋሪው ፒፕል ፍሬን መያዙ አይቀርም።
•••
የዐቢይ አህመድ ዘመን ዘመነ አሲዳም ነው። ረድኤት በረከት የሌለበት፣ ሞት የሠርግ ያህል የበዛበት፣ ራብ ቸነፈር አፍጦ የመጣበት፣ ኮቴ መናና ገፊ፣ አስጨናቂ ተስፋ የጨለመ በት ዘመን ነው። ወረርሽኝ፣ ግድያና ዝርፊያ ሞትና ስደት የነገሰበት ዘመን ነው። በተለይ መጪው ጊዜ ከባድ ነው። አንድ ፍሬ እንቁላል 6 ብር፣ ጤፍ 5ሺ ብር… … ሳላሙን ያምጣ።
•••
የኦሮሞው የአየር ኃይል አዛዥ ባለፈው ጊዜ ከአቢይ አህመድ ጋር ሆኖ “ወዳጃችን” ኢሳይያስ አፈውርቂን በመጋበዝ የአየር ኃይሉን ጓዷ ጎድጓዳ ሲያስጎበኘው መክረሙ ሳያንስ አሁን ደግሞ እንቁራሪቱ በሬ ካላከልኩ ብሎ “ ፕሬዘዳንት ትራንፕን ሲያስፈራራ ታይቷል። ሃገሪቷ ትፍረስ ካልሆነ በቀር ይሄ የማይመስል ፉከራ ነው። ይልቅ ከመርዳሳ አየር ኃይል ይልቅ የደብተራው መግለጫ በቂ ነበር። “ ኢትዮጵያን የሚዋጉ ይወድቃሉ” ብሎ ለእግዚአብሔር አሳልፎ እንደመስጠት በባዶ ሜዳ ፉከራ አያዛልቅም። ወዳጄ አሁን ጦርነቱ ዱርና ገደል መሯሯጥ አይፈልግም። አከተመ።
•••
ዓለም ጭንቅ ላይ ናት ፈረንሳይ በኮረና ምክንያት ዳግም ሎክዳውን ዐውጃለች፣ ጀርመን ሰኞ ትጀምራለች፣ ጎርፍ በሚልዮን የሚቆጠሩ ዜጎችን በኤዥያ አፈናቅሏል፣ እሳት አሜሪካንን እየፈጃት ነው። ፈረንሳይ ከእስላሞች ጋር እሰጥ እገባ ውስጥ ገብታለች፣ በቱርክ የምትደገፈው አዘርባጃን በኦርቶዶክሳዊቷ አርመኒያ ላይ ጦርነት ከፍታለች፣ 15 ሚልዮን ዐማሮች፣ ትግሬና አፋር እንዲሁም ኦሮሞዎች ራብ ከፊታቸው ተደቅኗል። ደቡብ አሜሪካም ጧ እያለች ነው። ዓለም በስብሳለች። አርጅታለች። በዚህ መሃል ሁሉ ግን የኢትዮጵያ ትንሣኤ ይታወጃል። ይኸው ነው።
•••
ሻሎም ! ሰላም !
ጥቅምት 19/2013 ዓም
ከራየን ወንዝ ማዶ።