“ከኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ሦስት በከፍተኛ ኃላፊነት ያሉ ጄኔራሎች እራሳቸውን በማግለል ወደ መቀሌ ገቡ!”
የኢትዮ-360 ወታደራዊ ምንጮች
የኢትዮ-360 ወታደራዊ ምንጮች እንደ ገለጹት ከሆነ ከኢፌዴሪ መከላከያ ሰራዊት ከፍተኛ ኃላፊነት እራሳቸውን በማግለል ወደ ትግራይ ያቀኑት የደቡብ ምስራቅ እዝ ምክትል አዛዥ፣ የሚሳኤል ክፍል ዋና አዛዥና የ12ኛ ክፍለ-ጦር ምክትል አዛዥ ናቸው። የደቡብ ምስራቅ እዝ ምክትል አዛዥ ብ/ጄ ግዑሽ ገብሬ ከግል ጥበቃ ኃይላቸው፣ ሹፌራቸውና መኪናቸው ጋር ወደ መቀሌ የገቡ ቢሆንም ከቀናት በኋላ መኪናቸውንና ሹፌራቸውን ወደ አዲስ አበባ መሸኘታቸውን ምንጮቻችን ጨምረው ገልጸዋል። የሚሳኤል ክፍል ዋና አዛዥ የነበሩት ብ/ጄኔራል ወዲእጽ እና የ12ኛ ክፍለ ጦር ምክትል አዛዥ በእጃቸው ያለውን ንብረት ወደ አዲስ አበባ መላክና አለመላካቸውን ማወቅ አልተቻለም።
ይህ በእንዲህ እንዳለ ጀነራሎቹ በወሰዱት አቋም ምክንያት በመከላከያ ሠራዊት ውስጥ ከፍተኛ ውጥረት የተከሰተ መሆኑን የኢትዮ-360 ምንጮች ገልጸዋል። ሁኔታዎች በዚህ ከቀጠሉ መከላከያው ወደ ማያባራ ተቋማዊ ቀውስ ስለሚገባ አገሪቷ በአጭር ጊዜ ውስጥ ወደ ከፋ የእርስ በእርስ ጦርነት ልትገባ እንደምትችል ምንጮቻችን ስጋታቸውን ገልፀዋል።
Ethio 360