>
5:21 pm - Thursday July 20, 3256

ከ200 በላይ አማሮች በአሰቃቂ ሁኔታ ተጨፈጨፉ...!!!  (ጎበዜ ሲሳይ)

ከ200 በላይ አማሮች በአሰቃቂ ሁኔታ ተጨፈጨፉ…!!! 

ጎበዜ ሲሳይ

* ከሁለት መቶ በላይ  አማራዎች በጊንቢ ዞን በአቢይ ኦነግ ሸኔዎች ተጨፈጨፉ። የአካባቢው ታጣቂ ሃይል ስፍራውን ለቆላቸው ሲወጣ፣ ሸኔዎቹ አማራዎችን ት/ቤት ውስጥ ሰብስበው ጨፈጨፏቸው። የአቢይ አስተዳደርና
 
 “ሚስቴ አማራ ልጆቼም ግማሽ አማራ እመኑኝ እኔ አሻግራችኋለሁ”  ያለን ከሕይወት ወደ ሞት ነበር እንዴ ??   
 
በዚህ ሌሊት መርዶ ነጋሪ ባልሆን ደስ ይለኝ ነበር ። ግን ከስፍራው በስልክ የሚመጣልኝ መልእክት እንቅልፍ የሚነሳ ነው።
በየጫካው የልቅሶ ድምጽ ከአውሬ ድምጽ ጋር ተቀላቅሎ ይሰማኛል። ሸሽተው ወደጫካ የገቡት ሰዎች በሹክሹክታ ነው የሚያወሩኝ ። የፈሩት አውሬውን ሳይሆን ኦነግ ሸኔን ነው። እባካችሁ ለወሬ ነጋሪ አትርፉን ሲሉ መተኛት አልቻልኩም።  በአይናቸው ያዩት ሲነግሩኝ የሟቾቹን ቁጥር ከ200 በላይ ያደርሱታል። ይህን ቁጥር ለመጥቀስ  እኔ ፈራሁ ግን እንሱ አሉ ። የመከላከያ ሃይል ቅዳሜ አካባቢውን ለቆ ሲወጣ ህዝቡ ገላችሁን ሂዱ ወይም ይዛችሁን ሂዱ ብለው የመከላከያ ተሽከርካሪ  (ኦራል) አግደው እንደነበር ተናግረዋል። “መከላከያም ታዘን ነው የወጣነው” በሚል  አጭር መልስ ሰጥቶ ጥሎ ወጣ ነው የሚሉት። የእለቱ እለት ኦነግ ሸኔ በመከላከያ እግር ገብቶ ዛሬ  የቀበሌውን ህዝብ ለስብሰባ እፈልጋችኋለሁ ብሎ  የተኩስ እሩምታ በመክፈት ከ200 በላይ ህዝብ እንደገደለ ነው የሚናገሩት።
አብይ አህመድ ደሴ ሆጤ አዳራሽ ተገኝቶ “ሚስቴ አማራ ልጆቼም ግማሽ አማራ እመኑኝ እኔ አሻግራችኋለሁ”  ያለን ከሕይወት ወደ ሞት ነበር እንዴ ??   ወገኖቻችን መከላከያውን አትሂድብን እናልቃለን ወይ ይዛችሁን ውጡ እንሂድላቸው ብለው እየተማፀኑ መከላከያው ጥሎ ወጣ ሰብስበው እረሸኗቸው።  እየተማከሩ እየተናበቡ አረዱን !!
              ሳግ ያነቀው  የደሴ አዛውንት ድምፅ
                                ——-
ኦነግን ከነሙሉ ትጥቁ ከኤርትራ ወደ ወለጋ እንዲገባ ማን ጋበዘው?  የጠ/ሚ  ዓቢይ አህመድ ኦሕዴድ ።
ኦነግ አገርቤት ከገባ በኋላ ኦሮሚያ ፖሊስ ውስጥ እንዲቀላቀል ማን አደረገው? የጠ/ሚ  ዓቢይ አህመድ ኦሕዴድ።
ኦነግ እንዲህ አገር ሲያሸብርና ንፁሃን ኢትዮጵያውያን ላይ ጭፍጨፋ ሲያካሂድ ቆሞ የሚመለከተው ማነው? የጠ/ሚ  ዓቢይ አህመድ ኦሕዴድ።
ጠ/ሚ ዓብይም ሆኑ ኦሕዴድ እንደ ኦነግ ቃታ ባይስቡም ኦነግ ጭፍጨፋና ሽብር የሚፈጥርበትን ስርአት በደንብ በማቀነባበራቸው ለጭፍጨፋውና ለሽብሩ ከኦነግ እኩል ልንጠይቃቸው ይገባል።
Filed in: Amharic