>

የሞኝ ዘፈን ሁል ጊዜ አበባየ (ዶ/ር በቃሉ አጥናፉ ታዬ)

Dr. Bekalu Atnafu

 የሞኝ ዘፈን ሁል ጊዜ አበባየ

ዶ/ር በቃሉ አጥናፉ ታዬ

 


በትናንትናው ምሽት/22/02/2013 በምዕራብ ወለጋ ዞን ጉሊሶ ወረዳ በአማራ ተወላጆች ላይ በደረሰው ጥቃት ከ250 በላይ አማራዎች እንደተገደሉ ተገልፆል፡፡ እንደ ጎበዜ ሲሳይ ገለፃ  የመከላከያ ኃይል ታዞ ቅዳሜ ጥቅምት 21/2013 አካባቢዉን ለቆ መውጣቱ ለኦነግ – ሸኔ የሽፍታ ቡድን እንዲፈነጭ ዕድል ስለሰጠው ግድያው እንዲፈፀም ሁኖዓል፡፡ 

ዛሬም የአማራ ብልፅግና ጥቃቱን የፈፀመው ትህነግ/ህወሀት ከኦነግ – ሸኔ ጋር እንደሆነ ይገልፃል፡፡ የሞኝ ዘፈን ሁልጊዜ አበባየ፡፡ የወደቀን የማፊያ ቡድን ትህነግ/ህወሀትን ዘወትር እንደ ምክንያት ማቅረብ የእናንተን ደካማነት ያሳያል እንጅ የወደቀውን ቡድን ታላቅነት አያሳይም፡፡ በየትኛውም ጊዜ በክፋት ከደነዘዘ እና ዘረኛ ከሆነ ቡድን ጋር ህብረትን እየፈጠራችሁ በስልታዊ ጥቃት ህዝቡን ዛሬም ለዕልቂት ትዳርጉታላችሁ፡፡ ላለፉት ሀያ ሰባት ዓመት አንድ ቃታ ስቦ የማያውቅ ቡድን ዛሬ ኃይልን እንዴት አገኘ ብላችሁ እንኳን ጉዳዩን ልትመረምሩ አላቻላችሁም፡፡ ዛሬም ትህነግ/ህወሀትን ለተንኮል ስራዎች ሁሉ እንደ ምክንያት አድርጋችሁ አታቅርቡት፡፡ የአማራ ብልፅግና ሆይ፡ ከቻላችሁ ቆፍጠን ያለ እርምጃ ውሰዱ፤ ህዝባችሁንም ታደጉት፤ ካልቻላችሁ ቦታውን ልቀቁትና ወንዶች ይያዙት፡፡ ለዚህ ሁሉ ለተዘራው የጥፋት ዘር የሚሰበሰብበት ጊዜ ይመጣል፡፡ እናንተም በድርጊታችሁ ተጠያቂ ትሆናላችሁ፡፡

Filed in: Amharic