>

ትህነግ የፈፀመው ሽብር ለሕዝብ ይፋ ይደረግ‼️  (ጋዜጠኛ ጌታቸው ሽፈራው)

ትህነግ የፈፀመው ሽብር ለሕዝብ ይፋ ይደረግ‼️

ጋዜጠኛ ጌታቸው ሽፈራው

በፎቶው የምንመለከተው በባንዳው ህወሀት ክህደት የተፈጸመበት አገር ወዳዱ ጀግና የሰሜን እዝ ዘመቻ መምሪያ ዋና አዛዥ..!!!ብርጋዴር ጀኔራል አዳምነህ መንግስቴ {ዘገመሃሎ በላይ ዘለቀ} ይባላል።
ብርጋዴር ጀኔራል አዳምነህ መንግስቴ  የሰሜን እዝ ዘመቻ መምሪያ ዋና አዛዥ ነው። ወያኔ ሰሜን እዝን ለመዝረፍ ከመሞከሯ በፌት የብርጋዴል ጀነራል አዳምነህ መንግስትን ጠባቂዎች ረሽኖ ጀነራሉን አግቷል አዳምነህ እስካሁን ድረስ ያለበት ሁኔታ አይታወቅም።
ብጋዴር ጀኔራል አዳምነህ መንግስቴ በቅጽል ስሙ ዘ-ገመሃሎና በላይ ዘለቀ በ21 ኛ ክፍለ ጦር በብርጌድ አዛዥነት በገመሃሎ ግንባር ውጊያ ጀብድ የፈፀመ ጀኔራል ነው።
በገመሃሎ ውጊያ በ1990 ዓ.ም 3 ጊዜ ቆሳሏል። በ1992 ዓ. ም የ11ኛ ክፍለ ጦር ዋና አዛዥ ሆኖ በዛላንበሳ, አልቴና, አይጋ, መለኩሴቶ ግንባር ጀብድ የፈጸም ወታደራዊ ከፍተኛ መኮነን ነው።
በአሁኑ ወቅት የሰሜ ዕዝ ዘመቻ መምሪያ ዋና አዛዥ ነው። የሰሜን ዕዝ ዋና አዛዥ ስለሌለው ዋና አዛዥነቱንም አጣምሮ በመምራት ላይ ያለ ጀኔራል ነው። የዚህ ጀኔራል ሁኔታ እስካሁን ድረስ አልታወቀም። ይህ ጀኔራል በከሃዲዎች አንድ ነገር ቢሆን የምናወራርደው ሂሳብ እጅግ እጅግ እጅግ በጣም ከባድ ነው!!!
ጀኔራል አዳምነህ መንግስቴ አንድ ነገር ከሆነ የሚናወራርደው ሂሳብ በምን እንድሚገለፅው አናውቅም።
በመሆኑም መንግስት ትህነግ የፈፀመው ሽብር  ለሕዝብ ይፋ ማድረግ አለበት።በተለይ ከአሁን ቀደም አማራው መከላከያ ሰራዊቱ ውስጥ ውክልና እንዳይኖረው በተለያየ ስም  ፈርጆ  ከ45 ሺህ በላይ  አማራዎችን ከሰራዊቱ ያባረረው ትህነግ በሰሞኑ ሽብር በአማራነታቸው አፍኖ የረሸናቸውን የአማራ መኮንኖች ጉዳይ ግልፅ ማድረግ አለበት። ከሃዲዎቹ የትግራይ የሰራዊት አመራሮች የፈፀሙትን ክህደትና ሽብር በይፋ በዝርዝር ለሕዝብ መግለፅ አለበት!
የራሳችን ጓዶች ናቸው ብለው ባመኗቸው የትግሬ ተወላጆች ወታደሮች ደባ የተገደሉትን፣ የቆሰሉትን የመከላከያ ሰራዊት አባላት ጉዳይ ለኢትዮጵያ ሕዝብ ግልፅ ማድረግ አለበት!
ከሃዲዎቹ የትግራይ ተወላጅ መከላከያ ሰራዊት አመራርና አባላት ከትህነግ ጋር ተመሳጥረው አሳልፈው ስላስጠቁት መከላከያ ሰራዊት የትግራይም  ሕዝብ ጭምር በዝርዝር ማወቅ አለበት!
Filed in: Amharic