>

ሰለ ህዳሴው ግድብ  የተሞገቱት ፖለቲከኞች  አሸነፉ....!!! (ህብር ራዲዮ)

ሰለ ህዳሴው ግድብ  የተሞገቱት ፖለቲከኞች  አሸነፉ….!!!

ህብር ራዲዮ

ኢትዮጵያ በአባይ ወንዝ ላይ በምትገነባው የህዳሴው ግድብ ዙሪያ የአሜሪካው ፕ/ት ዶንል ትራምፕ  በቅርቡ ተገቢ ያልሆነ  ፣ለግብጽ ያደላ አነጋገር በመናገራቸው ቅሬታቸውን በአደባባይ በመግለጽ እና ፍትህ ለኢትዮጵያ እና ለኢትዮጵያዊያን ብለው የጮኹ  ሁለት  የአሜሪካ ፖለቲከኞች በሰሞኑ የምረጠኝ  ዘመቻቸው  ዳግማዊ ድል ቀናቸው።
አሶሴትድ ፕሬስ እንደ ዘገበው በኮሎራዶ  ግዛት ስድስተኛው ኮንግርጌሽናል ዲስትሪክት የዲሞክራቲክ  ፖርቲን በመወከል የተወዳዳሩት በቅርብ ስለ ኢትዮጵያው የህዳሴ ግድብ ከትውልደ ኢትዮጵያኖች  ጎን  የቆሙት  ጃሰን ክሮው ተፎካካሪዎቻቸው ሪፖብሊካኑ ስቲቭ ሀውስን 57.1% ለ 40% በሆነ  ልዩነት  አሸንፈዋቸዋል።
የህዝብ እንደራሴው  ክሮው ፕ/ት ትራምፕ በቅርቡ በህዳሴው ግድብ ዙሪያ ከጋዜጠኞች ፊት  “ግብጽ ግድቡን ልታጋየው ትችላለች” ማለታቸውን”  በተመለከተ “ሀላፊነት የጎደለው፣የአሜሪካ የረጅም አመታት አጋር የሆነው የ ኢትዮጵያ  ማንነትን ያላገናዘበ ነው”ከማለታቸው  በተጨማሪ ፕ/ት ትራምፕ በኢትዮጵያ ላይ የጣሉት የ130 ሚሊዬን ዶላር ማነቆ እንዲነሳ እና የታማኝ  ታዛቢነት ሚናን እንዲጫወቱ በቅርቡ በትዊተር ገጻቸው ላይ መጻፋቸውን መዘገባችን አይዘነጋም።
ከዚሁ ከአፍቃሪ የህዳሴው ግድብ ጉዳይ   እና የአሜሪካ ምርጫ  ጋር በተያያዘ  የመጀመሪያው ትውልደ  ኢትዮጵያዊው የኔቫዳ ግዛት  ም/ቤት  አባል አሌክሳንደር አሰፋ ተፎካካሪዎቻቸውን  66.5% ለ21.3% እና 12.2% በሆነ በከፍተኛ  ብልጫ በማሸነፍ  ለሀለተኛ  ጊዜ ተመርጠዋል ሲል ኬኤ ላኣስ ዘግቧል።በ42ኛው ዲስትሪክት የተወዳደሩት  አሌክሳንደር  የመራጩ ፣ማህበረሰብ ችግሮችን ለማዳመጥ እና ለመቅረፍ  የበኩላቸውን እንቅስቃሴ  በማድረግ ላይ ይገኛሉ።
እኤአ ከ2018 ጀምሮ የምክር ቤት አባል የሆኑት አሌክሳንደር አስፋ የፕ/ት ዶናል ትራምፕ የቅርቡ ጸረ የህዳሴው ግድብ አስተያየታቸውን “ብስለት የጎደለው፣ከፋፋይእና የዲሞክራሲያዊ ወዘና የሌለው አሰተያየት ነው ” በማለት በጽኑ  ማጣጣላቸው አይዘነጋም።
Filed in: Amharic