>
5:13 pm - Tuesday April 19, 3188

ዛሬም እንደ ትላንቱ አሸባሪው የትሕነግ ቡድን በሰላማዊ ዜጎች ላይ የዘር ማጥፋት ወንጀል ፈፅሟል! (አ.ብ.ን)

ዛሬም እንደ ትላንቱ አሸባሪው የትሕነግ ቡድን በሰላማዊ ዜጎች ላይ የዘር ማጥፋት ወንጀል ፈፅሟል!

አ.ብ.ን

* ከአምስት መቶ በላይ ንጹሀን አማሮችን የትሕነግ ጦር የአካባቢውን አማራ ህፃናትና እናቶች ሳይቀሩ ገጀራ፣ የተለያዩ ስለት ያላቸውንና ማነቂያ ገመድ በመጠቀም ጭምር በጅምላ ጨፍጭፎ ከቦታው ለቆ መውጣቱ ታውቋል…!!!
 
አሸባሪውን የትሕነግ ቡድን ለአንዴ እና ለመጨረሻ ጊዜ ለመደምሰስ እየተደረገ ባለው ተጋድሎ የጀግናው መከላከያ ሰራዊት፣ የአማራ ልዩ ኃይል እንዲሁም የአማራ ሚሊሻና ፋኖ እያገደረጉት ባለው የማጥቃት እርምጃ እግሬ አውጭኝ ብሎ እየፈረጠጠ ይገኛል።
ሆኖም ይህ ኢ-ሰብአዊና የታሪክ አተላ ስብስብ በአማራ ሕዝብ ላይ እስካሁን ሲያደርስበት በነበረው ግፍ ባለመርካቱ ንፁሀን አማራዊ ወገኖችን ዛሬም በጅምላ መጨፈጨፉን ቀጥሏል።
ትሕነግ በማያቋርጥ ሽሽትና ሽንፈት ውስጥ እንኳ ሆኖ ፊት ለፊት ሊገጥመው ያልቻለውን ሕዝብ ወገን ናቸው የሚላቸውን አማሮች በመለየት የዘር ፍጅት እየፈፀመ ይገኛል።
በማይካድራ ከተማና አካባቢው በነበረው የትሕነግ ጦር ላይ በተከፈተው መጠነሰፊ ጥቃት ምክንያት ሸሽቶ የፈረጠጠው የትሕነግ ጦር ከተማዋን ከመልቀቁ በፊት ንፁሀን ሰላማዊ ዜጎችን በአማራ ማንነታቸው ብቻ ለይቶ የዘር ማጥፋት ወንጀል እንደፈፀመባቸው ተረጋግጧል።
የትሕነግ ጦር የአካባቢውን አማራ ህፃናትና እናቶች ሳይቀሩ ገጀራ፣ የተለያዩ ስለት ያላቸውንና ማነቂያ ገመድ በመጠቀም ጭምር በጅምላ ጨፍጭፎ ከቦታው ለቆ መውጣቱ ታውቋል። በርካታ አስክሬኖችን በትራክተር ለማጓጓዝ ሙከራ እያደረገ ባለበት ሁኔታ የመከላከያ ሰራዊትና የአማራ ሀይል ስለደረሱበት አስከሬኖችን በየቦታውና በየቱቦው ጥሎ ሄዷል።
የኢትዮጵያ ጥምር ጦር ማይካድራን ሲቆጣጠር በትህነግ በጅምላ የተጨፈጨፉ ንፁህ የ500 አማራዎችን አስከሬን አግኝቷል :: ይሄን የጦር ወንጀል ዓለም ሳያየው የአማራ ክልል መንግስት ወገኖቻችንን መቀበር የለበትም :: በፍጥነት የዓለማቀፍ ሚዲያዎችን እና የሰባዊ መብት ድርጅቶችን ቦታው ድረስ አስገብቶ  የተፈፀመውን ወንጀል ማሳየት ይኖርበታል :: መቀመጫቸውን በአዲስ አበባ ከተማ ላደረጉ ዲፕሎማቶች እንዲሁም ለUN እና ለAU  ሪፓርት ማድረግ ይኖርበታል ::
ከእንግዲህም ከጠቅላይ ሰፈር በሚሰጠው ትዕዛዝ መሰረት በትሕነግ ላይ እየተካሄደ ያለው ይህ ጦርነት አሸባሪው የትህነግ ቡድን የሚፈፅማቸውንና ሊፈፅማቸው የሚችሉ ጅምላ ጭፍጨፋዎችን ከግምት ውስጥ ባስገባ መልኩ እንዲሆን አብን ያሳስባል ።
መንግስት በጎንደር—ወልቃይት፣ ፀገዴ፣ ሁመራና በቀሪዎቹ አካባቢዎች እና በራያ በተለያዩ አካባቢዎች ትሕነግ ከመሸሹ በፊት ተመሳሳይ የዘር ማጥፋት ወንጀሎችን እንደሚፈፅም ታሳቢ በማድረግ የቅድመ መከላከልና ንፁሀንን የመታደግ ስራ ላይ ትኩረት እንዲደረግ በአፅንኦት እንጠይቃለን።
አሁን የትሕነግ ኃይል በተቃራኒ ጎራ በጦርነት የተሰለፈ ጠላት ብቻ ሳይሆን በዓለምአቀፍ የጦር ሕግጋት ፍፁም የማይገዛ ፀረ-ሰው ኃይል ነው።
በመንግስት በኩል በትሕነግ ኃይል ላይ የተከፈተውን አገራዊ ጦርነት በፍጥነትና በተሟላ ስኬት ለማጠናቀቅ ከሚደረገው የማጥቃት ስራ ጎን ለጎን በጁንታው ኃይል ታግተው የሚገኙ ንፁሀንን መታደግ ይገባል። በተጨማሪ በዚህ ሂደት በትሕነግ ኃይል እየተፈፀሙ ያሉትን ባጠቃላይ በስብዕና ላይ የሚፈፀሙ ወንጀሎችን በልዩ ሁኔታ ደግሞ በአማራ ሕዝብ ላይ የሚፈፀሙትን የዘር ማጥፋት ወንጀሎችን በተመለከተ የተጠናከሩ ማስረጃ የማሰባሰብ ስራዎች በፍጥነት እንዲካሄዱ እየጠየቅን የትሕነግ ኃይል ከተደመሰሰ በኋላ በየአካባቢዎቹ የቀሩና በሰፊው ያስታጠቃቸውን ኃይሎች በአስቸኳይ ትጥቅ የማስፈታት ስራ እንዲሰራ አብን ለማሳሰብ ይወዳል።
የኢፌድሪ የሕዝብ ተወካዬች ምክር ቤት በቅርቡ በአማራ ሕዝብ ላይ የዘር ማጥፋት ወንጀል እንደተፈፀመ መግለፁን መነሻ በማድረግ አሁን በሚካሄደው ጦርነት መካከል በትሕነግ ኃይል እየተፈፀሙ ያሉትን ጭምር በማሰናዳት፣ ባጠቃላይ በዚህ ኃይልና በግብረአበሮቹ ሲፈፀሙ የቆዩትን የዘር ማጥፋት ወንጀሎች የሚያጣራ ገለልተኛ ኮሚሽን እንድሰይምም ድርጅታችን የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ(አብን) ጥሪውን ያቀርባል።
Filed in: Amharic