>
5:26 pm - Wednesday September 17, 9659

አትመፃደቁ!!! በደም የተፃፈ ህገ መንግሥት የሚባል ነገር የለም!!!  (ብርሀኑ ተክለአረጋይ)

አትመፃደቁ!!! በደም የተፃፈ ህገ መንግሥት የሚባል ነገር የለም!!!

 ብርሀኑ ተክለአረጋይ

*  ይህንን ዜጎችን የማረጃ ቢላ ለክልሎች የሚሸልም የፍጅት ሰነድ  መሸቀያ የስልጣን እድሜ ማራዘሚያ አታድርገው
 
 “ህገመንግሥቱ” የተፃፈው በወረቀትና በቀለም ያውም በሻዕቢያ፣በወያኔና ኦነግ መሪዎች ጠባብ ጭንቅላት ነው። (የዛሬን አያርገውና መረራ ጉዲና አሁን እንዲህ ጠበቃው ሳይሆን የተፃፈበትን ቀለም ያህል ዋጋ የማያወጣ ብሎ ይጠራው ነበር)
አማራው በገዛ ሀገሩ ተቅበዝባዥና ታዳኝ እንዲሆን የተፈረደበት፣ጋምቤላው በጅምላ መቃብር የተከመረው፣ የኦሮሞ ህፃናት በሁለት ጥይት እንዲመቱ የፈቀደው፣አፋርና ሱማሌን ያናከሰው ፣ማይ ካድራ ደም እንደ ጎርፍ የፈሰሰው፣መተከል ጆሮ ጭው የሚያደርግ አውሬያዊ ድርጊት የተፈፀመው፣ ምስኪኑ ወታደር ባመነው አካል ተከድቶ ታንክ የተነዳበት … በዚህ ስሁት “ህገመንግስት” ሀሳባዊ ፈቃድ ነው።
ወዳጄ ከፋፋዩ “የብሔር ብሔረሰቦች መብት አጎናጸፍኩ” ባዩ ህገመንግስት ያመጣብንን ጣጣ ወደ ጋርዮሽ ስአተ ማህበር የጎተተን ሂደት ላመላክትህ:-
የብሔር ብሔረሰቦች ቀን ብለህ እሽኮለሌ አትበል። ብሔሮች ምን እንደሚሰሩ እናውቃለን። ገና ከድንጋይ ዘመን ያልተላቀቁ አራጆች፥ ኅላ ቀር፥ በአጉል ልማድ የታሰሩ ናቸው።
የሴት ቂንጥር ቆርጦ ለውሻ የሚጥል፥ የሰባት ዓመት ልጅ እጁ ለቆረፈደ የአርባ ዐመት ሽማግሌ የሚድር፥ ወፍጮ እንዲሰራ የታረደ ህጻን ደም የሚቀባ፥ ፍንጭት ልጅ እርግማን ነው ብሎ ወደ ገደል የሚወረውር፥ በቁራጭ መሬት የጎረቤቱን አናት በመጥረቢያ የሚተረትር፥ የበሰበሰ ቅቤ አናቱ ላይ ደፍድፎ የሚዞር፥ ደም መላሽ ብሎ እስከ ሰባት ትውልድ ምንም የማያውቀውን የሩቅ ዘመድ በጥይት የሚጨፈጭፍ፥ ቦረንትቻ፥ ቃልቻ፥ አዋቂ እያለ ጥቁር በግና ገብስማ ዶሮ ሰው በር ላይ የሚጥል ምናምን ምናምን እኮ ነው።
 ይህንን ዜጎችን የማረጃ ቢላ ለክልሎች የሚሸልም የፍጅት ሰነድ  መሸቀያ የስልጣን እድሜ ማራዘሚያ አታድርገው
የብሔር ብሔረሰቦች ቀን የሚለውን ተረትህን ተውና፥ ይሄ ኅላ ቀር ሕዝብ እንዲነቃ፥ እንዲማር፥ እንዲሰለጥን አድርገው። የተሸከመው ድብቅ አውሬነት አለ። በዕውቀት መርዙን እንዲተፋ አድርገው። ዘላለም መሸቀያ አታድርገው።
ወገን
ብሔረሰብ ብቱቶውን ለብሶ ስቴዲየም ውስጥ ሲዘል፥ እስክስ ሲል፥ ሲሽከረከር ዓለም ጥሎት እየገሰገሰ ነው። አንተ ባህል፥ ቋንቋ፥ ማንነቴ ስትል ዓለም ላብ ውስጥ ስንዴና ስጋ ለማምረት ይባጠሳል። ለሺ ዘመን ቀንበር ስትጎትት ሌላው ዓለም በዚህ፥ በኩል ገበያውን በሰው ሰራሽ ጥጥ፥ ስንዴ፥ ገብስ ቅብርጥሶ እያጥለቀለቀልህ ነው።
መዝጊያ
ደሞ እኮ ደፋር ነህ። ባህሌ ብለህ ሞፈር እና ቀንበር ይዘህ ትወጣለህ። ባህሌ ብለህ እንጥል መቧጠጫ ምላጭህን ይዘህ ትመጣለህ።

ከፋፋዩ “ህገ መንግስት” ይለወጥ!!!

Filed in: Amharic