>
1:34 pm - Thursday March 30, 2023

ዐቢይ እና ጓደኞቹ ከህወሓት የበለጠ ዐማራ ጠል ናቸው ስንል...!?! (ዘመድኩን በቀለ)

ዐቢይ እና ጓደኞቹ ከህወሓት የበለጠ ዐማራ ጠል ናቸው ስንል…!?!

ዘመድኩን በቀለ

… አንዱ የተለመደ እንደ እኔው የሐረርጌ ቆቱ መራታ የሆነ ወዳጄ ዘመዴ ይኸው “ዛሬም በመተከል ዐማሮች በኦሮሞው ኦነግና በጉምዙ አሻህድሊ ሃሰን ታረዱ” ይለኛል። አያይዞም ማስረጃ ብሎ የዐማራ መገናኛ ብዙሃንን የዐማራ ነታረድ የመርዶ ዜና አባሪ አድርጎ ይልክልኛል። https://www.facebook.com/118697174971952/posts/1430640457110944/
… እኔም አልኩት። መለስኩለትም። ኦቦሌሶ የዐማራ አራጁና አሳራጁ እኮ ራሱ ዐቢይ አሕመድ አሊ ነው። እሱ ሳያውቅ ሽመልስ አብዲሳ የሚፈጽመው 0.5 የሆነ አንዳች ነገር የለም። ዐቢይ እና ጓደኞቹ ከህወሓት የበለጠ ዐማራ ጠል ናቸው። ባለፉት 3 ዓመታት ዐቢይ በሚመራት ኦሮሚያ የታረዱትን ዐማሮች፣ የወደሙትን የዐማሮችና የኦርቶዶክሳውያን ንብረቶች ስታይ ዐቢይ አሕመድ ምን ያሕል ዐማራ ጠል እንደሆነ ይገለጥልሃል። እናም አሁን እነ አቡቹ ህዳሴ ግድብ ዙሪያ ለመሥፈር ሲሉ ወያኔ ጠፍጥፎ ከፈጠረው አዲሱ የቤኒሻንጉል ክልል ውስጥ ባለቤቱን ባለ ርስቱን የጎጃም አገውና ዐማራ ይጸዳ ዘንድ ተግተው እየሠሩ ነው። ይሄ የህወሓትም የኦነግም ፍላጎት ነው።
… በተለይ የዐማራው ራያና ጠለምትን፣ ወልቃይትና ጠገዴን አስነጥሶ በንጥሻ አንጥሴ ብሎ አስደንብሮ ርስቱን ማስመለሱ ከኦህዴድ መንደር ሽብር ፈጥሯል። ቀውጢ ነው የሆኑት። የሌለ ነው የደነበሩት። እናም አሁን የሰሜኑ ግርግር በቶሎ ካለቀ ዐማራው ተራራው በህወሓት የተነጠቃቸውን ቀሪ ርስቶቹን ያስመልሳል በሚል ስጋት ቶሎ ቶሎ ዐማራውን በማረድ፣ ጉበት ኩላሊቱንም በመብላት በዐማራ ደም ኦነጎቹ የሌለ መወፈር፣ መፋፋትም ሳይፈልጉ አልቀሩም።
… የቤኒሻንጉሉን መሪ አሻድሊ ሃሰንን መተማመኛም የሰጡት ይመስላል። እኛ እያለን ማንም አባቱ ዞር ብሎ አያይህም። ጫፍህንም አትነካም። እያሉ በዝግ ስብሰባ ሳይሞሉት አይቀሩም። በአደባባይ ጭምር በላዩ ላይ እጃቸውን ጭነው ለፈፀመው ዐማራን የማረድ ተግባሩ ኬክ ሲያስቆርሱት ታይተዋል። እናም የጉምዙ ሰውዬ የልብ ልብ የተሰማው የዐቢይ ሽመልስን ይሁንታ አግኝቶ ነው። ሃላስ።
… አሁን ዐቢይ የዐማሮቹ የአዴፓዎች አቋም እየጠነከረበት ከመጣ በቅርቡ ኦሮሞዋን መዓዛ አሸናፊን በማዘዝ ጃዋር መሃመድን ያስፈታዋል። ይፈታዋል። ጃዋርም ወጥቶ ይቀውጠዋል። አቢይንም ኦሮሚያንም ያተራምሳል። ይሄ አንደኛው ነው።
… ሌላው እነ ሽመልስ አብዲሳ ቶሎ ቶሎ ዐማራን ካፀዱለት በኋላ በሚፈልገው መጠን ዐማራ መጽዳቱን ካረጋገጠ አቢቹ ሽመልስንም አሻሃድሊንም ይበላቸዋል። ይበላቸውና እነሱን እንደ ለማ መገርሳ አጣጥሞ ሌላ በላተኛ ያስቀምጣል። ያለ በለዚያ ራሱን እነ ሽመልስ ይበሉታል። ሂኢ …
… ይሄ ነገር ግን ታዲያ ለዐቢይም ሆነ ለሽመልስ፣ ለአሻህድሊም መንግሥት ፍጻሜያቸውን የሚያቀርብ ይመስለኛል። ግብአተመሬት !!
… በሌላ በኩል ከዐማራው በኩል በቀጣይ የሚመጣውን ወላፈን ለመመከት በሚል ሰበብ የኦሮሚያው ሽመልስ አብዲሳም፣ የጫካው ኦነግም በሚሊሻ ሥልጠና እና ምርቃት ላይ መጠመዳቸው እየታየ ነው። https://www.facebook.com/106158897520824/posts/227162135420499/ ። የዐማራ ልዩ ኃይል የቅጥር ማስታወቂያ ስላወጣ ብቻ እሪሪ ብላ አደባባይ የወጣችው ሙፈርያት ካሚል የእናቷን ዘመዶች የሚሠሩትን ግን ባላየ ባልሰማ ላሽ ማለቷም አስተችቷቷል።
… በሌላ ወፍራም ያልተጣራ ወሬ ዐቢይ አሕመድ ለጦር መሪ ጄነራሎቹ ደብረ ጽዮንን እንደምንም በሕይወት ይዛችሁ አምጡልኝ ብሎ መማጸኑም ተሰምቷል። እሱን ሳታቆስሉ በህይወት አምጡልኝ ብሏል ነው የሚባለው። ሌሎቹንስ? ሲባል እንደፈለጋችሁ የፈለጋችሁትን እርምጃ ውሰዱባቸው። ደፂን ግን በህይወት ያዙልኝ ብሎ መማጸኑን ነው የውስጥ አዋቂ ነን የሚሉ ሹክ እያሉን ያሉት። ሂኢ አቢቹ ግን ምን አስቦ ነው። አይ የልጅ ነገር።
… አቢቹ ደፂን በህይወት የፈለገው ጠጋግኖ የህወሓትን ነፍስ ሊዘራባት ሳይፈልግ አልቀረም። ኤርትራዊቷን ኬሪያ ኢብራሂምንም ምንም ዓይነት ጭረት ሳይነካት በሳኒታይዘር የታሸ እጇን ለመንግሥት ሰጠች የተባለውንና እጅ መሥጠቷንም ተከትሎ ለዐቢይ አሕመድ አቀረበች የተባለውን ውዳሴ የሰሙ አንዳንዶች “የሌለ ነው የሸከከን” ቢሉም አይፈረድባቸውም የሚሉም አሉ።
… በሌላ ዜናም የእነ ሽመልሱ የኦነጉ ክንፍ ሰላማዊዋን ሶማሊያን በመበጥበጥ ጅጅጋን በማወክ ሙስጠፌን ለመፈንቀል እንቅስቃሴ ጀምረዋል። እንደ አዲስ ዐማሮችን ማሰቃየት በጅጅጋ ተጀምሯል። እናም የሙስጠፌ በኢትዮጵያውያን ሁሉ ዘንድ የተለየ ክብር ማግኘት አቢቹን ሄጵ ሳያሰኘው አልቀረም የሚሉ አሉ። እንደ ለማ መገርሳ ሳይሆን እንደ ዶር አምባቸው ብቻ እንዳይበላው ብለው የሚጸልዩም አሉ የሚሉ አሉ። ሙስጠፌ ፈጣሪ ይሁንህ።
… አሁን የደፈረሰው ሁሉ እየጠራ ነው። ከኦህዴድ መንደር በጭባጫው እየበዛ ነው። ክንብንቡም እየተገለጠ ነው። ታዬ ደንደአ እንኳ የሌለ እየወበራ በው። ብአዴንም ሄጵ ማለት ጀምሯል። ዐማራ ተራራው ግን መሬት የወረደ ሥራ እየሠራህ ወጥር !!  ወጥር ወጥርና እኔንም ኢትዮጵያንም ነፃ አውጣን  !!
… በማርያም  !!
Filed in: Amharic