>

ኢትዮጵያዬ ክብር ለሚገባው ክብር ስጭ...!!! (ሳሙኤል ገዛህኝ)

ኢትዮጵያዬ ክብር ለሚገባው ክብር ስጭ…!!!

ሳሙኤል ገዛህኝ

እኝህን ሰው ልናመሰግን: አገራቸውን መልሰው እንዲያዮ ልንረዳ: የክብርም አቀባበል ልናደርግ ይገባል:: ገብረመድኅን አርአያ የቀድሞው የህወሃት አባል የነበሩ ናቸው:: የህወሃትን የውንብድና እና አገር የማፍረስ ስራ ጠንቅቀው ከተረዱ በኇላ: ከድርጅቱ ከድተው ለኢትዮጲያ መንግስት በመግባት: ከምስረታው ጀምሮ እስከ ውድቀቱ ድረስ ያለውን የህወሃትን እኩይ እቅድ እና ስራ በዝርዝር አስረድተዋል:: በኢህዲሪ ዘበን በኢትዮጵያ ቴሌቭዥን በተከታታይ ፕሮግራሞች ማብራሪያ ከመስጠታቸውም በላይ: “የወያኔ ታላቁ ሴራ” የሚል አጭር መድብል ከጏደኛቸው አብርሃም ያየህ ጋር አዘጋጅተው ለኢትዮጵያውያን ግንዛቤ እና ለታሪክ ፍርድ እንዲሆን አቅርበው ነበር::
አቶ ገብረመድህን ከአገራቸው ከወጡም በኇላ (ከአውስትራሊያ) ያለማቋረጥ በተለይ ለኢሳት ቴሌቭዥን ቅርብ በመሆን ስለ ህወሓት ማንነት እና ባህሪ ማብራሪያ ሲሰጡ ኖረዋል:: የህወሃት ውድቀት እንደማይቀር ሲናገሩ የነብሩት ገብረመድህን: ዛሬ ውድቀቱን እና ሽንፈቱን በህይወት ቆይተው በማየታቸው እጅግ ደስተኛ ሆነዋል:: ደስታቸው ግን ሙሉ የሚሆነው ወደ አገራቸው ተመልሰው በትግራይ ምድር ህወሓት ዜጎችን የሚያሰቃይበትን እና የሚገድልበትን ምስጢራዊ ስፍራዎችን ለህዝብ ካጋለጡ በኇላ እንደሆነ ይናገራሉ:: እግዚአብሄር ጤናና ሰላም ይስጥዎት::
Filed in: Amharic