ጌታቸው ሽፈራው
በታዬ ደንድኣ በኩል የምትወረወረው የእብሪት ቃላት ሆን ተብላና ታቅዶባት ነው። የማንነት ጥያቄ ከሕዝብ ጋር ያስታርቃል ሲባል ስላዩ ነው። የአማራ ርስት የሆኑትን ራያና ወልቃይት ጠገዴ ጉዳይ አልፎ አልፎ ሲይዝ በአማራ ፌስቡከኛ ይውደም የሚባለው የአማራ ብልፅግናም “አይዞህ” ሲባል ስለሚያዩ ነው።
ኦህዴድ እስካሁን አዲስ አበባን አስረክባችኋለሁ እያለ ነበር በሕዝብ ዘንድ ድጋፍ የሚያገኘው። አሁን ከእነ ጃዋርም ከእነ ለማም ጋር ተኮራርፎ ተጨማሪ ማንደጃ አስፈልጎታል። ስለሆነም በምንም ተአምር የራሱ ያልሆነውን፣ ኦነግ በእብሪት ካርታ የሳለበትን የራያን ጉዳይ አንስተው በኦሮሞ ሕዝብ ዘንድ ተቀባይነት ለማግኘት ነው። ሆን ተብሎ፣ ተነጋግረውበት የሚሰጥ አጀንዳ ነው። ወለጋን ሰላም ያላደረገ፣ ቡራዩና ሰላሌ ወጥቶ መግባት የማይችል የሌላውን ርስት የሚያነሳው ለዛው ነው። 15 ሚሊዮን አማራ የሚኖርበት ኦሮሚያ ውስጥ በማንነት ሲያጠቃ የኖሮ ኃይል ቦታ ጠቅሶ የእኔ ነው የሚለው ተመክሮበት፣ ለአማራ አጀንዳ ለመስጠት ብቻ ሳይሆን ለኦሮሞ ሕዝብ ተስፋ ሰጥቶ ለመመረጥ ነው። የአማራ ርስት ጠቅሰህ ልትመረጥ ቀርቶ ኦሮሚያ ውስጥ ሰርተህ የሚሰማህ የለም!
የአማራ ብሔርተኝነት ያነሳው የአማራ ርስት ጥያቄ የአማራ ብልፅግና ሲይዘው እውቅና የሰጠው የአማራ ርስት ስለሆነ ነው፣ የኦሮሞ ብልፅግና ኦነግ ያነሳውን የሌላ ሁሉ አንስቸ ተቀባይነት አገኛለሁ ብሎ ከተጃጃለ፣ ነገ ደግሞ ኦነግ ይዞት የኖረውን የመገንጠል ጥያቄም አያመጣም አይባልም። በጠላው የኦሮሞ ሕዝብ ዘንድ ተቀባይነት አገኛለሁ ብሎ ኢትዮጵያ ሱሴ ካለበት፣ ኢትዮጵያ ትበተን ወደሚል ወራዳ የኦነግ ጥያቄ አይሄድም አይባልም። ኦነግን እየተከተለ በሕዝብ ተቀባይነት አገኛለሁ ብሎ ከነጎደ ከአሁኑ መዳረሻውን መገመት እንችላለን።
ኦህዴድ የኦነግን ትርክት ተቀብሎ በሚሊዮን ብር በሀሰት ትርክ፣ በአንድ ልብ ወለድ ላይ የተጠቀሰውን የጡት ሀውልት አሰርቶ፣ ወጣቱን በአማራ ጥላቻ አስተምሮ የተረፈው ከተማ የሚያወድም፣ ዜጎችን አርዶ ከጎናቸው ጫት የሚቅም አረመኔ ትውልድ ነው። አሁንም የኦነግን ዱካ እየተከተሉ የሕዝብን ድጋፍ ለማግኘት የሚለፉ ደንባራዎች የሚገቡበትን ጭቃ መጀመርያ ራሳቸው የማይወጡበት ነው!
የኦሮሞ ብልፅግና ኦነግነትን ለምርጫ ፈልጎታል!
የኦሮሞ ብልፅግና የኦሮሞን ብሔርተኝነት መረከብ ፈልጓል። ለዚህ ደግሞ በዋነኛነት ያሰለፈው እነ ታዬ ደንድኣን ነው። ሆን ብለው ፅንፍ እንዲይዙ ይደረጋል። ሌላው ቀርቶ የአማራ ብልፅግና ጋር የተጣሉ ከመሰሉ ወይንም ከወረፉ ሕዝብ ይቀበለናል ብለው ያምናሉ። በውጭ ያሉት ብሔርተኞች ከኩርፊያ ይመለሳሉ ብለው ያምናሉ። ከግምገማቸው “ነፍጠኛ እያሰኘን ያለው የአማራ ብልፅግና ነው።” ብለዋል። ባይጠሉትም የተጣሉት መስለው መቅረብ ይፈልጋሉ። ስለሆነም የርስት ጥያቄ ያነሳለሁ። የኦነግን ጥያቄ የሚያስጥልላቸው ከመሰላቸው ማርስንም ብዙ aaaa ደርስረው በኦሮምኛ ፅፈው የኦሮሞ ግዛት ነው ሊሉ ይችላሉ።
አንዳንዱ አጀንዳቸው ለአማራ ብልፅግና አማራሮችም ቢሆን ግልፅ ላይሆን ይችላል። የአማራ ብልፅግና አመራሮች በከፍተኛ አመራሩ ስልጠና “ታዬ ደንድኣ እንዲህ እያለ ነው” ብለው አቤቱታ ቢያቀርቡ በጠቅላይ ሚኒስትሩ ደረጃ ሳይቀር “ከእናንተም እንትና እንዲህ ይላል፣ እንትና እንዲህ ይፅፋል፣ የሁሉም ስህተት ነው።” ተብሎ በማመቻመች ይታለፋል።
የኦዴፓ ዋናዎቹ ሰዎች ለአዴፓ ሰዎች ሆን ብለው ታየን ያሙላቸዋል። “አስቸገረን፣ የእነ ታከለ እጣ ይደርሰዋል፣ ኦነግ ነው፣ ቆይ ይጠብቅ” ብለው ሊቀልዱባቸው ይችላሉ። አሊያም በስብሰባ ሙልጭ አድርገው ሊገመግሙት፣ ሊወቅሱት ይችላሉ። የሚስማሙት ግን ታዬ ይሄን ኃላፊነት ሊወስድ ነው። እየተነሳው ያለው በሙሉ እንደማይሆን ያውቁታል። የምርጫ ቅስቀሳ ስለጀመሩ ነው። አሁን ኦነግ በተኛበት ላዩ ላይ ሆነው ለኦሮሞ ሕዝብ አለን ለማለት ነው። የሚያዋጣቸው ከሆነ የኦነግን ባንዲራ ይዘው ምናምን ፎቶ አስለቅቀው፣ እኛ እነዚህ ኦነጎች እንድንላቸው ይፈልጋሉ። እነሱ የሚከስሩ የሚመስላቸው ከኦነግ በሀሳብ ተቃረኑ ቢባል ነው። የኦነግነት ፍረጃውን በእጅጉ ፈልገውታል። ሊመረጡበት ነው!
አይተቹ ማለቴ አይደለም። ተገቢው መልስ ይሰጣቸው። በሚጠቅማቸው መልኩ ግን አንሂድላቸው። ስልጣን ላይ ሆነው እንዴት ስልጣንን መበሻቀጫ እንዳደረጉት ነው ማሳየት የሚገባው።
ማመን ያለብን በአሁኑ የኢትዮጵያ ፖለቲካ ሰነድ በማዘጋጀት፣ የይሁናል ትንተና በመስራት፣ ሴራ በመጎንጎን፣ የሀሰት አጀንዳ በመስጠት፣ የኦሮሞ ብልፅግናን ያህል ማንም የለም። ስለሆነም ከዛ ሰፈር የሚመጣውን የትኛውንም አጀንዳ እንደመጣ አንቀበለውም። ለምርጫ ቅስቀሳ አብረናቸው አንሰለፍም!
ተገቢ መልስ ይሰጣቸው!
በመንግስት ስልጣን ቁጭ ብለው ኃላፊነት መወጣት አለመቻላቸው ይነገራቸው!
ኦሮሚያና አዲስ አበባ ያለው ይነገራቸው!
ይቀለድባቸው!