>

ነጻ ህጋዊ ምርጫ ከተካሄደ እኮ አቶ እስክንድር ቦታቸው ቃሊቲ አይደለም ምኒልክ ቤተ መንግስት ነው....!!! (የህግ ባለሙያ ሄኖክ አክሊሉ)

ነጻ ህጋዊ ምርጫ ከተካሄደ እኮ አቶ እስክንድር ቦታቸው ቃሊቲ አይደለም ምኒልክ ቤተ መንግስት ነው….!!!
የህግ ባለሙያ ሄኖክ አክሊሉ

 

* የእነ እስክንድር ገዳይ ለፍትህ ስርአቱ ጥቁር ጠባሳ ነው….!!!

* ፈጣሪን ስትፈራ ህግ ስታከብር ሹመኛ ይዳፈርሀል!
* አቶ እስክንድር ከወተት የነጻ እውነት አላቸው!
 
አቶ እስክንድር ነጋ ትናንት በ1997 ከሁለት አመት በላይ ታስረው ሌሎች የሰላማዊ ትግል አማራጭ አበቃ ብለው ወደ ትግል ሜዳ በሄዱ ጊዜ እርሳቸው ግን የሰላማዊ ትግል አማራጭን ተከትለው በመጓዛቸው አለም አቀፉ ማህበረሰብ ጭምር ለሰላማዊ ታጋይነታቸው ያለውን ክብርና አድናቆት ለመግለጽ  በርካታ ሽልማት የሰጣቸው ሰው ናቸው።
ዛሬ ምን አገኘሁ ብለው ነፍጥ ያነሳሉ? የኢትዮጵያ ህዝብ እኮ ይመርጣቸዋል፤ ለምን ብለው ህዝብን ከህዝብ አጋጭተው ሀገሪቷን ወደ ምስቅልቅል ውስጥ ያስገባሉ??
ነጻ ህጋዊ ምርጫ ከተካሄደ እኮ አቶ እስክንድር ቦታቸው ቃሊቲ አይደለም ምኒልክ ቤተ መንግስት ነው….
Filed in: Amharic