ክቡር ኮሚሽነሩ ‹‹መንግሥት ያለ አይመስልም ነበር!›› የሚል ሪፖርት ቢያቀርቡም፣ እኔ ግን ‹‹አለን!›› እላለሁ…?!?
አሳዬ ድርቤ
ንጹሐንን የሚያስገድል! ኢንዱስትሪ የሚያወድም!
መንግሥትማ በጣም አለ፣ በአደባባይ የሚፎክር
በመንገድ ፈንታ መቃብር- በስካቫተር የሚያስቆፈር
ከፋፍሎ ያስገደለውን- አስተቃቅፎ የሚቀብር
የሠራው ወንጀል ሲጋለጥ- ቋንጣ ዜና የሚሰብር❗️
ኢትዮጵያማ መንግሥትማ አላት-
አገር አፍራሽ፣ ደም አፋሳሽ
ሤራ ጎንጉኖ ሲያበቃ- ፕሌን ተሳፍሮ የሚሸሽ፤
መንግሥትማ በጣም አለን- ያውም ባለ ብዙ ሃይል
ከሜንጫ ያመለጠን ሕዝብ- በጥይት ደረቱን የሚል
ነፍጠኛ የሚባል ሟች- ኦነግ ሸኔ ይሉት አራጅ
በአሳቡ ፈጥሮ ሲጨርስ- አማራን በጅምላ የሚፈጅ
በገሃድ ለቀጠፈው ነፍስ- ስውር ጦሩን የሚፈርጅ፡፡
መንግሥትማ በጣም አለን- የመኖር መብት ገፋፊ
ዛፍን ከምሣር ታድጎ- ሕፃን እና አራስ ጨፍጫፊ፡፡
መንግሥትማ በጣም አለን
አገር እንጂ የቸገረን…❗️