የውሸት ንጉሶች…!!!
አንዳንድ ጊዜ ብቻዬን ሆኜ ጠ/ሚ አብይን አስባለሁ። የትኛው ነው ስል እጠይቃለሁ?።በተስፋ የተሞላው መጀመሪያ ጊዜ በፖለቲካውን ወድፊት መጥተው በተቆጣጠሩ ጊዜ ያይኋቸው መሪ ወይስ ላለፍት ሁለት አመታት የመራንን መሪ።
ጠቅላይ ሚንስትር አብይ አሁንም አልገቡኝም እኝህ ሰው እስኪገቡኝ ሀሳቤን የመግለጽ እግዚያብሄር የሰጠኝን መብቴን ተጠቅሜ እጽፋለሁ።
የአሜርካው የቀድሞ ፕሬዝዳን ዶናል ጄ. ትራምፕ በመዋሸት፣ያልተረጋገጡ ወሬዎችን በማሰራጨት፣ አስቀድመው የተናገሩትን በካድ በአሜርካ ረፓብሊክ ታሪክ የመጀመሪያው ፕሪዝዳንት ሆነዋል።ምናልባት በወርልድ ጊንየስ ቡክ ሊመዘገቡ ይችል ይሆናል።አንዳንድ የስነልቦና ጠበብት (pathological liar) ይሏቸዋል ።ራሱን የቻለ በሽታ ነው።የውሽት በሽታ።
ዶናልድ ትራምፕ ዋይት ሀውስ ገብተው ሊወጡ ሁለት ሳምንታት እስኪቀራቸው ማለትም ጀነዋሪ 6 /2021 [ትዊተር በቋሚነት እስከሰረዛቸው] ድረስ 30,373 የተረጋገጡ ወሸቶችን ዋሽተዋል።በአቬሪጅ ከተወሰደ በቀን 20.9 ውሽቶችን አሰራጭ ተዋል ማለት ነው።
የውሽቶቻቸው ተቀባዮች ደግሞ 70% የኢቫንጀሊካን እምነት ተከታዮችና ፕሮቴስታንቶች ናቸው።እነዚህ የእግዚያብሄርን መብት እናስከብራለን የሚሉ የፕሮቴስታንት አማኞች ከዶናልድ ትራምፕ ጋር የትራራው ጫፍ ገደል ድርስ የሚሄድ ፍቅር የያዛቸው ናቸው።ዶናልድ ትራምፕ የሃይማኖት ሰው አይደሉም።
በክርስትና ሚዛን ላይ ከተቀመጡም በሁሉም መለኪያ የሚወድቁ ናቸው። ሶዋስት ጊዜ አግብቶ የፈታ፣አመንዝራ፣ወለድ የሚቅበል፣ታክስ የማይከፍል፣አታላይ፣ ውሸታም ፣ዘረኛ፣ታናናሾችን የሚንቅ ፣ድሀ የሚጠየፍ፣አምባ ገነን እና ግብዝ ነው። እነዚህ ጠባዮች ታዲያ በየትኛውም ሀይማኖት የተውደዱ አይደሉም። በክርስትና ሀይማኖት በየትኛውም ይሁን… የአስርቱ ትእዛዛት ላይ የተቀመጠውን የእግዚያብሄርን የቃልኪዳን ህግ ትእዛዝ የሚጥስ ከመሆኑም ባሻገር በመጽሀፍ ቅዱስ ላይ የተቀመጡትንም የሞራል ሕጎችም የሚጥስ ነው።
ክርስትያን ምእመናን ፕሮቴስታንቶች ብቻ ሳይሆኑ የዶናልድ ትራም አክራሪ ተከታዮች መሪዎቹም ጭምር ናቸው። ማለትም መጋቢዎቹ፣ፓስተሮቹ፣ነብዮቹ ፣ሁዋርያዎቹ፣ ቄሶች ዋናዎቹ ናቸው። ዶናልድ ትራምፕ “ዋሽ” ብለው አውግዘው አያውቁም እንዳውም ውሽቱን በትንቢት መልክ የተናገሩ ሀዋርያ አሉ።የሚችጋኑ ሳውዘርን ባፕቲስት ቸርች ሀላፊ ፓስተር ጆናታን ትሮውን የተባሉ ቄስ ” እግዚያቤሄር ተናገረኝ፥ምርጫውን ዶናልድ ትራምፕ አሽንፎል ” ብሎ አውጆል። በዚያን ሰት ታዲያ ዶናልድ ትራምፕ 42 ጊዜ በፍርድ ቤት ተሸንፈሀል የተባሉበት ወቅት ነበር።
የአሜርካኖች የተስፋዋ ምድር የት እንደሆነች ባይታወቅም< ልክ እንድ ሙሴ የተስፋዋ ምድር ወደ ከነን የሚያደሰን ዶናልድ ትራምፕ ነው እያሉ እስከ ጄነውሪ 6/2021 አ.ም ድረስ በዋይት ሀውስ እየተሰበሰቡ ሌሊት እና ቀን የጸሎት ፕሮግራም ያደርጉ ነበረ።እንዲያውም የዳላስ ኢቫጀካል ፓስተር የሆኑት ሮበርት ጀፈሪ የምርጫውን ውጤት እግዚያብሄር የአሁኑን ፕሬዝዳንት ጆ ባይደንን አልተቅበለውም የትራሞፕ መንግስት እንደሚቀጥል ” ተናገረኝ>በሚል ኢቫንጀሊስቶች አሳምነዋል።ጸሎት ፕሮግራም ሲከናውኑ ሰንብተዋል።
እንግዲህ ይህ ሁሉ የመጽሀፍ ቅዱስ አስተምህሮት በቅጡ አላቸው የሚባሉ ፕሮቴስታንቶች ምንነትን ምን ያህል ውድቀት ላይ መሆኑን ፍንትው አርጎ የሚያሳይ ነው። እውነት የለም፥ሕግ የለም፥ ሞራል የለም፥ ከሁሉ በላይ እምነት የለም ።ያለው ምንድነው ቤተክርስቲያን ብቻ ነው። እነዚህ ደግም ተፅፎል “ምድራዊ ድንኳኖች ናቸው” ተብሎ።በዘመናችን ሀይማኖት ምን የህል በፖለቲካና በዘር የተበከለ እንደሆነ ያሳያል።
መጽሀፉ ከሀጢያት አትተባበሩ ይላል።መተባበር ይቅርና ያሰበ እንዳደረገ ይቆጠራል ይላል።ያመነዘረ ብቻ ሳሆን ለማመንዘር ያሰበ እንዳደረገ ይቆጠራል ይላል።አሁን እያለን የለው ክርስትና ግን የኛ ወገን ከሆነ፣የኛ ደጋፊ ከሆነ፣ የኛ ፍላጎት አስፈጻሚ ከሆነ፣ <ከእግዚያብሄር ትእዛዛት ፈቅ ቢልም፣ጸረ እግዚያብሄር አካሄድቢኖረውም>ተክክልነው።እንከተለዋለን።
ይህ ማለት የሰይጣን መንፈስ የእግዚያብሄርን ቅጥር ዘልቆ ተቆጣትሮታል ማለት ነው። አሁን በተግባር ሰይጣን ያለው ማን ጋር እንደሆነ ስራቸው እየመሰከረ ነው ማለት ነው። እንሆ እምነት ከስራ ውጭ ሙት ነው ይላል ጢሞትዎስ። ሀማኖት እንጂ እምነት የለም ።ቤተክርስቲያን እንጂ ስራ የለም።
ወደኛ ጠ/ሚ አብይ አህመድ አሊ እንመለስ፣ ሕብረ ሀይማኖት ያስተናገዱ ቢሆንም በመጨርሻ የፖቴስታንት እምነት ተከታይ ናቸው፣እንደ ዶናልድ ትራምፕ የደርጉት ክህደት እና የዋሹት በመመዝገቢያ ቋት [ዳታ] ስለ ሌለ ምን ያህል ጊዜ በዚህ ሁለት አመት እንደዋሹ በቁጥር ማስቀመጥ ይክበድ እንጂ እስከዛሬ ከገጠሙን መሪዎች በውሽት ቁጥር አንድ ሳይሆኑ አይቀርም።
በልጅነቴ ስላክ የማንንም መኪና አስነስቼ እሄድ ነበረ፣እናቴ ሲባተኛ ንጉስ ትሆናለህ ብላኝ ነበረ፣ሩዋንዳ ወታደር ሆኜ ዘምቼ አንድ ፈረንሳዊ ካላገብሁ ሞቼ እገኛለሁ ብላኝ ነበረ ፣ወደ መካከለኛ ምስራቅ ፊትህን አዙር ብሎኝ[በራእይ ሊሆን ይችላል አላብራሩም} ሄድኩና ኢትዮጵያን የሚታደግ ገንዘብ ይዤ መጣሁ ፣ዘረኛ አይደለሁም ይሉና ብልጽግና የኦሮሞ ነው፥ ህገ መንግስቱም ይቀጥላል።የኦሮሞ የበላይነት የለም 78% ስልጣን የፌድራሉ በኦሮሞ ተይዞአል፣ለትግራይ ማስክ እንጂ በኮሮና ዘመን ቦንብ አንልክም የመኽር እህሉን እንኳ ሳይሰበስብ በቦንብ አጋዩት፥ ጦርነቱን የጀመረው ወያኔ ነው ይሉና ከኢሳያስ ጋር አልዶለትንም፣እኔ በሄድኩበት ዝናብ ይጥላል፣ በትግራይ ጦርነት አንድም ሲቪል አልሞተም ፣ኢኮኖሚው ዜሮ በገበበት ባሁኑ ወቅት 6% አድገናል 30 አመት በኋላ ከአለም አንደኛ በኢኮኖሚ፣ሱዳንን ድንበር ጠብቂ እንጂ መሬት ውሰጂ አላልንም፣የኤርትራ ወታደሮች ትግራይ ጦርንርት ላይ አልተሳተፉም እናም የሉም፥ሰችዌሽን ሩም ፣300 ንፁሀን ታርደው ግጭት ነው።ሰላም ሰፍኗል
አሜሪካ የህዳሴ ግድብ ታዛቢ እንጂ አደራዳሪ አይደለችም ፣የ አውሮፓ መሪዎች የሚደውሉልኝ እኔ የጀመርኩትን ሪፎርም እንደሚደግፉ ለማስወቅ ነው ብልፅግና የተባለ ከዘር ፓለቲካ የጸዳ ፖለቲካ ፓርቲ የመሰረትኩ ብቸኛ መሪ ነኝ ,,,,,,,,ወ.ዘ፣ተ
ቁጥር ስፍር የሌላቸው ውሽቶች እየዋሹን ነው።ተከታዮቻቸው ደግሞ እንደ ዶናልድ ትራምፕ ሁሉ አብዛኛው ፕሮቴስታንት ናቸው።በቤተመንግስት እነ ፕስተር ዮንታን ቢያንስ በሳምንት ሁለት ጊዜ የጸሎት ፕሮግራም አላቸው ይባላል። እግዚያቤር ተናገረኝ< “አትዋሽ”ቢሉት ምናለ ጠቅላያችንን! አንደበታቸውንም እንዲቆጣጠር ለመንፈስ ቅዱስ ማመልከቻ ቢገባ….ሌላው ግምት ደግም ፕሮቴስታንቶች ቀና ማሰብ አስተምህሮ(positive thinking ) ምናልባት ቃል መጣልን ” ተናገረን እያላችሁ “ከባችሁ መሪያችንን እያስቃዣችሁት ያላችሁ እናንተ ትሆኑ እንደ ሆነ…ደግ እየሰራችሁ አይደለምና መሪያችንን መልሱልን። ጠቅላላ መሪያችን እኮ ሌላ ፕላኔት ላይ ነው የሚኖሩ የሚመስሉት።
አዎ <ምላስ የራሷን ፍሬ ትበላለች ተብሎ ተጽፎልና> ለሚደርሰው ያልተሳካ ውጤት ሁሉ መንፈሳዊ አስተሳሰብ በመያዝ ማስቀልበስ ተብሎ ከሆነ ፖለቲካ ላይ ይሰራም።ይህ ቢሆን ኖሮ የሮማው ፖፖስና የኮንስጠጠንያ ቆፖሳት እስካሁን ምድርን በገዙ ነበረ። ይሄ አስተሳሰብ እንኳን ለኢትዮጵያ ለቫቲካንም አይሰራ።የቄሳርን ለቂሳር የእግዚብሄርንም ለእግዚያብሄር።
የምያሳዝነው አብዛኛው የአብይ ተከታዮች እንደ ዶናልድ ትራም ተከታዮች ሁሉ እውነውትን ከመቀበል ይልቅ የአብይ ሲተች ወይም ሂስ ሲደረግ ጠላቶች የሚያስወሩት ነው። የወያኔ ደጋፊዎች ወይም ስልጣን ናፋቂ ተቃዋሚዎች እያሴሩበት ነው ብለው ሰበብ መስጠት ነው የሚቀልላቸው። እነዚህ ተቃዋሚዎች እኮ የዛሬ ሁለት አመት እልል ብለው የተቀበሏቸው መሪ እንደነበሩ የአብይ ደጋፊዎች የዘነጉት ይመስላል።
መሪያችን በውሽቱ ቀጥሏል፣አገራችንም እየውደመች ነው፣ጠላቶቻችንም በዝተዋል ፣ መሪያችን¸ ከስተታቸው የሚማሩ አይነስሉም። እእእእእእእእኛም ውሽትን እይተለማመድን ወደፊት ቀጥለናል።
እንኪያስ እኛም አጣቀሰን እንለያይ
ዘሑልቁ ም፥25 እግዚአብሄር ፊቱን ያብራልህ ይራራልህም ተብሎ ተፅፎልና።ለመሪያችንም ለኛም እንለምናለን።
“ሀለ ሉ ያ አሜን! “