>
6:42 pm - Wednesday June 7, 2023

የኦነግ/ኦህዴድን ጫማ ሲጠርጉ እየዋሉ "ብሄረተኝነትን እንደመሥሠዋለን!" ለሚሉ "ብልጣብልጥ" የአማራ ፖለቲከኞች....!!! ( ሸንቁጥ አየለ)

የኦነግ/ኦህዴድን ጫማ ሲጠርጉ እየዋሉ “ብሄረተኝነትን እንደመሥሠዋለን!” ለሚሉ “ብልጣብልጥ” የአማራ ፖለቲከኞች….!!!
ሸንቁጥ አየለ

የኦህዴድ/ኦነግን ጫማ ከአንዳርጋቸዉ ጋር ቁጭ ብሎ ሲጠርግ እየዋለ የዜግነት ፖለቲካ አራማጅ ነኝ የሚልህ ብልታብልጥ የአማራ ፖለቲከኛ ነፍ ነዉ::  እና ኦነግ/ኦህዴድን እየካደምክ እንዴት አድርገህ ነዉ ብሄረተኝነትን የምታጠፋዉ ስትለዉ መልስ የለዉም::ወይም የሆነ የተንሸዋረር ተጠይቅ ይዞልህ ይመጣል::
ከነዚህ ብልጣብልት የአማራ ፖለቲከኞች ጋር መከራከር ስትጀምር በሶስት ደቂቃ ማንነታቸዉን ትረዳዋለህ:: ብልጣልጥ የአማራ ምሁራን ትልቁ የሞኝነት ብልጠታቸዉ ምን መሰልህ ኦህዴድ/ኦነግን በማስደሰት ስየስልጣን ፍርፋሪ የሚያገኙ ይመስላቸዋል::እዉነታዉ ግን ኦነግ/ኦህዴድ አንፈርፍሮ ይበላቸዋል::ለራሳቸዉም ለወጡበትም የአማራ ማህበረሰብ ክብር ስለሌላቸዉ በሚሊዮን የሚቆጠር አማራ በአንድ ቀን ቢፈናቀል: ቢታረድ:ቢገደል ከቶም አይቆጡም::ባላዬሁም ያልፉታል::ብልጥ መሆናቸዉ እኮ ነዉ::ይባስ ብለዉም ይሄን በአማራ ላይ የሚደረገዉን የዘር ፍጅት የሚቃወምን ሰዉ ዘረኛ ሲሉ ያሳጡታል::ብርሃኑ ነጋ እንዲህ ሲያደርግ ብታገኘዉ ላይገርምህ ይችላል::
ኦህዴድ/ኦነግ የሆኖ ፖለቲከኞች መቼም ብሄረተኝነትን እናወድመዋለን አይሉም::እነሱ እንዲያዉም ገና ብሄረተኝነታችንን ለሶስት ሽህ አመታት እናስቀጥላለን እያሉ ነዉና::ኢትዮጵያን ለሶስት ሽህ ዘመን ብቻችንን እነገዛለን::ሌላዉን ገፍተንም ጨፍጭፈንም መሬቱን ሁሉ አዲስ አበባንም ኦሮሚያንም ቤኒሻንጉልንም በደቡብም እኛ ብቻ እንቆጣጠረዋለን የሚል ቅዠት ዉስጥ ያሉ ናቸዉ::በብዙ ሽህ ህዝብ ጨፍጭፈዉ ሰዉ በግሬደር እንደ ቆሻሻ ቀብረዉ አንድኛቸዉም የኦህዴድ/ኦነግ ፖለቲከኞች ወጥተዉ የሀዘን ስሜታቸዉን ለመቶ ሚሊዮን ህዝብ የማይገልጹ ናቸዉ::በነሱ ጭንቅላት የተጨፈጨፈዉ አማራ እንጂ ሰዉ አይደለም::ከእነሱ ነገድ ሰዉ የተፈናቀለ እንደሆነ አንድ ሚሊዮን ሰዉ ከሶማሌ ክልል አምጥተዉ ቤት ሰርተዉ አዲስ አበባ ላይ ያሰፍራሉ::
ብልጣብልጡ የአማራ ፖለቲከኛ ይሄ አያስቆጣዉም::አያናድደዉም::የ እኩልነት ጥያቄ የለዉም::ብልታብልጡ የአማራ ፖለቲከኛ ለማስመሰል ኢትዮጵያ እንዳትፈርስ ይልሃል:: ኢትዮጵያ ለሱ ምን ማለት እንደሆነች ብትጠይቀዉ ግን መልስ የለዉም::ያዉ የብልጣብልጥ መልሱን ይሰጥሃል::
ኦነጋዉያን/ኦህዴዳዉያን በአማራ ፖለቲከኞች ላይ ሁል ጊዜ የሚበሳጩት “የአማራ ፖለቲከኞች ብልጣብልጥነት ያበዛሉ” እያሉ ነዉ:: ሁለት ሞኝ አብሮ ይጓተታል እንጂ ኦነጋዉያን/ኦህዴዳዉያን ላሰቡት የሶስት ሽህ ዘመን ብሄረተኝነታቸዉ ማስቀጠያ እንደ ብልጣብልጥ የአማራ ፖለቲከኞች መልካም ፈረስ ፈጽሞም አያገኙም ነበር::
ኦነጋዉያን/ኦህዴዳዉያን የማያዉቁት ግን የእዉነተኞቹን የኢትዮጵያዉያንን የፖለቲካ ፍልስፍናን ነዉ::እዚህ እዉነተኞቹ ኢትዮጵያዉያን ፖለቲከች የፖለቲካ ፍልስፍና ፊት ኦነጋዉያንም/ኦህዴዳዉያን ጨርሶ አይቆሙም::ዉላፈኑ እንኳን ያቃጥላቸዋል::እንኳን ሀሳቡ ተገልጦ:: ብልጣብልጦቹ የአማራ ፖለቲከኞች ግን እንደ ኦነጋዉያን/ኦህዴዳዉያን አይደሉም::ሌላ ሀይል ቢመጣ መገልበጥ ይችላሉ::የአዞ እንባ እያነቡ ኢትዮጵያ እያሉ ይገለበጡልሃ::እዉነታቸዉ ግን አይደለም::ከሃዲ ናቸዉ::ከብልጣብልጥ የአማራ ፖለቲከኛ ኦነጋዊ/ኦህዴዳዊ መልካም እና ጥሩ ጠላት ነዉ::
ኦነጋዉያንን/ኦህዴዳዉያንን/ህዉሃታዉያንን/ኢህአዴጋዉያንን/ደህዴናዉያንን/ብልጽግናዉያንን/ብአዴናዉያንን ኢትዮጵያዊነት የሚለዉ ትርጉም ስለማይመጥናቸዉ የእዉነተኞቹ የኢትዮጵያዉያን የፖለቲካ ፍልስፍና የሚለዉ ዉስጥ እንደማይካተቱ ግን በደንብ ይሰመርበት::ኢትዮጵያ በቅኝ ግዛት ተፈጠረች የሚል እሱ የሚርመጠመጠዉ የባርነት የፖለቲካ ህሳቤ ዉስጥ ነዉና ኢትዮጵያዊነት ይመጥነዉም::
እናም ብልጣብልጥ የሆኑ የሚመስላቸዉ የአማራ ፖለቲከኞች በኢዜማ ዉስጥ እና በብልጽግና ዉስጥ ተወሽቀዉ የኦነግ/ኦህዴድን ጫማ ሲጠርጉ እየዋሉ በብዙ ሚሊዮን የአማራ ህዝብ ሲጨፈጨፍ ባላዬንም እያለፉ ሳያፍሩ “ዘረኝነትን ከኢትዮጵያ እናጠፋዋለን” ይሉሃል::ብልጥ መሆናቸዉ እኮ ነዉ::ከብ አዴን ካድሬ እስከ ዳንኤል ክብረት : ከዳንኤል ክብረት እስከ ዶ/ር አንዳርጋቸዉ እስከ ክቡር ገና ኢዜማ በብዛት እስከ ተሰገሰጉት በርካታ ብልታብልጥ የአማራ ፖለቲከጮች ያሉትን ያካትታል::
በነገራችን ላይ ብልጣብልጥ የሚለዉን ስም እኔ አልለጠፍኩላቸዉም::ጫማቸዉን ሲተርጉላቸዉ የሚዉሉት ኦነጋዉያን/ኦህዴዳዉያን ናቸዉ የለጠፉላቸዉ::
Filed in: Amharic