ቻይና፤ ሩስያ እና ህንድ ትግራይ ላይ የተያዘውን የመገንጠል አጀንዳ ውድቅ አድርገዋል…!!!
ደሳለኝ ሀገረሰላም
* በተባበሩት መንግሥታት የጸጥታው ም/ቤት ቋሚ አባላትና ድምጽን በድምጽ የመሻር መብት ያላቸው ቻይና እና ሩስያ እንዲሁም ተለዋጭ አባል የሆነችው ህንድ ኢትዮጵያ የራሷን የውስጥ ችግር በራሷ አቅም መፍታት የምትችል ሀገር ነች ጣልቃ መግባት አላስፈላጊ ነው በማለት የትግራይ ጉዳይ ላይ የተያዘውን የመገንጠል አጀንዳ ተቃውመዋል፡፡
* የሰብአዊ መብት ተሟሟጋች ነኝ ባዩዋ የቴዎድሮስ አድሃኖም ወዳጅ በአሜሪካና እንግሊዝ ታጅባና አጥንታ ያቀረበችውን ውንጀላ የፀጥታው ምክር ቤት ከማሕበራዊ ሚዲያ የተለቃቀመ እንጂ ተጨባጫነት አላገኘሁበትም ብሎ ወደ ቅርጫት ወርውሮታል ።
ኢትዮጵያ አምላኳ እኮ ሀያል ነው፤ የተባበሩት መንግስታት በኢትዮጵያ ላይ ለሴራ መተባበር መተባበር አልቻሉም..።
በትግራይ ጉዳይ ላይ ለመምከር የተሰበሰበው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የጸጥታው ምክር ቤት ያለ ስምምነት ተበትኗል
በመሆኑም ሩሲያ፣ህንድና ቻይና የትግራይ ጉዳይ የኢትዮጵያ የውስጥ ጉዳይ ነው ስላሉ ያለምንም ውሳኔ የተባበሩት የፀጥታው ምክር ቤት ስብሰባ ብትንትኑ ወጥቷል፤
ከእውነት ጋር ስለቆማችሁ እናመሠግናለን ሩሲያ ! ፣ እናመሰግናለን ቻይና ! ፣ እናመሰግናለን ሕንድ ! ፣ እናመሰግናለን ሚስተር ባኮክ !
በተጨማሪም ሸረኛዋ አሜሪካ የኒውዝላንድን ከባድ ርዕደ መሬት ተከትሎ በሱናሜ ማዕበል ቁራኛ ስር ወድቃለች፤ ኢትዮጵያን የነካ፥የለውም በረካ…ይሉታል እንዲህ ነው