>
5:21 pm - Sunday July 21, 3326

የስልቀጣ ፖለቲካ...!!! (አቻምየለህ ታምሩ)

የስልቀጣ ፖለቲካ…!!!

አቻምየለህ ታምሩ

* የኦሮሙማ አፓርታይድ አገዛዝ ያለረፍት ኢትዮጵያን በመሰልቀጥ ላይ መጠመዱ ሕወሓትና  ሸሪኮቹ በአገራችን ላይ እንዲዘምቱ እድል  ፈጥሮላቸዋል! 
በመንግሥትነት የተሰየመው የዐቢይ አሕመድ የኦሮሙማ አፓርታይድ አገዛዝ ያለ እረፍት ኢትዮጵያን በመሰልቀጥ ላይ ስለተጠመደ እና ለኢትዮጵያ የሚሆን ጊዜ ስለሌለው አገራችን ያላት ተራራ የሚያህል እውነት ፋሽስት ወያኔ በየቀኑ ከትግራይ በርሀ በሚያመርተው የውሸት ክምር እየተሸነፈ ይገኛል። በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር ያለው አገር ወዳድ ኢትዮጵያዊ  የኢትዮጵያ ካንሰር የሆነውን ሕወሓት የሚባለውን የወንጀል ኢንተርፕራይዝ ለማስወገድ የሚችለውን ጠጠር ሲወረውር ሲውል በመንግሥትነት የተሰየመው አገዛዝ ግን የሙሉ ጊዜ ስራውን ኢትዮጵያን ኦሮማይ ስላደረገ የተቆጣጠረውን የመንግሥት መዋቅር  አንድ ቀንም እንኳን በስህተት ኢትዮጵያን ከሕወሓት አለማቀፋዊ ጥቃት ለመከላከል አውሎት አያውቅም።
በፋሽስት ወረራ ዘመን መላው አውሮፓ ጣሊያንን ሲያባብልና የፋሽስትን ፕሮፓጋንዳ በኢትዮጵያ ላይ ሲያስተጋባ በነበረበት ወቅት በተከራዩት የግለሰብ ቤት ውስጥ የስደት መንግሥት መስርተው ያንን ሁሉ ፕሮፓጋንዳ በመመከት የኢትዮጵያ እውነት እንዲያሸነፍ ያደረጉ ታላላቅ ዲፕሎማቶች እንዳልነበሩን ዛሬ በብሔራዊ ቤተ መንግሥት ውስጥ  በመንግሥትነት የተሰየሙት አካላት ኢትዮጵያን ለመዋጥ ካልሆነ በስተቀር አገርን ከውስጥና ከውጭ ጠላቶች ለመከላከል ጊዜ ስለሌላቸው በቢሊዮን ዶላር የውጭ ርዳታና ብድር እየጎረፈላቸው እና ከሌላው ዓለም ሊያገኙ  የሚችሉትን ‹ሥልጣኔ› ሁሉ እያገኙ በጨለማ ዘመን የኖሩት አባቶቻችን ከግራ ከቀኝ የሚመጣባቸውን ጠላት በትከሻ፣ ባሕያና በበቅሎ የተያዘ በሶ፣ ቆሎና ጥሬ እየበሉ፤ በወጣ ገባና አስቸጋሪው የሀገራችን መልክአ ምድር እየተንገላቱ ሲያስከብሩ የኖሩት ብሔራዊ ክብርና ሉዓላዊነት ጫካ ካሉት የፋሽስት ቅሪቶች የፕሮፓጋንዳ ጥቃትና የጎረቤት ጠላቶች ወረራ ለመከላከል ፍላጎቱ እንኳን የላቸውም።
ከሁለት ሺህ በላይ ንጹሐን የአማራ ተወላጆች በአንድ ቀን የተፈጁበት የማይካድራው ጭፍጨፋ፤ ባለፉት 27 ዓመታት ሕወሓት በወልቃይት፣ በጠገዴ፣ በሁመራና በጠለምት ያሰፈራቸው “ታጋዮች” በየአማራ ተወላጁ ቤት እየሄዱ አባወራውን አባርረው ሚስቱን አስገድደው ሲደፍሩ፤ እያንዳንዱ የሕወሓት ታጋይ እስከ አስር የሚደርሱ የአማራ ሴቶችንና ሕጻናትን አስገድዶ እየደፈረ፣ መሬትና ሀብት ባለበት ደግሞ ባለትዳሮችን በኃይል ከትዳራቸው እንዲፋቱ እያደረገ ወይም አባወራው በማሰርና በመግደል አማወራዋን እየደፈረ ትግሬ ልጅ እንዲወልድና በወረራ በተያዟቸው አካባቢዎች ውስጥ ይኖር የነበረው ነባሩ ሕዝብ እየጠፋ በትግሬ እንዲተካ ሲያደርጉ የኖሩትን ዘግናኝ ወንጀል አለም እንዲያውቀው አልተደረገም።
ሌላው ቀርቶ  አስፓልት ላይ እንዲተኙ ተደርገው ከባድ የጭነት መኪና በላያቸው ላይ የተነዳባቸው የሰሜን ዕዝ ወታደሮች፤ ጡታቸው የተቆረጠ፣ በማሕጸናቸው እንጨት የከተቱባቸውና በባሎቻቸው ፊት ተገደው የተደፈሩ ሴት ወታደሮችና ወታደር ያልሆኑ የወታደር ሚስቶች ታሪክ ለአለም አልተነገረም።  ኢትዮጵያን ኦሮማይ ማድረግን የሙሉ ጊዜ ስራው አድርጎ የያዘው የዐቢይ አሕመድ የአፓርታይድ አገዛዝ ተነግሮ ከማያልቀው የፋሽስት ወያኔ ወንጀሎች መካከል የተወሰኑትን ነቅሶ በአማርኛ በሰራቸው ዶክመንተሪዎች ማቅረቡምንም ለአማራ favor እንደሰራ አድርጎ ነው የሚቆጥረው። ይህ የበጃቸው ፋሽስት ወያኔዎች ትግራይ በረሀ ውስጥ ሆነው በየቀኑ በሚያመርቱት የውሸት ፕሮፓጋንዳቸው የሴኩሪቲ ካውንስል በኢትዮጵያ ላይ እንዲሰበሰብ እስከማድረግ ችለዋል።
ፋሽስት ወያኔ የኔ በሚለው ሕዝብ ላይ ሳይቀር ዘግናኝ ወንጀል እየፈጸመና እንዲፈጸም እያደረገ በሌላ አካል እንደተፈጸመ አድርጎ ፕሮፓጋንዳ መስራት ሲያሸንፍ የኖረ የወንጀል ድርጅት [Criminal Enterprise] ነው። ሐውዜን የተካሄደውን ፍጅት ያቀነባበረው ራሱ እንደሆነ ታጋዮቹ ምስክርነታቸውን ሰጥተዋል። የአይደርን ፍጅት ፋሽስት ወያኔ ራሱ ያቀናበረው ጥቃት እንደሆነ ብዙ ሰው የሚያውቅ አይመስለኝም። ይህን ሁሉ የማድረግ ልምድ ያለው ወንጀለኛ ድርጅት ባለፉት ጥቂት  ወራት ብቻ የኔ በሚለው ሕዝብ ላይ ሳይቀር ተነግሮ የማያልቅ አለማቀፍ ወንጀል ፈጽሟል። ይህንን የሚፈጽመውን አለማቀፍ ወንጀል በሌላ አካል እንደተፈጸመ አድርጎ ፕሮፓጋንዳ ይሰራበታል። ባለፉት ጥቁር ወራት የሚሉ ጊዜ ስራቸው ይህ ነበር። እነሱ ይህን ሲያደርጉ በመንግሥትነት የተሰየመው አገዛዝ  ኢትዮጵያን ለመሰልቀጥ እንጂ ወያኔ የሚያሰራጨውን የውሸት ፕሮፓጋንዳ ለማጋለጥ ጊዜ ስለሌለው አገራችን በሁሉም አቅጣጫ  በየቀኑ አጣብቂኝ ውስጥ እየገባች ትገኛለች።
አገዛዙ ኢትዮጵያን ለመሰልቀጥ የሚያሳየው ትጋት አንድ አስረኛውን  ቀንሶ ሕወሓት ከአዶልፍ ሒትለሩ የናዚ ፓርቲ፣ ከቤንቶ ሙሶሎኒ ፋሽስት ፓርቲ፣ ከአልቃይዳና ከአይሲስ የከፋ የወንጀል ኢንተርፕራይ እንደሆነ የሚያሳዩ የኢትዮጵያ እውነቶችን በተጠና መልኩ አለም እንዲያውቀው ቢያደርጎ ኖሮ ፋሽስት ወያኔ የኔ በሚለው ሕዝብ ላይ ሳይቀር  የዘር ማጥፋት፣ የጦር ወንጀልና  በሰብዓዊ ፍጡር ላይ የጭካኔ ተግባር  እየፈጸመ በሚሰራው የውሸት ፕሮፓጋንዳ ኢትዮጵያ አትከሰስም ነበር።
Filed in: Amharic