ኢትዮጵያን ያለ ሀፍረት …!!!
ጄፍ ፒርስ
“ኢትዮጵያ ጥንታዊት ነች፡፡ ከሹክሹክታዎችና ከጩኸቶቿ የገዘፈች፡፡……… ኢትዮጵያ ትቀጥላለች ምክንያቱም ህዝቦቿ ያምኑባታልና፡፡ የኢትዮጵያን የማይቀርላትን ውድመት የሚተነብዩ የምዕራባዊያን ሚዲያዎችና ለዲያስፖራ ተብለው የሚሰራጩ አነስተኛ ድህረ ገፆችን በማየት ቀኑን ሙሉ ልትውሉ ትችላላችሁ፡፡….. ኢትዮጵያ የምትባል ሀገር ኖራም አታውቅም የሚል ትርክት እንሰማለን፡፡ ኖራም አታውቅም ግን አሁንም አደጋ ነች ይሏታል እነዚሁ ተቺዎቿ፡፡ ስሟን እየተጠቀሙ እርኩስ ይሏታል፣ ኖራ አታውቅም ያሏትን ሀገር፡፡….. አረሞች የሚያፈሩት ጥሩ ማዳበሪያ ሲኖር ነው፡፡ በርግጥም ጥሩ ማዳበሪያ ነበረ፡፡
በአንዳንድ ትርክቶች እንደሚነገረን ኢትዮጵያ ማለት ገዢዎች ለሺህ አመታት በህዝቦቿ ላይ ሲጠቀሙባት የነበረች ማጭበርበሪያ ነች፡፡
ምንም እንኳን ከታላላቆቹ አፄዎች አንዱ ትግራዋይ የነበሩ ቢሆንም፣
ምንም እንኳን ከዚች አፈ ታሪክ ከሚሏት ሀገር ጀግኖች አርበኞች አንዱ ሌላው ትግራዋይ ራስ አሉላ ቢሆኑም፣
ምንም እንኳን ሪቻርድ ግሪንፊልድ እንደፃፈው የሸዋ ገዢዎች አልፎ አልፎ ከኦሮሞ ቤተሰቦች ጋር ሲጋቡ የነበሩ ቢሆንም ፣
ምንም እንኳን እጅግ ተወዳጅ የነበሩት ንጉሰ ነገስት የተቀላቀለ ዘር የነበራቸው ቢሆንምና ከብዙ የኦሮሞ ቡድኖች ጋር በድርድር ቢግባቡም፣
ምንም እንኳን የመጨረሻው ንጉሰ ነገስቷ የኦሮሞ ዘር የነበረባቸው ቢሆንም………ኢትዮጵያ በአማራ የበላይነት ስር እንደነበረች ሊያሳምኑ እንደሚሞክሯት ጥንታዊ አቢሲኒያዊ ግዛት ነች።
.
.
የኢትዮጵያን ባንዲራ የሚጠሉ ይኖራሉ፣ እኔ ግን የአንዲት ሀገር ነፍስ አርማ ነች እላለሁ።……” ሙሉውን በዚህ ማስፈንጠሪያ ያዳምጡት! https://youtu.be/ nrnSbucjVz4