>
5:13 pm - Monday April 20, 6465

አሁን ያሉት ፓለቲከኞች ህዝቡን ፈፅመዉ አያዉቁትም...!!! (አርቲስት መሀሙድ አህመድ)

አሁን ያሉት ፓለቲከኞች ህዝቡን ፈፅመዉ አያዉቁትም…!!!

አርቲስት መሀሙድ አህመ

* እነሱ ሀገሬን ለመግለፅ ከፃፉት መፅሀፍ ከደሰኮሩት ዲስኩር፡ ካቅራሩት ሽለላ በላይ የ እጅጋየሁ ሽባባዉ አንድ ስንኝ ዜማ መቶ እጥፍ ሀገርን የመግለፅ አቅም አለዉ…!!!
  ፓለቲካ ህዝብን መወከል ከሆነ ግን! አሁን ያሉት ፓለቲከኞች አንዳቸዉም የወከሉትን ህዝብ ለኔ አላስረዱኝም
  የአማራ ወኪል ነን ያሉ ሰዎች ካወሩልኝ አማራነት ይልቅ እነ ማሪቱ ፡ ኤፍሬም፡ አስቴር እና ሌሎች የዘፈኑልኝ ባህልና ታሪክ በደንብ ገብቶኛል:
:
   የኦሮሞ ጠበቃ ነን ብለዉ ሲደሰኩሩልኝ ዉለዉ ከሚያድሩ ፓለቲከኞች በላይ አሊ ቢራ ያቀነቀነልኝ ኦሮሞነት ሲበዛ ገብቶኛል፡፡
  የትግራይ ጠባቂ ነን ብለዉ ጆሮዬን ከሚያደሙት በላይ የኪሮስ ጊታር ሺ እጥፍ ትግሬነትን አስረድቶኛል፡፡
    አሁን ያሉት ፓለቲከኞች ህዝቡን ፈፅመዉ አያዉቁትም! እሱንም አይወክሉም፡፡ እነሱ ሀገሬን ለመግለፅ ከፃፉት መፅሀፍ ከደሰኮሩት ዲስኩር፡ ካቅራሩት ሽለላ በላይ የ እጅጋየሁ ሽባባዉ አንድ ስንኝ ዜማ መቶ እጥፍ ሀገርን የመግለፅ አቅም አለዉ፡፡
Filed in: Amharic