>

በቻግኒ ከተማ የሆነው እንዲህ ነው! (አማራ ኮምዩኒኬሽን)

በቻግኒ ከተማ የሆነው እንዲህ ነው!

አማራ ኮምዩኒኬሽን

* … በገዳዩና በነፍሰበላው ቡድን አባል ላይ ስለተወሰደው እርምጃ  አንድ እዉነት መታወቅ አለበት..!
እርምጃ የተወሰደበት ሰዉ “ለህክምና የመጣ ነው” የሚለው ፍፁም ሃሰት ነው።
ይልቅስ በመተከል የንፁሃንን ነፍስ የሚቀጥፈው የገዳይ ቡድኑ አባልና ለስለላ ተግባር ወደ ቻግኒ የታለከ ሰው ነበር። እውነታውን ከልብህ መረዳት ከቻልክ ይህን አንብብና ለሌሎችም  እውናታውን አጋራ!
ሰሞኑን መተከል በተከሰተዉ ግድያ ከቻግኒ ግልገል ያለዉ መስመር ተዘግቶ ነበር። በዚህ መካከል መንገዱ በመዘጋቱ ይሄ ገዳይ የነበረው  ጉምዝ  ግለሰብ ወደ ቻግኒ ይገባል። በዚህ መካከል ጉምዙን ከተማ ዉስጥ የተመለከቱ ቻግኒ የሚገኙ ተፈናቃዮች እየተጠራሩ መሰባሰብ ይጀምራሉ። ወቅቱ አስጊ በመሆኑ የከተማዉ የፀጥታ ሀይሎች ጉምዙ ቻግኒ ከተማ ዉስጥ መገኘቱ ስላሳሰባቸዉ ሊያናግሩት እየሞከሩ ነዉ። በመካከል የተሰባሰበዉ ተፈናቃይ ከቁጥጥር ዉጭ ሆነ። ጉምዙን ከፀጥታ ሀይሎች ነጥቀዉ የእራሳቸውን እርምጃ  መውሰድ  ጀመሩ።
ጉምዙ ሻምበል ይባላል። ድባጢ ዙሪያ ሲጨፈጭፉ ከነበሩ ጉምዞች አንደኛዉ ነዉ። በቪዲዮዉ ላይ እንደሚታየው ሟቹን በተደጋጋሚ እየደበደበው የነበረዉ ልጅ ሻምበል የተባለው ጉምዝ  እናትና አባቱን በአሰቃቂ ሁኔታ ሲገድል ተመልክቷል፤ አዎ ሻምበል የቤተሰቦቹን ነፍስ በልቶበታል። ሌሎቹ ተፈናቃዮችም ሻንበልን በድባጢ ዙሪያ የነበሩ ገዳይ ሽፍቶች አባል እንደሆነና ግድያ ሲፈፅምም ያዉቁታል። እነዚህ ልጅ፣ ወንድም፣ እህት፣ እናት፣ አባት የተገደለባቸዉ ቁጡ ተፈናቃዮች ናቸዉ ግድያዉን የፈፀሙ። ብዙዎቹ በደረሰባቸዉ ግፍ ስነልቦናዊ ቀዉስ ዉስጥ የሚገኙ ናቸዉ። በዚህ መንፈስ ዉስጥ የሚገኙ ሰዎች ደግሞ መሰል አረመኔያዊ ግድያ የመፈፀም እድል አላቸዉ። መተከል እየተፈፀመ ያለዉ ነገር እጅግ አደገኛ ነዉ። አንድን ማህበረሰብ ነጥሎ ማጥቃት ቂምና ጥላቻን ያወርሳል ብለን ብዙ ጩኸናል። ይሄዉ ከጭፍጨፋ ተርፈዉ ተፈናቅለዉ የሚገኙ ወገኖቻችንን በተፈፀመባቸዉ ግፍ የገቡበት እልኸኝነት፣ ቂምና ጥላቻ መሰል የመንጋ ፍርድ ዉስጥ አስገብቷቸዋል።
ግድያዉ ሻምበል ቤተሰቦቻቸዉን የገደለባቸዉ በተቆጡ ተፈናቃዮች የተፈፀመ ነዉ። የከተማዉ ሰዉ በዚህ ግድያ ላይ ተሳትፎ አላደረገም። የሻምበልን መገደል የሰማዉ የጉምዝ ገዳይ ሽፍታ ቡድን ወደ ቻግኒ ሰርጎ በመግባት ለመጨፍጨፍ ሲሞክር የከተማዉ ሰዉ ነዉ ተሰብስቦ የተከላከለዉ። ሰሞኑን ማህበራዊ ሚዲያዉ ላይ ሰማዕትነት የከፈሉ ሰዎች ሲዘዋወሩ የተመለከታችኋቸዉ ንፁሃንን ከጅምላ ጭፍጨፋ ለመታደግ ሲፋለሙ የወደቁ ናቸዉ።
~~~
ንፁሃን አማራዎች በዘግናኝ መልኩ ሲገደሉ ዝም ያላችሁ፣ ዛሬ ገዳይ ሲገደል ነጠላ ዘቅዝቃችሁ መጣችሁ… ወይስ የበርካቶች ንፁሃን አማራዎች ግድያ በቪዲዮ ተቀርፆ ይላክላችሁ? መርጦ አዛኝነትና የገዳይ ጠበቃነት መሆናችሁ ቀርቶ ግፍን በእኩል ማውገዙ ለነጋችን በእጅጉ ያግዘናል።
  ግድያውን ማውገዙ ተገቢ ቢሆንም አማራ  በወለጋ በመተከልና በማይካድራ በጅምላ ተረሽኖ በዶዘር ሲቀበር ባለ  አልፎ የዛሬውን ብቻ ነጥሎ ማውገዝ  ግን ፍትህ አይደለም።
 ስናወግዝ እኩል ማውገዝ እንጅ እየመረጡ ማውገዝ ተገቢ አይደለም።
Filed in: Amharic