>

አንዳንድ "ሰብዐዊያን"¡¡¡ (መስከረም አበራ)

አንዳንድ “ሰብዐዊያን”¡¡¡

መስከረም አበራ

*… የገዳያችሁን አውሬነትን በመጋራት የሚመጣ ድል የለምና ትግላችሁን ወደኋላ በሚጎትት የጭካኔ ተግባር ውስጥ አትግቡ!
 
የአማራ/አገው ህዝብ በማንነቱ ሰበብ የውሻ ሞት እየሞተ እንደሆነ በግልፅ ስናገር ይህን በመፃፍሽ የአማራውን ሞት ታብሻለሽ ፣ታባያለሽ እንጅ ተጎጅዎችን ምንም አትጠቅሚያቸውም የሚሉኝ “ሰብዓዊያን” ዛሬ ጉሙዝ በአማራ/አገው በጭካኔ መገደሉን ለማወጅ በአንድ ሰዓት ውስጥ ሶስቴ ፖስት እያደረጉ ነው። ምነው ያባላል ብለው አልተውትም???!
እነዚህን ነው “አንዳንድ ሰብዐዊያን” የምለው። እንጅ በማንኛውም ሰዓት ኢ-ሰብዐዊ ድርጊትን የሚያወግዙትን አይመለከትም።
 ለአንዳንድ ሰብዐዊያን አማራ/አገው በማንነቱ አለቀ ማለት ያባላል፤ የእነሱ አንድ ጉሙዝ በቻግኒ ከተማ በአማራ/አገው ተቀጥቅጦ ተገደለ ማለት ብሄር ብሄረሰቦችን ያፋቅራል ፣ያሳስማል ፣ ያስተቃቅፋል ¡
 #ሰባራ_ሚዛን
የገዳያችሁን አውሬነትን በመጋራት የሚመጣ ድል የለምና ትግላችሁን ወደኋላ በሚጎትት የጭካኔ ተግባር ውስጥ አትግቡ
የአገውና የአማራ ህዝብ የተደረገበትን ቃላት የማይችሉት በደል አሳምሬ አውቃለሁ ብቻ ሳይሆን እጅግ የማዝንበትና በየደረስኩበት የምጮህለት ነገር ነው።ሌላው ቀርቶ  ባለ ጠበንጃን  መንግስት  ሳይቀር የምሞግትበት ነገር ነው።
 ስለዚህ የአገውን እና የአማራን ህዝብ ይህን በደሉን ለማስቆም የሚያደርገው ትግል ውስጥ ምን መደረግ ምን አለመደረግ እንዳለበት የመሰለኝን ስናገርም በሞታችሁ ጊዜ ድምፃቸውን አጥፍተው ያጠፋችሁ ሲመስላቸው ብቻ  ሊወቅሷችሁ እንደሚመጡ ወዳጅ መስሎ ጠላት ፍርደ-ገምድሎች ሆኜ አይደለም!!!!
 እዚህ ያደረሳችሁ ምን እንደሆነ ይገባኛል፣ቁስላችሁ ያመኛል። ሆኖም የገዳያችሁን አውሬነትን በመጋራት የሚመጣ ድል የለምና ትግላችሁን ወደኋላ በሚጎትት የጭካኔ ተግባር ውስጥ አትግቡ። የድሉ መንገድ ሌላ ነው! ወገኖቸ ልለምናችሁ እንደዚህ አይነት የተሳሳተ መንገድ ውስጥ አትግቡ……
 እንዲህ ያለው ተግባር ሞታችሁ ይቆም ዘንድ ለመሞገት አፍ ሞልቶ ለመናገር የሚያደነቃቅፍ ነገር ነው። እባካችሁ የውስጣችሁን ብሶት ቻል አድርጋችሁም ቢሆን ከሰብዓዊነት ማማ አትውረዱ።  ልመና ነው
Filed in: Amharic