>

ኤፌሶን_አጣዬ ዛሬም በከባድ መሳሪያ እየተናጠች ነው!  - ሰዎች ይሞታሉ፣ ይፈናቀላሉ፤ ከብቶች ይነዳሉ ቤቶች ይቃጠላሉ !! (ዘመድኩን በቀለ)

ኤፌሶን_አጣዬ ዛሬም በከባድ መሳሪያ እየተናጠች ነው!
 – ሰዎች ይሞታሉ፣ ይፈናቀላሉ፤ ከብቶች ይነዳሉ ቤቶች ይቃጠላሉ !!
ዘመድኩን በቀለ

*….  ከአዲስ አበባ- ደሴ -መቀሌ የሚያስኬደው ዋና መንገድ ትራንስፖርት ተቋርጧል…!
 
እንግዲህ ቢመራችሁም ዋጡት… 
 
… ኢንሻአላህ እያሉ አጣዬን እያቃጠሉ የሚታየውን ቪድዮ የሚቀረጽው ሰው ለመላ የኦሮሞ ሙስሊሞች፣ ለእነ ጀበሉ ሪፖርት እያቀረበ ነው። በረመዳን ጾም ላይ ላሉ ሙስሊሞች ሪፖርት እያቀረበ ነው። ለእነ ሽመልስ አብዲሳ፣ ለእነ ብርሃኑ ጁላ ሪፖርት እያቀረበ ነው። ዐቢይ አሕመድን፣ ደመቀ መኮንንን፣ ሙፈሪያት ካሚልን ጮቤ የሚያስረግጥ ሪፖርት እያቀረበ ነው። እንዲህ ነው የሚለው። …  
… አሰላም አሌይኩም ወረመቱላ ወበረከቱ፥ ይኸው የአጣዬ ከተማን እንዲህ እያደረግናት ነው። አሁን ነፍጠኛ ተሰዳ ከከተማዋ ለቃ ሸሽታ ወጥታለች። ይኸው እንደምትመለከቱት ጭስና እሳት ብቻ ሆኗል። ኢንሻአላህ ፈጣሪ ካለ ድሉ የእኛ ነው። ትልቁ ጦርነት በጸሎት ነው። በጸሎት አላህን ጠይቁልን፣ አግዙን። አሁን ሲቃጠል የምታዩአቸው ቤቶች በሙሉ የዐማራ ቤቶች ናቸው። ጦርነቱ እዚያማዶ ነው የሰላማ መንገድ የሚሉት ሥፍራ ላይ ነው። የሥፍራዎቹን ስም በደንብ አላውቃቸውም። ከዚህ ከዐማሮች ቀብር ጀምሮ ከወንዙ ጨምረን አንድ ሳናስቀር ነቅለን አውጥተን ጨርሰናቸዋል። ያስቀረነው የለም። ከወደላይ ልዩኃይሏ አለች ይላሉ ነገር ግን ኢንሻአላህ ድሉ የእኛው ነው። እናንተ ጸሎት ብቻ አድርጉልን።በጸሎታችሁ ከእኛ ጋር ሁኑ ነው የምንላችሁ። ወሰላም አሌኩ ወረመቱላ ወበረካቱ… ነው የሚለው እስላማዊው የሰሜን ሸዋ ተዋጊ።
… አንዳንዶች እውነታውን መቀበል ከብዷቸዋል። ዐቢይ አሕመድ ኢትዮጵያን ኢያፈረሳት ነው ብንልም ሰሚ አጥተናል። አንዳንዶች እሱ ምን ያድርግ ሽመልስ ነው፣ አዲሱ ነው፣ አዳነች፣ ታከለ ነው። እሱ ምን ያድርግ ብለው ጭራሽ ሽንጣቸውን ይዘው ይሟገቱለታል። እንደ ጻድቅ እንደ ቅዱስ እሱን ብቻ የሚሰብኩት ሞልተዋል። በተለይ ኦርቶዶክሳውያን ሆነው ጳጳስ መምህር ካህን ሆነው ዐቢይን ሲሰብኩት ማየት ያማል። ሃገር ግን የምትመራው በዐቢይ አሕመድ ነው። የሁላቸውም ሿሚና ሻሪ ዐቢይ አሕመድ የሚሉት ናቡከደነፆር የሆነ ሶዬ ነው። ይሄን ማመን አይፈልጉም።
… እሳቱ ግን በ4ቱም አቅጣጫ እየነደደ ከደጃፍ ደርሷል። ሳትወድ በግድህ አፍንጫህ ስር ሲደርስ ታየዋለህ። ያነዜም ታምናለህ፣ ትቀበለዋለህም። ቁስሉ ሲደርስብህ… ሲነካህም ይሰማሃልም። መባነንህ ከረፈደ ይሆናል። ያንጊዜ ትጮሃለህ የማይጠቅም ጩኸት ነው። ያን ጊዜ እሪሪሪ ትላለህ፣ የማይጠቅም እሪታ ነው። ያን ጊዜ ኡኡ ዋይዋይ ትላለህ፣ የማይጠቅም ዋይታ ነው። ከንቱ ጩኸት።
… ከኦሮሚያ እያጸዱህ ነው። በጎንደር በኩልም እንደዚያው። ከመተከልም አጽድተውሃል። ሰሜን ሸዋም እያጸዱህ ነው። በገዛ ሃገርህ ስደተኛ ደሃ አድርገው የኩርድን መንገድ አስይዘውሃል። ተደራጅ፣ ራስህን ጠብቅ ስንልህ አሾፍክብን፣ ሳቅብን፣ ተሳለቅብን፣ ሰደብከን፣ አዋረድከን። እንግዲህ መቻል ነው። የሚመጣውን መጋፈጥ ብቻ ነው። የከበደ ነገር ከፊታችን መጥቷል። መንግሥታዊ ጄኖሳይድ… ሩዋንዳ…
… አሁን ዐቢይ አሕመድ ጮቤ እየረገጠ ነው። የማስቀየሻ፣ አጀንዳ የማስቀየሪያ ቁማር እየደረሰም ነው። ” ኢትዮጵያ አትፈርስም” ይልልሃል ኢትዮጵያን አንድዶ እያጨሳት። ዐመድ እያስደረጋት። ጄነራል ብርሃኑ ጁላ ፌሽታ እያደረገ ነው። ዶር ብርሃኑ ነጋ ለምርጫ ውድድር ሱፍ እየቀያየረ ነው። አንዷለም አራጌ ዘመዶቹ እየተሰደዱ ነው። እዚህ አጣዬ የዐማራ ቤት፣ የክርስቲያን የሙስሊም ዐማራው ቤት እንዲህ እንደ ጧፍ እየነደደ ነው። ጄኖሳይዱ መንግሥታዊ ነው። መንግሥት መር ነው።
… ብአዴንን እርሱት። አትውቀሱትም። ተዉት በቃ ንቃችሁ፣ እንደሌለ ቆጥራችሁ እርሱት። ይልቅ እያንዳንድህ ራስህን አድን  !!
*****
በኦሮሞ ብልፅግና የሚደገፈው ኦነግ-ብልፅግና በጥንቷ #ኤፌሶን በዛሬዋ #አጣዬ ከተማ ላይ፣ እላይ ተራራው ጫፍ ሆኖ የጦርነት እሩምታ ከፍቷል። ከተማዋ ላይ ከፍተኛ ቃጠሎ ተነስቷል። ህዝቡም ለቆ እየወጣ እንደሆነ እና  በአካባቢው ካለው ልዩ ሀይል እና መከላከያ ሰራዊት አቅም በላይ መሆኑን ነው የአካባቢው ሰዎች የሚናገሩት።
ሰሞኑን በቆሬ ሜዳ የከባድ መሳሪያ ልምምድ ሲያደርጉ የነበረው ይህ አሸባሪ ቡድን ጦርነት የከፈተው በካራ ቆሪ፣ በአንጾኪያ ገምዛ፣ በአላላ፣ በቀወት፣ በማጀቴ….. አካባቢዎች ጭምር ነው።
በጦርነቱ ምክንያት ከአዲስ አበባ- ደሴ -መቀሌ የሚያስኬደው ዋና መንገድ ትራንስፖርት ተቋርጧል።
በቅርቡ ከሸዋሮቤት ጥቂት ኪሎ ሜትሮች ወጣ ብላ በምትገኘው እና ባልጭ በተባለች መንደር
በአይሱዙ ላይ የነበሩ እና በሃይሩፍ የህዝብ ማመላለሻ መኪና ውስጥ የነበሩ ንጹሃን ላይ ድንገተኛ ጥቃት ከፍቶ ሰዎች እንደሞቱ ይታወሳል።
 ከአንድ ወር በፊት ከ300 በላይ ሰዎች ህይወት እንዳለፈ የምናስታውሰው ነው።
አጣዬ በተደጋጋሚ ስልክ ደወልኩ ከተማዋ እንዳለ ጫፍ እስከ ጫፍ በአሸባሪዎቹ ተወራለች!!!
ሙሉ ለሙሉ በሚባል ደረጃ በእነርሱ ቁጥጥር ስር ውላለች ከላይ ከተራራው ከፈተኛ የጦር መሳሪያ ጭምር ወደ ከተማዋ እየተተኮሰ ነው ህዝቡ ከተማዋን በፍጥነት ለቆ እየወጣ ሲሆን ሽፋን እንኳን የሚሰጣቸው የመንግስት የፀጥታ አስከባሪ ሀይል እንደሌለ በምሬት እየተናገሩ ነው
የሚሰማው የተኩስ ድምፅ እንኳን ከዛ ላለ ሰው በስልክ ለሚሰማውም ያስበረግጋል
በአንፆኪያ ገምዛ መስኖ እየተበለ በሚጠራው አካባቢ ከፍተኛ ተከስ ተከፍቶ ንፅሀኖች እየወደቁ ነው
እንደዚሁም ቆሪሜዳ  ማጄቴ አንቃር አላላ  ኩሩቢሪ  አካባቢዎች የኦነግ አሸባሪ ሀይል  በከፍተኛ ሁኔታ ሀይሉን አጠናክሮ እየገባ ነው
የአጣዬ እና አካባቢው ነዋሪዎች እባካችሁ ሌላው ሁሉ ይቅር መንግስት ካለ ነፍሳችንን እንኳን ይታደገን ለሚመለከታቸው አካላት አሳውቁልን እያሉ ነው
እባካችሁ የሚመለከታችሁ የመንግስት አካላት በፍጥነት ይህንን ህዝብ ትታደጉት ዘንድ በልመናም ጭምር እንማፀናችኀለን
Filed in: Amharic