>

በበላኤ ሰብእ ዐቢይ አሕመድ ዘመን ኢትዮጵያ አማራ በጅምላ የሚታረድባት ቄራ ሆናለች...!!! አቻምየለህ ታምሩ

በበላኤ ሰብእ ዐቢይ አሕመድ ዘመን ኢትዮጵያ አማራ በጅምላ የሚታረድባት ቄራ ሆናለች…!!!
አቻምየለህ ታምሩ

ከቡሬ ወደ ነቀምት ይጓዝ በነበረ መኪና ውስጥ በተሳፈሩ የአማራ ተወላጆች ላይ ተየተፈጸመው አረመኔያዊ ጭፍጨፋ ኦሮሙማ እየተተገበረ እንጂ እየተጣሰ እንደሆነ የሚያሳይ አይደለም። ኦሮሙማ ኦሮሞ ያልሆነውን ፍጡር ሁሉ በጅምላ እየፈጁ ከምድረ ገጽ የማጥፊያ የጭካኔ መንገድ ነው። የዚህ የጭካኔ መንገድ ዋና ሥራ አስፈጻሚ በላኤ ሰብእ ዐቢይ አሕመድ ነው። በበላኤ ሰብእ ዐቢይ አሕመድ ዘመን በግፍ የፈሰሰው የንጹህ የአማራ ተወላጆች ደም፤ አሞራና ጅብ እንዲበላው የተደረገው የአማራ ሕጻናት፣ ሴቶችና አረጋውያን ሥጋ፤ የተፈጸመ ግፈና የጭካኔ አይነት ተነግሮ የሚዘለቅ አይደለም።
ባጭሩ በበላኤ ሰብእ ዐቢይ አሕመድ ዘመን ኢትዮጵያ አማራ በጅምላ የሚታረድባት ቄራ ሆናለች። በበላኤ ሰብእ ዐቢይ አሕመድ የሚመራው የበላኤ ሰብእ አገዛዝ [Predatory Regime] እስከቀጠለ ድረስ ዛሬ በአማራው ላይ የሚካሄደው ጅምላ ፍጅትና የዘር ማጥፋት ሁሉ ነገር በሁሉም ላይ ይደርሳል! የዛሬ መኖሩን ብቻ በማየት ነገ ባለተራ የማይሆን መስሎት በአማራ ላይ በየቀኑ የሚካሄደውን የጅምና ፍጅትና የዘር ማጥፋት እንዳላየና እንዳልሰማ አሜን ብሎ ተቀብሎ በኑሮ ጉዳዩ ተጠምዶ ቀኑን የሚያስተላልፍ ቢኖር ነገ ለሚደረግበት ሁሉ ዛሬ በራሱ ላይ እየፈረደ መሆኑን ይወቅ!
Filed in: Amharic