>

የአማራ ፖሊስ ኮሚሽነር አበረ አዳሙ ተገደሉ...!!! (ኢትዮ 360)

የአማራ ፖሊስ ኮሚሽነር አበረ አዳሙ ተገደሉ…!!!

ኢትዮ 360

ኮሚሽነሩ የተገደሉት ተመርዘው እንደሆነም ነው የኢትዮ 360 የውስጥ ምንጮች የገለጹት።
ኮሚሽነር አዳሙ በቅርቡ ከእነ አቶ አገኘሁ ተሻገር ጋ በአጣዬና አካባቢው ጉዳይ ከባድ ውዝግብ ውስጥ ገብተው እንደነበርም ምንጮቹ ይናገራሉ።
ይሄ ውዝግብ ደግሞ ኮሚሽነሩን ከስልጣን እስከማስነሳት የደረሰ እንደነበርም ነው ምንጮቹ ያስታወሱት።
አሁን ላይ ኮሚሽነሩ ስለመገደላቸው ይሄ መረጃ እስከወጣበት ድረስ ከባለስልጣናቱ የተባለ ነገር ባይኖርም በዚህ ግድያ ውስጥ ግን እስከ ፌደራል ድረስ ያሉ አካላት እጅ ሊኖርበት ይችላል ሲሉም አክለዋል።
በአማራ ክልል እየተፈጠረ ካለው የባለስልጣናቱ አለመግባባት ጋር ተያይዞ የሰኔ 15ቱ አይነት ግድያ ሊከሰት ይችላል የሚል መረጃን ኢትዮ 360 ለህዝብ ማቅረቡ ይታወሳል።
Filed in: Amharic