>

የሃጂ ቱሬን ገንዘብ እጨርሳለሁ ብለህ ጉበትህ እንዳይፈነዳ! (ሰሎሞን ንጉሡ)

የሃጂ ቱሬን ገንዘብ እጨርሳለሁ ብለህ ጉበትህ እንዳይፈነዳ!

ሰሎሞን ንጉሡ


አንድ ጨዋታ ከሰማሁ ብዙውን ጊዜ አልረሳም ነበር፡፡ አሁን አሁን ግን ዕድሜውም የወቅቱ አስጨናቂ ሀገራዊ ሁኔታም እየተደራረቡብኝ መርሳት ጀምሬያለሁ ብቻ ሣይሆን አንዱን ልጄን ለመጥራት ራሱ የስምንቱንም ስም ከጠራሁ በኋላ ነው መጥራት የፈለግሁትን የምጠራው፡፡ እንኳን ዘምቦብሽ እየሆንኩ ነው፡፡ እንደሀገሬ ሲያልቅ አያምር ሆኜላችኋለሁ፡፡

እናም የሃጂ ቱሬ ልጅ ይሁን የሌላ ቱጃር ልጅ – አይ የርሱው ይመስለኛል ኧረ – ረብጣ ረብጣ ብር እየያዘ ውድ ውድ ዝጉብኞችን ያዘወትር ነበር፡፡ አባቱ እጅግ ሀብታም ከመሆናቸው የተነሣ የገንዘብ ችግር የለበትም ነበር፡፡ የፈለገው ቡና ቤት ይገባና ቡና ቤቱ እንዲዘጋ በማድረግና ውስጥ ያሉትን ጠጪዎች የሁሉንም ሒሣብ በመክፈል እያዝናና ይዝናናል፡፡ በመጨረሻም ጥምብዝ ብሎ ወደ ቤቱ ይሄዳል፡፡ ይህን የተረዱት አባቱ ታዲያ “አንተ ልጅ፣ የሃጂ ቱሬ ገንዘብ ያልቃል ብለህ ጉበትህ ፈንድቶ እንዳትገላገል” በማለት ያስጠነቅቁት ነበር፡፡ ያሉት አልቀረም፤ ልቡ ትሁን ኩላሊቱ በመጠጥ ኃይል ፈንድተው አሁን በሕይወት የለም፡፡ ነፍስ ይማር፡፡ መኖር ሲቻል መሞትን የሚመርጡ ያሳዝናሉ፡፡

አቢይና ሽመልስ አማራን የፈጁ መስሏቸው የራሳቸውን ካርማ (Karma) በሰው ደምና አጥንት እያጨቀዩ ይገኛሉ፡፡ ይህ በወንጀልና በኃጢኣት የበከተ ስብዕናቸው የሚያስከትልባቸውን የነፍስና የሥጋ ሞት አልተረዱም፡፡ “የማያዛልቅ ባል ቅንድብ ይስማል” እንደሚባለው ኦሮሞን የጠቀሙ መስሏቸው ዕዳ ውስጥ እየከተቱት ነው – ያው በስሙ የሚንቀሳቀሱ በመሆናቸው የተወሰነ ማኅበረሰብኣዊ ቀውስ ማስከተላቸው እንደማይቀር ከተጋሩ ተምረናል፡፡ እንጂ ጎዳና ያዕቆብንና ታምራት ነገራን የወለደ የኦሮሞ ማሕጸን በኢትዮጵያዊነቱና በደገኛ ማኅበራዊ መስተጋብሩ የሚታማ ሆኖ አይደለም፡፡ ከስንዴ መሀል እንክርዳድ መኖሩ ግልጽ ነው፡፡ ችግሩ እንክርዳዱ ጉልበት ያገኝና ስንዴውን ሸፍኖ ግዘፍ መንሳቱ ነው፡፡ ያቺ የትግራይ ወያኔ በተጋሩ ስም ለ46 ዓመታት አባ ጉልቤ (ባሁኑ ምንዛሬው አባ ቶርቤ) ሆና በቀላሉ የማይፋቅ ታሪካዊ ጠባሳ እንዳስከተለችው ሁሉ እነዚህ በኦሮሞ ስም የሚነግዱ መቀመጫቸውን ያልጠረጉ ደናቁርትም ዝቀን የማንጨርሰው ዕዳ አሸክመውን እንዳያልፉ እንሰጋለን – የሚያልፍ ታሪክ የማያልፍ ጠባሳ እንዳይተውብን፡፡

 እንዳላዘናጋችሁ እፈራለሁ እንጂ አቢይም ሆነ ኦሮሙማው ኢትዮጵያን ያሸንፋሉ ብሎ ማመን የጅልነቶች ሁሉ ጅልነት ነው፡፡ እነሱም ለጊዜው “ቁማሩ” የተሳካ መስሏቸው ከልባቸው እየተጃጃሉ ነው፡፡ እዚህ ላይ ነው በርዕሴ የጠቀስኩት የሃጂ ቱሬ ልጅ መጠቀስ የሚገባው፡፡ ልጁ የአባቱን ገንዘብ ለመጨረስ ይሁን ራሱን ለማስደሰት ሲል የማይሆን ነገር ውስጥ ገብቶ ራሱን በደስታ ብዛት አጠፋ – ግን ራሱን ብቻ፡፡ እነአቢይ ደግሞ ኦሮሙማ የሚሉትን ከኦሮሞነት ፍጹም የተለዬ ሰይጣናዊ ፍልስምና እውን ለማድረግ ሰይጣን ራሱ በማያውቀውና ወንበር ዘርግቶ ከነሱ እየተማረው በሚገኘው፣ ዓለማችንም አይታው በማታውቀው የተለዬ ጭካኔ በተለይ አማራንና የአማራን ከተሞች በዘመናዊ ትጥቅና ስንቅ ታጅቦ በጥይትና በእሳት እየረመረመ ነው፡፡ ይህን ጭፍጭፋ የሚመራው አቢይ አህመድ መሆኑን ለመግለጽ በጣም ግልጽ ስለሆነ መሃላን ማባከን አያስፈልግም፡፡ በሌሎች ሀገራት ሲጀመር እንደዚያ ያለ ነገር አይታሰብም – ታስቦ ተግባራዊ ቢደረግ እንኳን አንድ ሰዓት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ መንግሥት ጦር ልኮ የችግሩን ፈጣሪዎች በመለቃቀም ወደ ህግ ያቀርባል፤ እኛ ሀገር ውስጥ ግን የተለዬ አጀንዳ ያለው አጋንንታዊ መንግሥት ቤተ መንግሥታችንን በመቆጣጠሩ ሸኔ በሚል የሚቆላመጠው ቡድን ለተከታታይ ቀናት ከተሞችን ሲያወድምና ዜጎችን በእሳትና በመትረየስ ሲረፈርፍ አቢይ አህመድ የሆሊውድ ፊልም እንደሚያይ በደስታ እየፈነጠዘ ጮቤ ይረግጥ ነበር – ይህ እሳት በቤተሰባቸው ሳይሆን በርሱና መሰሎቹ ላይ ብቻ ይውረድ!  በዚህ በ21ኛው መቶ ክፍለ ዘመን በዚህ ዓይነቱ ጅልነት ግዛትን ለማስፋፋት መሞከር ለጊዜው ጉዳቱ ከግምት በላይ ቢሆንም እንኳን የኋላ ኋላ ግን መዘዙ ወደ መጡበት ቦታ ድረስ ተሸኝቶ ብቻ የመዳን ዕድልም ላይኖረው እንደሚችል መረዳት ተገቢ ነው፡፡ ትክክል የሆነ ዓላማ ቢኖረን እንኳን ሥልቱ ኢሰብኣዊና ዐረመኔነትን የተመረኮዘ ከሆነ ከጊዜያዊ ድል ባለፈ የትም አንደርስም፡፡ 

ዙሪያ ጥምጥም መሄድ አያስፈልገኝም፡፡ ቅልብጭ ያለች ሦስተኛ ዐይን አለችኝ፡፡ በዚህ ዓይነቱ የጽሑፍ አማተራዊ ተሣትፎ የክርስቶስን ምድራዊ ዕድሜ ያህል ቆይቼበታለሁ፡፡ ትምህርትም ሆነ ገንዘብና ዝና ባይኖረኝ – አልሃምዱሊላ – የቀባጭን የመጨረሻ ዕጣ ፋንታ ለመገመትና ገምቼም ለመናገር የሚያስችል “ተሰጥዖ” ግን የለኝም አልልም፡፡ እዚህና አሁን ማስረጃ ልሰጣችሁ አልችልም፡፡ ግን ዝም ብላችሁ እመኑኝ፡፡ የላየ ላይ በል ብሎኝ ባልኩት አፍሬ አላውቅም፡፡

ስለዚህ አክራሪ ኦሮሞዎች ቋቱ እስኪሞላ ፊን ፊን ይበሉ እንጂ በጣም በቅርቡ ለዘር እንኳን በማይተርፉበት ሁኔታ ድራሻቸው ይጠፋል፡፡ እነሱ ይቅሩና የሚፈልጉትን ሰው “እንኳንስ ከአሜሪካ ከመንግሥተ ሰማይ”ም ማምጣት እንደማይሳናቸው በዕብሪት ይናገሩና እስከመቅኒያችን ድረስ ሰርስረው ገብተው የነበሩት ትህነጎችም ያ ሁሉ የዘረፉት ሀብትና ገንዘብና የጦር መሣሪያ በ15 ቀናት ውስጥ የዶግ ዐመድ ሆኗል፡፡ ክፋትን የሚያጠፋው የክፋት ሥራው ነው፡፡ ደም መጥፎ ነው፡፡ ግፍና በደል መቼም ቢሆን ሳይከፈል የማይቀር ዕዳ ነው፡፡ የዛሬው እግዚአብሔር እዚያ እስክትሄድለት ድረስ አይጠብቅህም፤ እዚሁ ነው ብድርህን በምድር የሚሰጥህ፡፡ የኔ ፍጹም እውነት የሆነ “ትንቢት” መሠረቱ ማንም ምራቅ የዋጠና ከሕይወት ተሞክረው ትምህርት የቀሰመ ዜጋ ሁሉ በግልጽ ሊናገረው የሚችለው ተራ ነባራዊ እውነት ነው፡፡ አንድ ሰው ሰውን በመግደል የትም ሊደርስ አይችልም፡፡ በማጥፋትና በማውደም ምንም ዓይነት ዓላማ ወደ ስኬት ጫፍ አይደርስም – የሥልጣን ጉጉዎች እርግጥ ነው በዚህ መንገድ ይራመዳሉ፡፡ ከዚህ አኳያ የነአቢይ ሙከራ ያገኟትን ጠማማ ዕድል ከመሞከር አይዘልም – ደግሞም ልጆች ናቸው – ሸውራራ ታሪክ ሲጋቱ ያደጉ ደመ ሞቃት ልጆች፡፡ በነዚህ ገልቱዎች የጨፍጭፉ ትዕዛዝ ከ80 የማያንሰው የኢትዮጵያ ጎሣና ነገድ በአሁኑ ወቅት በአርምሞ ፀጥ ብሎ በነግ በኔ እየታዘበ ነው – ብዙው ደግሞ በአማራ ላይ እየደረሰ ባለው የዘር ማጥፋት (ጄኖሳይድ) አንጀቱ እያረረ እንደሆነ መገመት አይከብድም፡፡ እያጦዙት ያለው ዙር “ሞሜንተሙን” ወይም አኪሩን ሲጨርስ ታያላችሁ፡፡ ሁሉም ነው የሚዘምትባቸው፡፡ ምክንያቱም “በጊዜ የጮኸ ጅብ አያሳድረኝም” እንደሚባለው ዛሬ ትግሬንና አማራን የበላና ያባላ ጅብ ነገ አፍታም ሳይፈጅበት ሶማሌንና አፋርን፣ ጀምጀምንና ኮንሶን፣ ጉራጌንና ወላይታን፣ ሲዳሞንና ጋሞን፣ ደራሳንና ጠምባሮን፣ ኑዌርንና አኙዋክን፣ በርታንና ሽናሻን፣ አገውንና ቅማንትን፣ ኣሪንና ሙርሲን፣ አደሬንና ቆቱን፣ ከምባታንና ሃዲያን፣… እንደሚሰለቅጣቸው የታመነ ነው፡፡ እነዚህ ሁሉ ጎሣዎች ይህን እውነት ያውቃሉ፡፡

ውድ ወገኖቼ!

በሚመጣው ከፍተኛ አደጋ አትደንግጡ አልልም – ደንግጡ፤ ተናደዱ፤ ራሳችሁን ከአደጋው ለመከላከልም ከጸሎት ጀምሮ የምትችሉትን ሁሉ አድርጉ፡፡ በነዚህ ደናቁርት ብዙ የግፍ ዓይነቶችን በኃጢኣታችን ጠረጴዛ ላይ በሚሰደር ብፌ ልናይ ጊዜው ከባዱን ሸክም ጥሎብናልና በእስካሁኑ እምብዝም አትደነቁ፡፡ ግን ግን “ሀገራችን ትፈርሳለች፣ ትበታተናለች” ብላችሁ ሃሳብ አይግባችሁ – ያን በአንድዬ እንጣለው፤ ኢትዮጵያ ዩጎዝላቪያ እንዳልሆነች ታሪኳ ምሥክር ነው፡፡ ከመስመር በመውጣታችን እኛን ለማስተካከል ፈጣሪያችን ወዶና ፈቅዶ የላከብን የግራኝ አህመድ ቀጣይ ቅጣት – ምዕራፍ ሁለት ክፍል ሦስት – ነው እየወረደብን የሚገኘው፡፡ ልዩነቱ አህመድ ግራኝ በትምህርት ያልገፋ ሲሆን ዳግማዊ ግራኝ አቢይ አህመድ ግን በማምታታትም ይሁን በለብ ለብ የትምህርት መርሐ ግብር ባለሦስት(ተኛ) ዲግሪና ባለከፍተኛ ማዕረግ የጦር መኮንን መሆኑ ነው፡፡ በአንድ በኩል እሱም ቢሆን ታዞ ነውና ብዙም አንፍረድበት፡፡ ልብ አድርግ – አንድ ሰው ከመሬት ተነስቶ “እነእገሌን በተኙበት በእሳት አንድዳቸው፤ ባገኘኻቸው ቦታ ሁሉ የመጨረሻውን ጭካኔህን አሳያቸው – እረዳቸው፤ ነፍሰ ጡሮችን ሆዳቸውን ቀደህ ጽንሱን ስትፈልግ ለሟች እናቱ አስታቅፋት ከፈለግህም ብላው…” የሚል ትዕዛዝ ማስተላለፍና አንዲትን ሀገር በሦስት ዓመታት ውስጥ ብቻ እንዲህ ሲዖል ማድረግ ከሰው አእምሮ በላይ ነው፡፡ ታዛዦቹም ያሳዝናሉ፡፡ እኔ በበኩሌ ያሳዝኑኛል፡፡ ትዕዛዙ ከጨለማው መንግሥት ባይሆን ኖሮ ለምሣሌ የአጣየና አካባቢዋን ኗሪዎች ስብሰባ በመጥራት ያን አካባቢ ጥለው እንዲወጡና ለኦሮሙማቸው እንዲያስረክቡ ቀጭን ትዛዝ ማስተላለፍ ይችሉ ነበር፡፡ መሣሪያ ያልታጠቁ ሕጻናትንና ሴቶችን መግደልንና ቤትና ንብረትን ማቃጠልን ምን አመጣው? የኢትዮጵያን ሕዝብ ወደ ኦሮሞነት መለወጥ ከፈለጉ ደግሞ እንዲህ በማስበርገግ ሳይሆን ቀላሉ ዘዴ የተለያዩ ጥቅማ ጥቅሞችን በመስጠትና “ኦሮሚያ” ውስጥ  ለሌሎች ዜጎች የሥራ ዕድሎችን በመክፈት ቀስ በቀስ ወደነሱ በመሳብ ነበር፡፡ 

በነገራችን ላይ ሰይጣንን ለመታዘዝ በትምህርት መግፋትና አለመግፋት ብዙ ለውጥ አያመጣም፡፡ እ.አ.አ. በ1966 በአሜሪካን ሀገር የሰይጣንን ቤተ አምልኮ (Church of Satan) በይፋ መሥርቶ ይንቀሳቀስ የነበረው አንቷን ሌቪ እጅግ የተማረና እርሱ ወደ ጌታው ወደ ሣጥናኤል መንግሥት ቢሄድም አሁንም ድረስ ከተከታዮቹ ብዙዎቹ ሁለተኛና ሦስተኛ ዲግሪ ያላቸው ናቸው – እጅግ በርካታ የሀገራት መሪዎች፣ ከበርቴዎች፣ አርቲስቶች (celebrities)፣ ምሁራንና በማኅበራዊና የተፈጥሮ ሣይንሶች ስመጥርና ገናና ሰዎች የዚህ አምልኮ አባላት ናቸው፤ ገንዘብ የኃጢኣት ምንጭ መሆኗ የሚነገረው ለጨዋታ ማስዋቢያ እንዳይመስለን – እውነት ነው፡፡ ስለዚህ በአቢይ ትምህርትና በአስመሳይ ባሕርይው ባለመታለል ማድረግ የሚገባንን በማድረግ ስቃያችን እንዳይረዝም ራሳችንን ከዕልቂት እናድን፡፡ ዝምታና ግዴለሽነት ብዙ ዋጋ እንደሚያስከፍለን ለመረዳት በራቸውን ያልዘጉ ሞኞች ተኝተው በነበረበት አንድ ቤት ውስጥ አያ ጅቦ ሌሊት ላይ ገብቶ በር አካባቢ ያገኘውን ሰው እግር መጎረዳደም እንደጀመረ አንዱ ጥጋት ላይ ተኝቶ የነበረ ሌላ ሰው “ምንድን ነው ይሄ የሚሰማኝ የመጎረዳደም ድምጽ?” ብሎ ቢጠይቅ እየተበላ ያለው ሰው “ዝም በል እንዳታስጨርሰን፤ የኔን እግር እየበላ ነው” ብሎ የተናገረውን ማስታወስ ይጠቅማል – የፉክክር ደጃፍ አይዘጋምና ጅብ ያስበላል፡፡ ስለሆነም ኦህዲድ ሸኔ ማንንም ለማይምረው ነገር ከሥሩ ሆናችሁ የምታሸረግዱ ብአዴንን መሰል ድንዙዛን አያልቅም እንጂ አማራን ከጨረሰ በኋላ ቀጣይ ዒላማዎች እናንተ መሆናችሁን ተገንዝባችሁ ንስሃ ለመግባትና ከገባችሁበት የሆዳምነት አዙሪትና የእሽክርና አባዜ ለመውጣት ብትሞክሩ የመጀመሪያ ተጠቃሚዎች እናንተና የናንተው ቀጣይ ትውልድ ነው፡፡ ሌላውን ለታሪክ እንተወው፡፡ በቅርብ ያበራየዋል፤ አበቃሁ፡፡ 

Filed in: Amharic