>

ኢትዮጵያዊ አርበኛ የመሆን ግዜው አሁን ነው!!!  ደረጄ አሳምነው

ኢትዮጵያዊ አርበኛ የመሆን ግዜው አሁን ነው!!!

ደረጄ አሳምነው

*….ዛሬ ዛሬ በሰፊው ሜዳ እንደልባችን እንድንኖር ብዙ እንደተከፈለልን ባናውቅም ብዙ ተከፍሎልናል።
 በዘርንና በመንደሬነት ሱስ ተለክፈን እርስበር የምንባላው በቂ የታሪክ ማስረጃዎቻችን  ባለመረዳት ይሆን????
 ብናውቅ ሀገራችን እጅግ በጣም አኩሪና አስደማሚ የሆኑ የድልና የተለያዩ ታሪኮች ምንጭ ባለቤት ስለመሆናችን የሚያስረዱን ብዙ የድል ታሪኮች መረጃዎች አሉን!!! 
•ታሪክን በተገቢው በንገድ እንወቅ!!
ጣሊያን ከአድዋ ሽንፈቷ 40 ዓመታት በኋላ በዘመናዊ የጦር መሣሪያና በወታደራዊ ኃይል ይበልጥ ደርጅታ በጠቅላይ ሚኒስትር ቤኒቶ ሙሶሎኒ ትዕዛዝ ኢትዮጵያን ከሦስት አቅጣጫዎች ወረረች፡፡
ሚያዝያ 27 ቀን 1928 ዓ/ም ወደ ኢትዮጵያ የዘመተው የጣልያኑ ጦር አዛዥ ጄኔራል ባዶሊዩ አዲስ አበባ ገብቶ በታላቁ ቤተ መንግሥት የጣሊያንን ባንዲራ ሰቀለ። ከአድዋው ዘመቻ ያልተሻለ የጦር ትጥቅ የነበራት ኢትዮጵያም የጣሊያንን ጦር በፅናት ተዋጋች፡፡
በጀግኖች አርበኞች ብርታትና መስዋዕትነት ተሰቅሎ የነበረው የጣሊያን ባንዲራ ከ5 ዓመታት በኋላ ሚያዚያ 27 ቀን 1933 ዓ/ም በዕለተ መድኃኔዓለም  ወርዶ በምትኩ የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ በታላቁ ቤተ መንግሥት ከፍ ብሎ በክብር ተሰቀለ፡፡
በጀግኖች አርበኞች ታላቅ ተጋድሎና አይበገሬነት ኢትዮጵያ በዓለም ፊት በልጆቿ መስዋዕትነትና የደም ማኅተም ነፃነቷን አፀናች፡፡
ይህም ልክ የዛሬ 80 ዓመት መሆኑ ነው።
በዚህ ቀን በእርግጥም ኢትዮጵያ  እጇቿን ወደ ፈጣሪዋ ዘርግታለች። አምላኳ ልጇቿን እንዲባርክ ትማፀናለች። ኢትዮጵያ ወደ ልጇቿም ትጣራለች። እንዲህም ትላለች ልጆቼ ሆይ ኢትዮጵያዊ አርበኛ የመሆኛ ጊዜው አሁን ነው ትላለች። አዎ ኢትዮጵያ በጠላት ዙሪያገባዋን ተከባለችና ሚሊዮን እርበኛ ልጆች ትፈለጋለች። ሚሊዮን ሸዋረገድ ተክሌ ሚሊዮን በላይ ዘለቀ፣ ሚሊዮን ጃገማ ኬሎ ትፈልጋለች። እናም እኛ ጥሪዋን የሰማን አቤት እንበላት ላልሰማ እናሰማላት። አይዞሽ አለን እንበላት። ኢትጵያውያን ፈፅሞ የማፈግፈግ ሃሳብ እልነበራቸውም። ቀድመው ገዢ መሬት በማያዝ አድፍጠዋል።
ህዳር 12 ቀን ከምሽቱ 3:30 ሰዓት l አካባቢ የኢጣሊያ ጦሩ እንዳጊዮርጊስ ሸለቆ ስለ ደርሷል።  ኢትዮጵያዊያን ግራና ቀኝ ላይ ኮረብታውን ተመሳስለው ለድንገቸኛ ጥቃት አድፍጠዋል  ሁሉም የጠላት ወታደር ሸለቆው ውስጥ እስኪገባላቸ አልመው እየጠበቁ ነው።
ተጠራጣሪው ጀነራል ማሪዮቲ በድንገት በቅሎውን አቁሞ ዙሪያውን ቃኘ። መድፈኛ ሻለቃውን አሰጠርቶ ትዕዛዝ ሰጠው።
ነገር ግን መድፈኛው ሻለቃ ትልቁን መድፍ ላያስተካክል ዘወር ከማለቱ አካባቢው በኢትዮጵያውያን የተኩስ ሩምታ ተናወጠ።
ሸለቆው ውስጥ የቆሙት ኢጣሊያ ቅጥረኛና ነጭ ወታደሮች በሽብር ተናጡ። በዚህ ሽብር ወቅት ሆነውም የኢጣሊያ ወታደሮች በንቀት ” ትንሽ ግዜ ስጧቸው የያዙት አራት ጥይት ሲጨርሱ ይሸሻሉ ” በማለት አሽሟጠጡ።
ነገር ግን ኢትዮጵያውያን ወታደሮች ጥይታቸውን ቢጨርሱም  ወደኋላ አላፈገፈጉም። ሳንጃና ጎራዴያቸውን ቁልቁል እንደ ደራሽ ውኃ ወራሪውን ወረሩት። ወራሪው የፋሽሽት ሀይል የአበሾቸን ህዝባዊ ጎርፍ መቋቋም አልቻለም። በፍረሀት የተሞላው የኢጣሊያ ሰልፈኛ የእጅ ቦንብ ይዞ ቆሟል። አበሾቹ እንደደረሱ ዘለው ተከመሩባቸው። ውጊያው ሳይቋረጥ ለሰባት ሰዓት ቀጠለ።
በሌላ የውጊያ አውድ ለመጀመሪያ ጊዜ ብረት ለበስ ታንክ የተመለከቱት ኢትዮጵያውያን ተደናገጡ። የሸሹም ነበሩ። ነገር ግን አንድ ልበሙሉ አበሻ ታንኩን ዞሮ ከተመለከተው በኋላ ዘሎ ወጣበት። ቀጣዩ ክስተት በመትረየስ የታጀበ ድምፅ ነበር። የመትረየሱ ጥዮቶች የኢትዮጵያዉያንን አካል መቁረስ ቀጠለ። ለዚህ ያልተንበረከኩት ኢትዮጵያውያን እንዳ አባ ጊና ቁልቁለት መጉረፍ ጀምረዋል። ቀኑ ሲጨላልም ኢትዮጵያውያኒ ወታደሮችና ጀግናው የጦር መሪያቸው ራስ እምሩ 50 ከባድ መትረየስ ማርከው ተመለሱ።
“በለው!” በሚለው ስሟ የምትታወቀው በዚያ ሽምቅ ውጊያ ጠላትን ማርበድበድ ቀጥላለች። ልጇንና ከጠላት የማረከችውን መትረየስ ተሸክማ ከባለቤቷና ከሌሎች አርበኝች ጋር ውጊያ ላይ ትገኝ ነበር።
ነሐሴ 10 ቀን የጣሊያን ሰራዊት ነልኬለሽ ላይ ጠንካራ ጥቃት ሰነዘረ። በጥቃቱ የተነሳም ልኬለሽና ባለቤቷ ተነጣጥለው መፋለም ጀመሩ። ልኬለየሽ ለአፍታ ባለቤቷን ከርቀት ሆና ተመለከተችው። ባለቤቷም እጁን አንስቶ ሰላምታ ሰጣት። ተመታና ወደቀ።  ልኬለሽ አጠገቡ ደረሰች። ባለቤቷ ሞቷል።
አስከሬኑን አንስታ አሰቀብራ ውጊያውን ቀጠለች…
በዚህ አይነት የአምስት አመት የአርበኝነት ትግል የኢጣሊያ ፋሸሽት ጦር አይቀሬውን የሽንፈት ፅዋ ጨለጠ።
ሚዚያ 27 ቀን በአዲስ አበባ የተለየ ድምቀት አየሩን ሞልቶታል። በአበበ አረጋይ የተመሩ 15 ሺህ ባለ ጎፈሬ አርበኞች እንዲሁም የወንድ ልብስ የታጠቁ መሳሪያ ያነገቡ እናት አርበኞች በሰልፍ ወደ አዲስ አበባ ገቡ። በሰንሰለት የታሰሩ ጣሊያን ምርኮኛችም ከሰልፉ ጋር ልህዝብ ታዩ። አርበኛቹን ተከትለው ጃንሆይ በጥቁር ሆነው ገቡ። የአዲስ አበባ ነዎሪዎች አረንጎዴ ቢጫ ቀዩን የኢትዮጵያ ሰንደቅ አላማ እያውለበለቡ ከግራና ቀኝ በመሆን ንጉሳቸውን ተቀበሉ።
አፄ ኃ/ሥላሴ ትልቁ የምኒሊክ ግቢ እንደደረሱ ለህዝቡ ንግግር አደረጉ። በንግግራቸውም  <<በዚህ ቀን በእርግጥም ኢትዮጵያ እጆቿን ወደ እግዚአብሔር ዘርግታለች>> ሲሉ ተደመጡ።
እንኳን የጀግኖች የአባት የአያቶቻችን የድል በአል  አደረሳቹ!!
 መልካም ያርበኞች ቀን!!!
Filed in: Amharic