>

ማነህ ባለ ሳምንት...???  (ዘመድኩን በቀለ)

ማነህ ባለ ሳምንት…??? 

ዘመድኩን በቀለ

• ኢንጂነር ስመኘው በቀለ … ኦርቶዶክስ ዐማራ 
• ዶር አምባቸው መኮንን … ኦርቶዶክስ ዐማራ 
• አቶ ምግባሩ ከበደ… ኦርቶዶክስ ዐማራ 
• አቶ እዘዝ ዋሴ… ኦርቶዶክስ ዐማራ 
• ብ/ጄኔራል አሳምነው ፅጌ… ኦርቶዶክስ ዐማራ 
• ሜ/ጄኔራል ሰዓረ መኮንን… ኦርቶዶክስ የወሎ ዐማራ 
• ጄነራል ገዛኢ አበራ … ኦርቶዶክስ ትግሬ
• ጋዜጠኛ ደምስ “ቬሮኒካ መላኩ”… ኦርቶዶክስ ዐማራ 
• ፋኖ አስቻለው ደሴ… ኦርቶዶክስ ዐማራ 
• ዛሬ ደግሞ ኮሎኔል አበረ አዳሙ… ኦርቶዶክስ ዐማራ እኒህ ሁሉ በዘመነ ዐቢይ አሕመድ የነውጥ ዘመን ከለውጡ ፍሬ ሳይቋደሱ በግፍ ተወግደዋል። ነፍስ ይማር !! 
… ይሄ ማለት እንግዲህ የባለ ሥልጣናቱ ሞት ብቻ ነው። እነሱም ቢሆኑ ሁሉም አልተጻፉም። በወለጋ፣ በመተከል፣ በሸዋ፣ በወሎ፣ በደቡብ፣ በኦሮሚያ፣ በአዲስ አበባና በትግራይ በጅምላ ተረሽነው በግሬደር ከሚቀበሩት በሺዎች ከሚቆጠሩት ዐማሮች እና ኦርቶዶክሳውያን ውጪ ነው። የዛሬ 15 ቀን ብቻ በሰሜን ሸዋ በጽዳት ሠራተኛው የዐቢይ አሕመድ መንግሥት ከ250 በላይ የሰሜን ሸዋ ዐማሮች በአንድ ጀምበር እንዲታረዱ ተደርገዋል። የአጣዬ እና ካራቆሬ ከተሞችም ወደ ፍርስራሽ አመድነትም መቀየራቸው ይታወሳል።
… ዐማራን መግደላቸው ብቻ ሳይሆን ዐማራው ከሞተም፣ ከገደሉትም በኋላ ለሌላ ተጨማሪ የሴራ ቦለጢቃ ማዘጋጀታቸው ነው የሚያስቀኝ። ጎጃም… ጎንደር… ወሎ… ሸዋ… እያሉ መልሰው ሊጫወቱበትም ይፈልጋሉ። ገድለውት ገዳዩን እዚያው በጎጥ ይመድቡለታል። ወዳጄ አትስማቸው። በርም አትከፈትላቸው።
… አክቲቪስት ስዩም ተሾመ የዐቢይ አሕመድን ብልጥግና ወክሎ፣ አክቲቪስት ናትናኤል መኮንን ደግሞ የብሬን ኢዜማን ወክሎ የወዳጃቸው የአበረ አዳሙን መነሣት ምክንያት በማድረግ የሆነ ፍንጭ የሰጡን በዚሁ ባሳለፍነው ሳምንት ነው። ቀኑ ነው እንጂ የማይታወቀው የሚወገዱ እንደሚኖሩ ፍንጭ ሰጥተውንም ነበር። አክ’ እንትቪስቶቹ።
… ጥያቄው ይቀጥላል… ነገስ ተገዳይ ተረኛው ማንይሆን? ማነው ባለሳምንት?
Filed in: Amharic