>

ከአዲስ አበባ ውጭ ለመጡ ወጣቶች በገፍ የምርጫ ካርድ እየተሰጠ ነው...!!!    (ጌጥዬ ያለው)        

ከአዲስ አበባ ውጭ ለመጡ ወጣቶች በገፍ የምርጫ ካርድ እየተሰጠ ነው…!!! 

  ጌጥዬ ያለው 

በአዲስ አበባ፤ ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ 12 የመራጮች መመዝገቢያ ጣቢያ 17 ላይ ከአዲስ አበባ ውጭ በገፍ ለመጡ ወጣቶች በሕገ ወጥ ሂደት የመራጮች ካርድ እየታደለ መሆኑን የባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ (ባልደራስ) የምርጫ ጣቢያዎች የክትትል ቡድን አስታውቋል።
ክስተቱን በምስል ለመቅረፅ የሞከሩት የባልደራስ የአካባቢው ተወካይ አቶ አንተነህ ደሳለኝ በፖሊስ ታስረዋል።
ወጣቶቹ የመጡት ኮድ 3፡27401 ኦሮሚያ በሆነ አይሱዙ ተሽከርካሪ ተሳፍረው ነው። የታርጋ ቁጥሩ ኮድ 4፡03548 የሆነ ፒካፕ የመንግሥት ተሽከርካሪ ደግሞ አይሱዙውን እያጀበ የምርጫ ጣቢያው ድረስ አድርሷቸዋል
የአካባቢው ኗሪዎች ወጣቶችን እንደማያውቋቸውና እንግዳ እንደሆኑም ተናግረዋል።
በተያያዘ ዜና በከተማዋ ለሚገኙ የጎዳና ተዳዳሪዎች ያለ አንዳች ቅድመ ሁኔታ የኗሪነት መታወቂያዎች እየታደሉ ነው። የቤት ቁጥርና መሰል መስፈርቶችን ሳይጠየቁ ነው መታወቂያ እየታደሉ ያለው። እደላው በምርጫ እንዲሳተፉ በሚል ከበላይ አካል በመጣ ትዕዛዝ እንደሆነ ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈለጉ የወሳኝ ኩነት ምዝገባ ኤጀንሲ ባለሙያ ተናግረዋል።
 ይህ የሆነው የአማራ ተወላጅ የጎዳና ተዳዳሪዎች ተመርጠው በኮሮና መከላከል ሰበብ ወደ ባሕር ዳር ከተሸኙ ከወራት በኋላ ነው።
Filed in: Amharic