>

አደባባያችንን አትንኩ! (ብፁዕ አቡነ ያሬድ የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት ዋና ሥራ አስኪያጅ)

አደባባያችንን አትንኩ! 

የቤተክርስቲያን ድምጿ ይሰማ!

  ብፁዕ አቡነ ያሬድ የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት ዋና ሥራ አስኪያጅ

 

ብፁዕነታቸው ዛሬ ለአዲስ አበባ  መስተዳድር የሰላምና ደኅንነት ቢሮ በጻፉት ደብዳቤ ሙስሊም ወንድሞቻችን ከዚህ ቀደም አፍጥርን በስታዲየም ሲያከብሩ መቆየታቸው እየታወቀ ዛሬ በመስቀል አደባባይ እንዲከበር መፍቀድ ተከባብሮ የኖረውን ክርስቲያኑን እና ሙስሊሙን ማኅበረሰብ ወደ አላስፈላጊ ግጭት የሚገፋ ተግባር መሆኑን ፈቃድ ሰጭው አካል እንዲያጤነው አሳስበዋል። ሊቀ ጳጳሱ በደብዳቤያቸው ለሙስሊሙ ማኅበረሰብ ያላቸውን አክብሮት ገልጸው የአፍጥር ዝግጅቱም ሆነ ዒድ አልፈጥር በዓል ግን በተለመደው ስታዲዬም እንጂ በመስቀል አደባባይ መከበር እንደሌለበት በአንክሮ አሳስበዋል።
መስቀል አደባባይ የቤተክርስቲያን የአምልኮት ሥርዓት መፈጸሚያ ነው። የቦታው ታሪካዊ እና ትውፊታዊ ባለቤትም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ናት ። እስከዛሬ የሌላ ሃይማኖት የአምልኮት ሥርዓት አልተፈፀመበትም ። የሃይማኖታዊ በዓላት ማክበሪያ ቦታችንን እያነሱ ለሌላው መስጠት ጠብ አጫሪነት ነው።

መስቀል አደባባይ ላይ ሙስሊሙ እንዳያፈጥር ችግር እየፈጠሩ ያሉት እነ ሙጅብ ናቸው…!!!

ጌታቸው ሽፈራው

አጀንዳው የማፍጠር ሳይሆን ስም ይቀየርልን “ኢድ አደባባይ ” ይባልልን ነው!
በዚህ የተቀደሰ ወር ክርስትያኖች ከሙስሊም ወገኖቻቸው ጋር በአፍጥር ሰዓት አብረው ነው የሚያሳልፉት። ደስስ ብሏቸው። ቄሶች ሳይቀሩ ተገኝተው አይተናል። ግን ለዚህ ደንቃራ እየሆኑ ያሉት እንደ ሙጅብ ያሉት የእምነት ግጭት ፈጥረው እስካሁን ያልተሳከላቸውን ማሳካት የሚፈልጉ ናቸው።
 አደባባይ ላይ ማፍጠሩ ምንም ሊያጨቃጭቅ አይችልም ነበር።  ይህ እንዳይሆን ከበስተጀርባ ሌላ የግጭት አጀንዳ ይዘው እየመጡ ያሉት እንደዚህ ያሉት በዚህ ቅዱስ ወር ግጭት የሚፈልጉ ናቸው። ተመልከቱ። ብቻውን ነው ይሄን የሚለው። ሌሎቹ እምነታቸው ላይ ናቸው። ከስግደቱ፣ ከፆሙ የበለጠበት ስም ይቀየርልኝ የሚለው አጀንዳው ነው።
ይሄ  የግጭት ጠማቂ የሚለው መስቀል አደባባይ ላይ እናፍጥር አይደለም። ስሙ ይቀየርልን ነው የሚለው። ሙስሊሙ አደባባይ ላይ ላፍጥር ሲል፣ ይሄ ክፉ ክርስትያኑም ጭምር አብሮ ተገኝቶ አደባባይ ላይ ከወገኖቹ ጋር እንዳያፈጥር ስም ይቀየርኝ እያለ ሌላ መጨቃጨቂያ አጀንዳ ያመጣል። ይህን አጀንዳ የጎተተው ዛሬ አይደለም። ወደኋላ ሄዳችሁ ፅሁፎቹን ተመክቱ።
ይህን አይነት ግጭት ቀስቃሽ መጀመርያ መቃወም ያለበት ሙስሊሙ ነው። ይህ ሰው መስቀል አደባባይ ላይ ሙስሊሙ እንዲያፈጥር አይፈልግም። የሚፈልገው በጭቅጭቅ እንዲቀር ነው። ከዛ እምነቶች መካከል ቁርሾ እንዲፈጠር ነው። ከዛም የራሱን አጀንዳ ያስፈፅማል። ለዛም ነው ከማፍጠሩ ይልቅ ስሙ ይቀየር የሚለውን አስቀድሙ ያመጣው።
ክርስትያኑም ጭምር ሙስሊም ወገኖቹ አደባባይ ላይ እንዲያፈጥሩ ይፈልጋል። አብሯቸው መሆን ይፈልጋል። ግን እንደሙጅብ ያሉት የሚፈልጉት የአደባባይ ስም ለውጥ ነው። ይህን እንዴት ይደግፍ?
Filed in: Amharic