>
8:12 pm - Tuesday June 6, 2023

የቱ ነዉ አማራ? መለኪያዉስ ደም ነዉ ወይስ አስተሳሰብ? ( ሸንቁጥ አየለ)

የቱ ነዉ አማራ? መለኪያዉስ ደም ነዉ ወይስ አስተሳሰብ? 

ሸንቁጥ አየለ

1.ታዲዮስ ታንቱ
“አማራን በሀሰት መክሰስ ነዉር ነዉ። የአማራን ዘር ከኢትዮጵያ ለማጥፋት የሚሰራዉን ስራ ሁሉ እቃወማለሁ። የአማራ ህዝብ ለኢትዮጵያ ባለዉለታ እንጂ ሀሰተኞች እንደሚሉት የሌሎችን ባህል አላጠፋም። የሌሎችንም ቋንቋ አልተጋፋም። ከዚያ ይልቅ ፊደል አስተምሯል። ሀገር ጠብቋል።ስነጽሁፍ አሳዉቋል። ብዙዉን ከአረመኔነት ወደ መንፈሳዊ ሰዉነት መልሷል። አሁን ግን የአማራ ህዝብ ላይ ሀሰተኛ ትርክት ሲተረክ ያንን ሀሰት ልክ አይደለም ብሎ የሚናገር የለም። ወያኔ ያስተማረው ዉሸት እና ሃሰት ነዉና ስህተት የሆነን ነገር መቃወም እንደነዉር ይቆጠራል። የአማራን ህዝብ እየጨፈጨፉ የአርበኞች  በዓል እናከብራለን ማለት ዘበት ነዉ::የሀገር ጠባቂ የሆኑ: የፍትህ ቀንዲል የሆኑ ጀግኖች ያፈራዉን የአማራ  ህዝብ እንዲሁም የአርበኞች ምንጭ የሆነዉን:የጀግኖች ምንጭ የሆነዉን የአማራ ህዝብ እያጠፉ ስለ አርበኝነት ማዉራት በራሱ ታላቅ ስላቅ እና ዘበት ነዉ::” ጋሽ ታዲዮስ ታንቱ ናቸው እንዲህ ምርር ብለዉ መራራዉን እዉነት በአረመኔዎች በተወረረ መሬት ላይ ቆመዉ የተናገሩት።
እኝህ ሰዉ ነገራቸዉ ሁሉ ይደንቀኛል።ለእዉነት ብቻ የቆሙ ታላቅ ኢትዮጵያዊ ናቸዉ። እዉነት ዋጋ ያስከፍላል እና በአረመኔዎች እጅ ከዚህ ቀደም  ድብደባ እንደተደረገባቸዉ ይታወቃል። አሁንም እኝህ ሰዉ ላይ ብዙ ስቃይ እንደደረሰባቸዉ ይሰማል።
2.ብአዴናዊነትን/የአማራ ብልጽግናን የሚወክለዉ አበረ አዳሙ
————-
ከዚህ በተቃራኒዉ ” አማራ አማራ የሚሉትን አሳደን እናጠፋቸዋለን” ብሎ የተናገረዉ አበረ አዳሙ የተባለዉ አንዳንዶች “ዘሩ አማራ ነዉ” የሚሉት ሰዉ ነዉ። ይሄ ሰዉ ፋኖን ከአረመኔዎች ጋር ተባብሮ በማጥፋት ተወዳዳሪ የሌለዉ ስራ ሰርቷል። አስረሽኗቸዋል። አሳስሯቸዋል። ይሄ ሰዉ በደም እጁ ተለቃልቆ ከአረመኔዎች ጋር ቁጭ ብሎ ዉስኪ እየጠጣ : ጮማ እየቆረጠ አማሮች በወለጋ በመተከል እና በኦሮሚያ ሲታረዱ እሱ በተባባሪነት በዝምታ ዉስጥ ነበር። ይሄ ሰዉ ከኢዜማ/ግ7 ብርሃኑ ነጋ ጋር ተባብሮ የአማራ ህዝብ ተቆርቋሪዎችን በማሳደድ እና በማስገደል ብሎም በማሸማቀቅ ወደር ያልተገኘለት ደንቆሮ ነበር:: ይሄ ቁልፍ የአማራ ብልጽግና ሰዉ ከስልጣን ሲወርድ እና ሲገደል ግን ብዙ ” አማራ” ነን ባዮች ጮህዉለታል። ጀግናም አድርገዉታል። እነዚህ አይነት ሰዎች አንዳንዶቹ ሰፈራቸዉን እየቆጠሩ:አዳንዶቹም ጓደኝነታቸዉን እየቆጠሩ ብዙዎቹም እዚያዉ ቆሻሻዉ ብአዴንዉስጥ አብረዉ የተግማሙትን አማራን የማስረሸን ነገር እያሰቡ ብዙ ለፍልፈዉለታል:: አንዳንዶቹም ቆመዉ የትናንትን ሁኔታ እራሳቸዉን ሳይጠይቁ በስሜት ብዙ ለፍልፈዋል:: ለነገሩ ስሜታቸዉ ያቀበላቸዉን በህሊናቸዉ ሳያንሰላስሉ የሚጽፉ ብዙ የሚመስሉ ጥቂት ሰዎች ናቸዉ እንጅ የአማራስ ህዝብ እንደ ቅዱስ ዳዊት “ሀጢያተኛ ጠላቴን በሀጢያተኛ እጅ አጥፋልኝ” ብሎ የሚጽልይ መንፈሳዊ ህዝብ ነዉና እግዚአብሄር ጠላቱን በምንም መንገድ ሲያጠፋለት ዝም ብሎ የእግዚአብሄርን ነገር ያደንቃል።
እዉነት ነዉ ! እግዚአብሄር ገና ብዙ ፍርድ ይሰጣል።አረመኔዎች እርስ በርሳቸዉ ይጠፋፋሉ። ብልጽግና ዉስጥ የተሰባሰቡት በአማራ ህዝብ ደም የሚቆምሩት እርስ በርስ ይጠፋፋሉ።በኢትዮጵያ ላይ ቂም የያዙ የዉጭም የዉስጥም ጠላቶች ፡ በአማራ ህዝብ ላይ ቂም የያዙ የዉጭም የዉስጥም ጠላቶች፡ በራሳቸዉ ሰይፍ እና በራሳቸዉ ወጥመድ እንደ እናበረ አዳሙ በሌሎች ይጠፋሉ። እርስ በርስም ይጠፋሉ።አረመኔዎቹም ምድሪትን እንወርሳለን የእግዚአብሄርን መንፈስ እናረክሳለን ብለዉ ተነስተዋል እና ጠፊ ናቸዉ። እግዚአብሄር ተዋጊ ነዉና ሀያላን አስነስቶ ያጠፋቸዋል። እስከ ቀኑ ድረስ እንደ እነ ጋሼ ታዲዮስ ታንቱ አይነቶችን ምርጥ ኢትዮጵያዉያን እግዚአብሄር ይጠብቃቸዉ። እንደ እነ ጋሽ ታዲዮስ ታንቱ አይነት ድንቃ ቅንቅ ሰዎች ስለ እዉነት እየተሰዉ በሄዱ ቁጥር ግን እዉነት እራሷ እንደ ጸሀይ በኢትዮጵያ ሰማይ ላይ ፈንጥቃ ትወጣለች::የአማራን ህዝብ እናጠፋዋለን ያሉ የአማራ ጠላቶች በሀያሉ እግዚአብሄር ፈቃድ ከምድረ ገጽ እስከ አስተሳሰባቸዉ ላንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ተነቅለዉ ይጣላሉ::
ድምዳሜ
——-
ብአዴን/የአማራ ብልጽግና ዉስጥ የተወሸቁ እና የአማራ ህዝብ ሲያልቅ እንደ አበረ አዳሙ ሁሉ በተባባሪነት አፋቸዉን ዘግተዉ የተቀመጡት ሁሉ አማራ አይደሉም::እነዚህ ጸረ አማራ ናቸዉ::ሆኖም እነዚህ አይነት ባለስልጣናት እና ካድሬዎች ሲሞቱ የአማራ ህዝብ ተቆርቋሪ ሊያደርጓቸዉ የሚታትሩ ጎጠኞች ሞልተዋል::በግልጽ መታወቅ ያለበት እነዚህ ጎጠኞች እራሳቸዉ ጸረ አማራ መሆናቸዉ ነዉ::የነእሱ ሰዉ ሰፈር ሰዉ ብአዴን ዉስጥ ቦታ ሲያገኝ እና ሲያጣ እንደሁኔታዉ የአማራነት ሚዛናቸዉ:የእዉነት ሚዛናቸዉ የሚዋዥቅ ከንቱዎች ናቸዉ::ዛሬ አገኘሁ ተሻገር ተሾመልን ብለዉ ትናንት የአማራ ብሄረተኛ ነን ይሉ የነበሩ ዛሬ የኦነጋዉያን/ኦህዴዳዉያንን ዉስኪ አጣጭ/ጮማ አቋራጭ ሆነዋል::የአማራ ህዝብ ላይ የሚደረገዉን ቁማር በደም እጃቸዉ አቡኪ ሆነዋል::እንዴዉም የአበረ አዳሙ ጎጥ እና የአገኘሁ ተሻገር ጎጥ ተቆጥሮ አበረን አገኘሁ ገደለዉ የሚሉ እና የለም አበረን አገኘሁ አልገደለዉም የሚሉ ምናንምንቴ የአማራ ብሄረተኛ ነኝ ባዮች ተነስተዋል:: እነዚህ ሰዎች ጭንቅላታቸዉ በብአዴን/የአማራ ብልጽግና የተነጠቀ  ምናምንቴዎች ናቸዉ::ይባስ ብለዉም የአበረ አዳሙ ሞት የአማራን ህብረት ያላላዋል የሚሉም ተነስተዋል::ብአዴንን እንደ አማራ የሚቆጥሩ እራሳቸዉ ጸረ አማራ ናቸዉ::ሁሉም አንድ በአንድ ይገለጣል::
 “አማራ ተከቧል::ከ500 አመት በፊት ከነበረዉ ሁኔታ በባሰ ሁኔታ አረመኔዎች አማራን ሊያጠፉት ተነስተዋል” ብሎ እዉነቱን ቁልጭ አድርጎ አደባባይ የተናገረዉን አሳምነዉ ጽጌን አስገድሎ ሲያበቃ “አማራ አማራ እሚሉትን አሳደን እናጠፋቸዋለን” ሲል የፎከረዉ አበረ አዳሙ ነዉ:: ይሄን ንግግር ከቶስ እንዴት መርሳት ይቻላል? ከቶስ አበረ አዳሙ አማራ ሆኖ ነዉ ዛሬ አበረ አዳሙን የአማራ ጀግና ለማድረግ ብዙዎች የሚጋጋጡት?
እና አማራ ማን ነዉ? አማራዉ እማ እንደ ጋሽ ታዲዮስ ታንቱ አይነት እዉነት እና እነጻነት ሚዛን ላይ የቆመ ሰዉ ነዉ::አምሀራ ከነገዳዊ ማንነት በዘለለ እዉነት: ነጻነት እና መንፈሳዊ መሰረት ላይ የቆመ ማንንነት ጭምር ስለሆነ ምንም እንኳን ጋሽ ታዲዮስ ታንቱ በነገዳቸዉ ወላይታ ቢሆኑም እዉነት ሚዛን ላይ ቆመዉ የአማራ ህዝብ ላይ የታወጀዉን የዘር ማጥፋት ወንጀል ፊት ለፊት የተጋፈጡ የእዉነት ሰዉ ናቸው::
አማራነት በነገድህ እንደ ፕሮፌሰረ አስራት አማራ ሆነህ የአማራ ነገድህ በሀሰት ሲሳደድ እዉነት ፊት መቆም ነዉ::አማራነት እንደ ታዲዮስ ታንቱ በነገድህ ወላይታ ሆነህ በአማራ ህዝብ ላይ የታወጀዉን የዘር ማጥፋት እና ሀሳተኛ ትርክትን ፊት ለፊት ማምከን ነዉ::
እንዲህ እንደ ሁለቱ ድንቅ ሰዎች ለእዉነት ስትቆም ብቻ ወደ ኢትዮጵያዊነት ማማ ላይ የተሳፈርክ ኢትዮጵያዊ ሰዉ ትሆናለህ::እዉነት:ነጻነት እና ሰብአዊ ልእልና ላይ የደረሱት ልበ ሙሉዉ ታዲዮስ ታንቱ የዘር ማጥፋት አዋጅ ስለታወጀበት አማራ ፊት ለፊት ተጋፍጠዋል እና በታሪክ ፊት ለሳቸዉ ብቻ ሳይሆን ለወጡበት ማህበረሰብም ታላቅ የኩራት ምንጭ እንዲሁም ለኢትዮጵያዊነትም አንድ ምሰሶ ሆነዉ ይቆማሉ::
እግዚአብሄር ኢትዮጵያን ይባካት ! የዋህ ህዝቧንም ይጠብቅ !
የኢትዮጵያን የመከራ ዘመንም በፍጥነት ያሳልፈዉ ! ያሳልፈዋልም !
Filed in: Amharic