>

ዩቱብ ላይ ተጥደው የሚውሉት የኦሮሙማ ኮተቶች ነገር. . .   (አቻምየለህ ታምሩ)

ዩቱብ ላይ ተጥደው የሚውሉት የኦሮሙማ ኮተቶች ነገር. . 

አቻምየለህ ታምሩ

ዩቱብ ላይ ተጥደው የሚውሉ የኦሮሙማ ኮተቶች የእውቀት ጾመኞች ስለሆኑ አጥንተውት ቀርቶ አንብበው ሊረዱት ስለማይችሉት የአባ ባሕርይን “ዜናሁ ለጋ*” ጽሑፍ ሲባል የሰሙትን የስድብ አይነት ሁሉ እየደገሙ ተረት ተረት የሆነ፣ እኔና መሰል ሰዎች ብቻ የምንጠቅሰው ድርሰትና ለምንጭነት የማይበቃ ጽሑፍ መሆኑን ሊነግሩን አዲስ ዘመቻ ከፍተዋል።
እነዚህ የኦሮሙማ ኮተቶች ድፍረት እንጂ እውቀት ስለሌላቸው የኦሮሞ ብሔርተኞች ሁሉ ከፕሮፈሰር መሐመድ ሐሰን፣ ዶክተር ነጋሶ ጊዳዳ፣ ፕሮፈሰር ተሰማ ተዓ፣ ዶክተር ጉሉማ ገመዳ፣ ፕሮፈሰር ሕዝቅኤል ጊቢሳ፣ ወዘተ ጀምሮ በአውሮፓና በአሜሪካን ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ የኦሮሞን ታሪክ አጠናን  የሚሉት የኦሮሞ ብሔርተኛ ዶክተርና ፕሮፈሰር ሁሉ ከመጀመሪያ እስከ ዶክትሬት ዲግሪ ድረስ የሚያቀርቧቸውን የመመረቂያ ወረቀታቸውን የጻፉት እና ዶክተርና ፕሮፌሰር ለመባል የበቁት የኦሮሞ ታሪክ ብቸኛ የጽሑፍ ምንጭ የሆነውን የአባ ባሕርይን “ዜናሁ ለጋ*” ጽሑፍ እስከቻሉት ድረስ ዝቀው መበጥቀው መሆኑን አያውቁም።
ከመጀመሪያ እስከ ዶክትሬት ዲግሪ ማሟያ ጥናቱ ድረስ የአባ ባሕርይን “ዜናሁ ለጋ*”ን እስኪቻለው በመዛቅ ያጣቀሰውና በኦሮሞ ብሔርተኞች ዘንድ እንደ ቁጥር አንድ የኦሮሞ የታሪክ አጥኚ የሚታየው የኦሮሞ ብሔርተኛው ፕሮፈሰር መሐመድ ሐሰን የአባ ባሕርይ “ዜናሁ ለጋ*” ጽሑፍ ለኦሮሞ ታሪክ ያለውን አስተዋጻኦ በሚመለከት ባሳተመው ወረቀት የአባ ባሕርይ ዜናሁ ለጋ* ጽሑፍ ኦሮሞ የጽሑፍ ታሪክ እንዲኖረው ያስቻለ መሆኑን፤ አባ ባሕርይም የምሑር ቁንጮ እንደነበሩ መመስከሩን የአባ ባሕርይን ጽሑፍ በመጥቀሳችን ሲረግሙን የሚውሉት የኦሮሙማ ኮልኮሌዎች አያውቁም!
ምን ይኼ ብቻ! አዲስ አበባ ከተማ የተገነባው “የኦሮሞ ባሕል ማዕከል” ውስጥ የምናገኛቸው የኦሮሞ መገልገያዎችና ልዩልዩ ስያሜዎች፤ በዚህ ሳምንት አዲስ አበባ ውስጥ እየተከበረ ነው በሚባለው “የኢትዮጵያ ሳምንት” አዉደ ርዕይ ላይ “የኦሮሚያ ቡድን” የተባለው ስብስብ  ያቀረባቸው ትዕይንትና የኦሮሞ መገለጫዎች ተደርገው የቀረቡት በሙሉ አባ ባሕርይ ከጻፉት ባሕርይ “ዜናሁ ለጋ*” የተወሰዱ ናቸው። ከሶስት ዓመታት በፊት በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ስም ዐቢይ አሕመድና ለማ መገርሳ  ለኦሮሞ ጥናት አደረገ ባሉት አስተዋጻኦ የክብር ዶክትሬት ዲግሪ የሰጡት ኤርትራዊው ፕሮፈሰር አስመሮም ለገሰም ቢሆን የኦሮሞን ታሪክ የጻፈው የአባ ባሕርይን  ዜናሁ ለጋ* ጽሑፍ የቻለው ያህል ዝቆ ወደ እንግሊዝኛ በመተርጎም ነበር። ደፋሮቹ የኦሮሙማ የዩቱብ ኮተቶች ይህንን ሁሉ አያውቁም!
ፕሮፈሰር አስመሮም ለገሰ ራሱ እ.ኤ.አ. በ1973 ዓ.ም.  ለዶክትሬት ዲግሪው ማሟያ  “Gada: three approaches to the study of African society” በሚል ርዕስ ባቀረበው ጽሑፉ ይህን አውስቷል።  የአባ ባሕርይን “ዜናሁ ለጋ*” የቻለውን ያህል በመዛቅ የዶክትሬት ዲግሪውን ያገኘውና ለዚህ ስራው ዐቢይ አሕመድና ለማ መገርሳ የክብር ዶክትሬት የሰጡት ፕሮፌሰር አስመሮም ለገሰም ሆነ ፕሮፌሰር መሐመድ ሐሰን ለሽያጭ ያቀረቧቸው የኦሮሞ ታሪክ ጥናት መጽሐፍቶቻቸውና በኦሮሞ ታሪክ ዙሪያ ያሳተሟቸው አርቲክሎቹ ሁሉ ቀዳሚና ዋና ምንጭ አባ ባሕርይ በ16ኛው መቶ ክፍለ ዘመን የጻፉት «ዜናሁ ለጋ*» ነው!
ባጭሩ የኦሮሞ ታሪክ አጥኝ ሆኖ የአባ ባሕርይን “ዜናሁ ለጋ*” እስኪበቃው ድረስ በመዛቅ ያላጣቀሰ አንድም የኦሮሞ ተወላጅ የታሪክ ዶክተርና ፕሮፈሰር ማቅረብ አይቻልም።
እንግዲህ! ዩቱብ ላይ ተጠምደው በሚውሉ የኦሮሙማ ኮተቶች ዘንድ ጥፋት የሚሆነው ይህ የኦሮሞ ዶክተሮችና ፕሮፌሰሮች ሁሉ የቻሉትን ያህል ዝቀው ያጣቀሱት የአባ ባሕርይ “ዜናሁ ለጋ*” ጽሑፍ በእኔና መሰል ሰዎች ሲጠቀስ ብቻ ነው። እነዚህን ማይምነት በሚሰጠው ድፍረት የሚመኩ  የኦሮሙማ ኮተቶች ሲባል የሰሙትን ከመድገም ውጭ ማሰብ የሚጠይቅ እውቀት ስለሌላቸው ሲባል ከሰሙት የሚደግሙትንና ኦሮሞ በአለም ቅርስነት የተመዘገበና ሙዚየም የቆመለት መገልገያ፣ ስያሜ፣ ባሕል፣ አደረጃጀትና አኗኗር አለብ ብለው ሊነግሩን የሚቃጣቸው ነገር ሁሉ  ተመዝግቦ የሚገኘው እኛን ለምን ጠቀሳችሁት እያሉ ላንቃቸው እስኪሰነጠቅ ድረስ በመጮህ ሲሰድቡበት በሚውሉት የአባ ባሕርይ ዜናሁ ለጋ* ውስጥ መሆኑን በማስታወስ ለመሞገት አልደክምም!
ጉብዝና ማለት ተደብቆ ሲሳደቡ መዋል፣ ዩቱብ ከፍቶ ባለጌውን ፍቶ እየለቀቁ እኛን ማሰደብ፣  ለብቻ ሆኖ ቡራ ከረዩ ሲሉ መታየትና በአፍ ነጠቅነት ሲባል የሰሙትን ሁሉ ያሳጣሩ ሲደግሙ ውሎ ማደር ሳይሆን እያንዳንዷን የጻፍናትን ታሪክና የሰጠናትን አስተያየት በሚመለከት እኛን የጽሑፉንና የሀሳቡን ባለቤቶች ባንድ ወገን፤ በኛ ጽሑፍና ሀሳብ የማይስማሙትን [ከቻለ ራሱ፤ ካልቻለ ሌላ የሚችል በመጋበዝ] ደግሞ በሌላ ወገን አድርጎ በኛ ጽሑፍና ሀሳብና  ዙሪያ በማስረጃ  ላይ የተመሰረተ ሙግትና ስርዓት የተላበሰ ክርክር ማድረግ ነው።
እኔ በበኩሌ እኔ በምጽፈው ታሪክና በምሰጠው አስተያየት ዙሪያ የማይስማማ ሰው ቢኖር በየትኛውም መድረክ ላይ ቀርቤ ከዚያ ሰው ጋር ለመሟገትና ክርክር ለማድረግ በማንኛውም ሰዓት ዝግጁ ነኝ!  ድብቅ የፖለቲካ ፍላጎት ያላቸው ሰዎች ግን የጻፉትን የፈጠራ ታሪክ እንዲከላከሉ ለሙግት ሲጋበዙ ውሸታቸው እንደሚጋለጥና የሚቀርብባቸውን ትችት እንደማይቋቋሙ ስለሚያውቁት አለም አጫዋቾችንና ሳቅና ምናንም ሲሉ የሚሉ አውደልዳዮችን እያሰማሩ እኛን ያሰድባሉ እንጂ  እነሱ ደፍረው የጻፉትን  ለመከላከልና የፊት ለፊት ሙግት ለማድረግ ወደ መድረክ አይወጡም። ይታያችሁ! የሚያሰማሩብን ለማሰብ ፍቃደኛ ያልሆነው ተከታያቸው እንደወረደ ሳያጣራ የሚቀበለውና እኛን ሲሳደብ የሚውለው የትርክቱ ዋነኛ ፈጣሪዎች በአደባባይ ቀርበው ሊከላከሉት የማይደፍሩትን የፈጠራ ትርክታቸውን ነው።
ከቻች የታተመው የቪዲዮ ማስረጃ  በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ስም ዐቢይ አሕመድና ለማ መገርሳ  ለኦሮሞ ጥናት አደረገ ባሉት አስተዋጻኦ የክብር ዶክትሬት ዲግሪ የሰጡት ኤርትራዊው ፕሮፈሰር አስመሮም ለገሰ የክብር ዶክትሬቱን ለመሸለም ከሶስት ዓመታት በፊት አዲስ አበባ በመጣበት የኦሮሞ ብልጽግና ልሳን ከሆነው OBN Afaan Oromoo  ጋር ያደረገው ቃለ ምልልስ ነው። በኦሮሞ ጥናት መስክ  አደረገ ለተባለው አስተዋጻኦ በነ ዐቢይ አሕመድ የክብር ዶክትሬት የተሰጠው ፕሮፈሰር አስመሮም ስለ አባ ባሕርይ ዜናሁ ለጋ* እና ስለ ኦሮሞ ወረራ የተናገረውን አስተያየት ሙሉውን አዳምጡና የአባ ባሕርይን ዜናሁ ለጋ* በማጣቀሳችን የውሸት ታሪክ እንደምናቀርብ አድርገው ሲሳደቡ ስለሚውሉ የኦሮሙማ ኮተቶች፤ እነዚህ ኮተቶች ላንቃቸውን በከፈቱ ቁጥር ሲያሳስቱት ለሚውለት ለማሰብ ፍቃደኛ ላልሆነውና እውነትና ውሸትን መለየት ስለማይችለው ተከታያቸው እዘኑለት!
የግርጌ ማስታወሻ፤ 
ፕሮፈሰር አስመሮም በንግግሩ “ፈላሲ” ሲል የተጠቀመው ቃል የትግርኛ ቃል ሲሆን የቃሉ አማርኛ ትርጉም መነኩሴ ማለት ነው።
Filed in: Amharic