>

ዐብይ አሕመድና የኢትዮጵያ ወንጌላውያን! (መስፍን አረጋ)

ዐብይ አሕመድና የኢትዮጵያ ወንጌላውያን!

 

መስፍን አረጋ


“You can fool all people some of the time, and some people all of the time, but you cannot full all people all the time.”

“ሁሉንም ሰወች ለተወሰነ ጊዜ፣ የተወሰኑ ሰወችን ለሁል ጊዜ ማሞኘት ቢቻልም፣ ሁሉንም ሰወች ሁል ጊዜ ማሞኘት ግን አይቻልም፡፡”   ለአብራሃም ሊንከልን የተነየተ (Attributed to Abraham Lincoln)

ዐብይ አሕመድ ከሞላ ጎደል ሁላችንንም ኢትዮጵያውያን ለተወሰነ ጊዜ ማሞኘት ብቻ ሳይሆን በደንብ አጃጅሎናል፡፡  በደንብ ሊያጃጅለን የቻለው ደግሞ የደደቢቱ ወያኔ ኢትዮጵያ የሚለውን የምናፈቅረውን ቃል ለሃያ ሰባት ዓመታት ሲስቅበትና ሲሳለቅበት ስለኖረ፣ ለይምሰል ያህል ቢሆንም እንኳን የኢትዮጵያን ስም በክብር የሚያነሳ ባለስልጣን ለማየት አጥብቀን እንመኝ ስለነበር ነው፡፡  በሌላ አባባል፣ የደደቢቱ ወያኔ ኢትዮጵያን ክፉኛ በማዋረዱ ምክኒያት አንጀታችን ክፉኛ ስለቆሰለ፣ የምንወዳትን ኢትዮጵያን ባይወዳትም እንኳን እወዳታለሁ እያለ የሚዋሸን ባለስልጣን ለማየት እንቋምጥ ነበር፡፡  ይሄን ድክመታችንን በደንብ የተረዳው ጮሌው (street smart) ዐብይ አሕመድ ደግሞ በዚህ ድከመታችን በደንብ ገብቶ በደንብ ስላነሆለለን፣ ዐብይ አሕመድ ማለት ኢትዮጵያና ኢትዮጵያውያን ለረዥም ጊዜ በተስፋ ሲጠባበቁት የነበረው መሲህ ነው እስከማለት ደረስን፡፡  

ብልጣብልጡ ዐብይ አሕመድ ያልተረዳው ትልቁ ቁምነገር ግን ሁላችንንም ጦቢያውያን ሁልጊዜ ሊያሞኘን አለመቻሉን ነው፣ ብልጣብልጥነት የሚያዋጣው እስከተወሰነ ደረጃ ብቻ ነውና፣ እጅግም ስለት አፎት ይቀዳልና፡፡ 

  • ዐብይ አሕመድ ማለት በጦቢያ ፍርስራሽ ላይ የኦሮሞን አጼጌ (Oromo empire) ለመገንባት የማይፈነቅለው ዲነጋ የሌለ፣ የኢትዮጵያን ለምድ የለበሰ የኦነግ ተኩላ መሆኑ ይበልጥና ይበልጥ ግልጽ እየሆነ መጥቷል፡፡  
  • ኢትዮጵያን ባሸብራቂ ቃሎች የሚያሽሞነሙነው፣ በኢትዮጵያ ላይ የሚፈጽመውን ኦነጋዊ ደባ ለመሸፋፈን ሲል ብቻ እንደሆነ ተነቅቶበታል፡፡  
  • ኢትዮጵያን እያፈራረሰ ያለው እሱ ራሱ መሆኑን ኢትዮጵያውያን ስለሚያውቁ (በጥላቻ የተመረዙ ጭራቃዊ መንጋወቹን አንገቶችን እንዲመተሩ፣ ማሕጸኖችን እንዲዘረከቱ፣ ሽሎችን እንዲቦጫጭቁ፣  ሕጻናትን ቤት ዘግተው እንዲያንጨረጭሩ፣ ከተሞችን ሙሉ በሙሉ እንዲያወድሙ ካመቻቸላቸው በኋላ) “ኢትዮጵያ አትፈርስም” እያለ ሲፎትታቸው፣ እንደ ማሽላ እያረሩ በምጸት ይስቁበታል፡፡  
  • ዝንቤን እሽ ብትሉ መቶ ሺወቻችሁ ባንድ ጀንበር ትታረዳላችሁ በማለት አሰቃቂ ዛቻ በግልጽ ሊዝት የቻለው፣ በሱ በራሱ በቀጥታ የሚታዘዝና ትዛዙን ለመቀበል ሁልጊዜም በተጠንቀቅ የሚጠባበቅ፣ እረድ ያለውን ሁሉ ለማረድ ቅንጣት የማያቅማማ፣ ሜንጫውን እያብለጨለጨ የሚወነውን፣ ተወርዋሪ አራጅ ሚሊሻ ስላዘጋጀ ብቻ መሆኑን ኢትዮጵያውያን ያውቃሉ፡፡  
  • በሱ ዘመን ባማራ ሕዝብ ላይ ተቆጥረው የማይዘለቁ ሰቅጣጭ ጭፍጨፋወች ቢፈጸሙም፣ አንድ ጊዜም እንኳን በጭፍጨፋው ማዘኑን (ለይምሰል ያህል እንኳን) አልገለጸም፡፡  ይህ በግልጽ የሚያሳየው የዐብይ አሕመድ አረመኔነት ወደር እንደሌለው፣ ለአማራ ሕዝብ ያለው ጥላቻና ንቀት ምን ያህል እንደሆነ፣ የሰባተኛው ንጉስ ትዕቢት ሰባተኛው ሰማይ እንደደረሰና፣ ስለዚህም ውድቀቱ እንደተቃረበ ነው፣ ትዕቢት የውድቀት መጀመርያ ናትና (መጽሐፈ ምሳሌ 16፡18)፡፡  
  • አፍንጫው ሥር በተፈጸሙትና በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ተጠያቄ በሆነባቸው አሰቃቂ ዘር ተኮር ጭፍጨፋወች ተወንጅሎ ለፍርድ የሚቀርብበት ቀን ኢትዮጵያውያን በጉጉት ይጠብቁታል፡፡  ፍርድ ቤቱ ደግሞ ወንጀሉን በፈጸመባትና ባስፈጸመባት በራሷ በጦቢያ ውስጥ እንጅ፣ (ወያኔን፣ ኦነግንና የመሳሰሉትን አፍሪቃዊ ጎጠኞችን እያበረታቱ፣ የጎጠኝነት ሰለባ ለሆኑት አፍሪቃውያን ያዞ እንባ በሚያነቡት) ባውሮጳ አገሮቸ ውስጥ ባይሆን ይመረጣል፡፡  ዳኞቹ ደግሞ የወንጀሉ ሰለባወች የሆኑት ኢትዮጵያውያን እንጅ፣ ኖቤል የሸለሙት አውሮጳውያን ሊሆኑ አይገባም፡፡   

የዐብይ አሕመድን ፀረጦቢያ ኦነጋዊነት ቁልጭ አድርገው የሚያሳዩ፣ ሊስተባበሉ የማይችሉ አያሌ ሐቆች በየጊዜው ቢፈርጡም፣ የተወሰኑ ጦቢያውያን ግን ዓይኔን ግንባር ያርገው በማለት በዐብይ አሕመድ ሁልጊዜ መሞኘትን የመረጡ ይመስላሉ፡፡  የዐብይ አሕመድ አፍና ምግባር ፍየል ወዲያ ቅዝምዝም ወዲሁ መሆናቸው አገር ያወቀው ፀሐይ የሞቀው ገሀድ ሐቅ ቢሆንም፣ ለነሱ ግን አይታያቸውም፣ ይልቁንም ደግሞ እንዲታያቸው አይፈልጉም፡፡  ዐብይ አሕመድ
ዐሊ የአነጉ ኦቦ፣ አፉና ምግባሩ ሐራምባና ቆቦ መባሉ አግባብ አይመስላቸውም፡፡   የዐብይ አህመድን ፀረጦቢያ አረመኔያዊ ድርጊቶች አይተው እንዳላዩ በመሆን፣ በዐብይ አሕመድ ሰናይ ንግግሮች ላይ ብቻ እያተኮሩ፣ በነዚህ ባዶ ንግግሮች ላይ በመመርኮዝ ብቻ የኢትዮጵያ ቤዛ ይሉታል፡፡  ዐብይ አህመድ በርግጥም ቤዛ ከሆነ፣ ቤዛነቱ ለኦሮምያ እንጅ ለኢትዮጵያ አለመሆኑን ሊያስረዳቸው ለሚሞክር ሁሉ ጀሮ ዳባ ልበስ ይላሉ፡፡  ዐብይ አሕመድ (ዕጹብ የማታለል ክሂሎቱን በመጠቀም ብቻ) በሦስት ዓመት የስልጣን ዘመኑ ለኦሮሙማ የሠራው፣ የኦሮሞ ጽንፈኞች በመቶ ዓመታት እንሠራዋለን ብለው ከሚያልሙት በላይ እንደሆነ አልተገነዘቡም ወይም ደግሞ መገንዘብ አይፈልጉም፡፡  

በዐብይ አሕመድ ሁልጊዜ መሞኘትን ምርጫቸው ያደረጉ ከሚመስሉ ቡድኖች ውስጥ ዋናወቹ የኢትዮጵያ ወንጌላውያን ናቸው፡፡  ስለዚህም፣ የሚከተለውን ጥያቄ መጠየቅ ግድ ይላል፡፡  ባብዛኛው አገር ወዳድ የሆኑት እነዚህ የኢትዮጵያ ወንጌላውያን፣ የሚወዷትን አገራቸውን ሙሉ በሙሉ ሊያጠፋ ለተነሳ፣ ዐብይ አሕመድ ለተባለ ኦነጋዊ ሰይጣን ሙሉ ድጋፋቸውን ለመስጠት ለምን መረጡ?  ለምን እንደመረጡ እንመልከት፡፡

የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተክርስትያን መካነ እየሱስ (Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus) በሚል ስያሜ ወንጌላዊነትን በጦቢያ ላይ በ1950ወቹ የዘሩት ጉዲና ቱምሳን የመሳሰሉ ቀንደኛ ኦነጋውያን ነበሩ፡፡ ለወንጌላዊነት ምሥረታ ከፍተኛውን እገዛ ያደረጉት ደግሞ የሉተራን (Lutheran) እና ፕሬስቢቴርያን (Presbyterian) ሚሲዮኖች ነበሩ፡፡  እነዚህ ሚሲዮኖች ወደ ጦቢያ የተላኩት ደግሞ የሮማን ፕሮቻዝካን (Roman Prochazka) ጦቢያን በጎጥ የማፈራረስ ዓላማ ለመተግበር ነበር:: 

The numerous tribes who inhabit the Ethiopian state are being forcibly kept from European colonialism by Abyssinian rulers whose aim is to act as champions of all black people so as to attack and destroy Western culture”

የጦቢያን አያሌ ብሔረሰቦች የነጭ ባርያ የመሆን ምርጫ የነፈጓቸው፣ ዓላማቸው በነጭ የባህል (እና የሐይማኖት) ወረራ መቃብር ላይ የመላው ጥቁር ሕዝብን ልዕልና መገንባት የሆነው የሐበሻ መሪወች ናቸው፡፡  Roman Prochazka (Abyssinia: The Powder Barrel, Vienna, 1935)

ስለዚህም ከኢትዮጵያ ወንጌላውያን መሪወች ውስጥ አብዛኞቹ ጽንፈኛ ኦነጋውያን ቢሆኑ አያስገርምም፡፡ በመሆናቸውም እነዚህ የወንጌላውያን መሪወች ዐብይ አሕመድን ሙሉ በሙሉ የሚደግፉት፣ በዐብይ አሕመድ ተሞኝተው ሳይሆን፣ ከዐብይ አሕመድ ጋር የጋራ አጀንዳ ስላላቸው ነው፡፡  የቀረው ወንጌላዊ መዕምን ከዐብይ አሕመድ ጀርባ የተሰለፈው ደግሞ፣ በማያቋርጥ ስብከት አማካኝነት መንጋዊ እሳቦት (herd mentality) እንዲኖረው ተደርጎ የተቀረጸ በመሆኑ ነው፡፡  መሪወቹን እንደ እንከን አልባ ነብዮች እንዲያያቸው ስለተደረገ፣ በነብይ መሪወቹ ተወግዞ በመዕምን ጓደኞቹ እንዳይገለል በመፍራት፣ ምንም ዓይነት ጥያቄ ሳይጠይቅ፣ መሪወቹ ደግፍ የሚሉትን ሁሉ ሳያቅማማ ይደግፋል፣ ተቃወም የሚሉትን ሁሉ ደግሞ ሳያመነታ ይቃወማል፡፡   

እዩ ጩፋን፣ እስራኤል ዳንሳንና ዮናታን አክሊሉን የመሳሰሉ አጭበርባሪ ቀማኞች ለተካተቱበት የኢትዮጵያ ወንጌላውያን አመራር፣ ወንጌላዊነት ግብ ሳይሆን የግብ መምቻ ነው፡፡  ግባቸው ደግሞ ምስኪን ወንጌላውያንን በሰበካ ብዛት አደንዝዘው አንጡራ ሐብታቸውን ሙልጭ አድርገው መዝረፍ ነው፡፡  ይህን ዓላማቸውን በቀጥታም ሆነ በተዛዋሪ የሚደግፍን ማናቸውንም ግለሰብ ደግሞ (የሚደግፍበት ምክኒያት ምንም ይሆን ምን)፣ እነሱም ባጸፋው ይደግፉታል፡፡  ግለሰቡ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ከሆነ ደግሞ እሰይው ያስብላቸዋል፡፡  በዚህ ምክኒያት ነው፣ ዐብይ አህመድ የሚንገዳገድ በመሰለ ቁጥር እዩ ጩፋና ሌሎች የወንጌላውያን መሪወች በመግለጫ ጋጋት ሊደግፉት የሚሯሯጡት፡፡              

የኢትዮጵያ ወንጌላውያን መሪወች ዋና ዓላማ፣ በስብከት ብዛት የማይራገጡ ገራም ላሞች ያደረጓቸውን ወንጌላዊ መዕምኖቻቸውን እስኪነጥፉ ድረስ ሙልጭ አድርጎ ማለብ ስለሆነ፣ የወንጌላዊ ላሞቻቸውን ቁጥር ለማብዛት ሲሉ ማናቸውንም ከማድረግ አይቆጠቡም፡፡  በዚህ ረገድ ለወንጌላውያን የመስፋፋት ጥቃት በቀላሉ ተጋላጭ ሁና የተገኘቸው የኢትዮጵያ ርቱዕ (ኦርቶዶክስ) ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ናት፡፡  ርቱዕ ተዋህዶ ለወንጌላዊ ተስፋፊወች በቀላሉ ተጋላጭ የሆነችባቸው አያሌ ምክኒያቶች ሲኖሩ፣ የሚከተሉት ሦስቱ ደግሞ ከዋናወቹ ውስጥ ጥቂቶቹ ናቸው፡፡

  • ተዘርዝረው የማያልቁት የሷ የራሷ አስተዳደራዊ ችግሮች፡፡  በተለይም ደግሞ ከልጆቿ ትምህርት ይልቅ ለንዋያተ ቅድሳቶቿና ለሕንጻወቿ የበለጠ አትኩሮት በመስጠት፣ የዋህ በጎቿን ለወንጌላዊ ነጣቂ ተኩላወች አጋልጣ መስጠቷ፡፡
  • የጦቢያን ፊደል ቀርጻ፣ ባህሏን አንፃ፣ ሕዝቧን በኢትዮጵያዊነት መንፈስ አስተባብራ፣ ኢትዮጵያን ኢትዮጵያ ያደረገች በመሆኗ ሳቢያ፣ ወያኔንና ኦነግን የመሳሰሉ ፀረጦቢያ ጎጠኞች አከርካሪዋን መትተው ለመሰባበር፣ በሰርጎ ገቦቻቸው አማካኝነት ሁልጊዜም የሚያሻጥሩባት መሆኗ፡፡
  • ካጼ ምኒሊክ ጋር አድዋ ዘምታ ቅኝ ገዥወችን ድባቅ በመምታቷ፣ ያፍሪቃውያን የነጻነትና የኩራት ምልክት የሆነውን አረንጓዴ-ቀይ-ቢጫ ሰንደቅ ዓላማ በጉልላቶቿ ላይ በኩራት በማውለብለቧ፣ ቅኝ ገዥወች ወደ አፍሪቃ ያላመጧት ብቸኛዋ (ከኮፕቲክ ቤተክርስቲያን ጋር) አፍሪቃዊ ቤተክርስቲያን በመሆኗ፣ እየሱስ በተሰቀለበት (ቀራንዮ) ላይ ምኩራብ (chapel) ካላቸው ጥቂት ቤተክርስቲያኖች ውስጥ አንዷና ብቸኛው የጥቁር ቤተክርስቲያን በመሆኗ፣ የብሉይና የሐዲስ ኪዳን ምንጭ የሆነው የመጽሐፈ ሄኖክ ብቸኛ ባለቤት በመሆኗ፣ እና ከሮማ ካቶሊክ አስቀድማ የተመሠረተች በመሆኗ ምክኒያት በነጭ ዘረኞች ጥርስ ውስጥ መግባቷ፡፡

በነዚህና በሌሎች ችግሮች ተሰቅዛ የተያዘችው ርቱዕ ተዋህዶ፣ በርግጥም ለወንጌላዊ ጩልሌወች ክፉኛ የተጋለጠች መሆኗ አያስገርምም፡፡  ስለዚህም የኢትዮጵያ ወንጌላውያን መሪወች (ወንጌላዊ መዕመኖቻቸውን በእየሱስ ስም እያጃጃሉ ለመመዝበር) የመሠረቱትን ድርጅት ዋና መሥርያ ቤት አዲሳባ ውስጥ ለማቆም ያሰቡት በመንበረ ፓትርያርክና በቅድስተ ማርያም ፍርስራሽ ላይ ቢሆን አያስደንቅም፡፡ የተዋህዶን ችግር ድርብርብ የሚያደርገው ደግሞ በስሙ የጦቢያ ጠቅላይ ሚኒስትር የሚባለው ኦነጋዊው ኦቦ ዐብይ አሕመድ፣ ተዋህዶን ውጦ ለመሰልቀጥ ያሰፈሰፈ መሆኑ ነው፡፡  ስለዚህም ዐብይ አሕመድና የኢትዮጵያ ወንጌላውያን፣ ለርቱዕ ተዋህዶ ባላቸው ጠላትነት የተሳሰሩ ናቸው፡፡  ትስስራቸው ግን ግራ አጋቢ ነው፡፡    

ዐብይ አሕመድ የጴንጤቆስጤን በዓልን ከማክበር ይልቅ ኢሬቻን ማክበር እንደሚመርጥ፣ ጴንጤ ከመባል ይልቅ ዋቄፈተኛ መባል ይበልጥ እንደሚገልጸው የኢትዮጵያ ወንጌላውያን መሪወች በሚገባ ያውቃሉ፡፡ በተጨማሪ ደግሞ ዐብይ አሕመድ ተዋህዶን ከውስጥም ከውጭም በመቦርቦር ለማፈራረስ ቆርጦ የተነሳው ከተዋሕዶ አስተምህሮ (doctrine) ይልቅ የወንጌላዊነትን አስተምህሮ በመምረጥ ሳይሆን፣ የኦሮሞን አጼጌ (Oromo empire) መገንባት የሚችለው ኢትዮጵያን ማፈራረስ ከቻለ ስለሆነና፣ ኢትዮጵያን ማፈራረስ የሚችለው ደግሞ ተዋህዶን ካፈራረሰ ብቻ እንደሆነ ስለሚያውቅ ነው፡፡  

ዐብይ አሕመድ በስልጣን ላይ እያለ በጦቢያ ውስጥ ለተፈጸሙት ለሁሉም ዘር ተኮር ጭፍጨፋወች (በተለይም ደግሞ ባስር ሺወች ለሚቆጠሩ አማሮች ባሰቃቂ ሁኔታ በኦነጋውያን መታረድ) በቀጥታም ሆነ በተዛዋሪ ተጠያቂ ነው፡፡  ይህን የኢትዮጵያ ወንጌላውያን መሪወች ያውቃሉ፡፡  በተጨማሪ ደግሞ (ከወንጌላውያን ውስጥ ብዙሃኖቹ አማሮች ሳይሆኑ ስለማይቀሩ)፣ ከዘር ጭፍጨፋ ሰለባወች ውስጥ አብዛኞቹ አማራ ወንጌላውያን የመሆናቸው ዕደል ከፍተኛ እንደሆነ፣ የኢትዮጵያ ወንጌላውያን መሪወች ያውቃሉ፡፡  

ይህ ሁሉ ግን የወንጌላውያን መሪወች ለዐብይ አሕመድ በሚሰጡት የማያወላውል ከፍተኛ ድጋፍ ላይ ኢምንት ተጽእኖ አይኖረውም፡፡  ከላይ እንደተጠቀሰው፣ የወንጌላውያን መሪወች ዋና ዓላማ የተዋህዶን ድምጥማጥ አጥፍተው መላውን የኢትዮጵያን ክርስቲያን ሕዝብ ያለ ሁነኛ ተቀናቃኝ ሙሉ በሙሉ በመቆጣጠር ሙሉ በሙሉ መመዝበር ነው፡፡  በመሆኑም (ዐብይ አሕመድን በተመለከተ) የነዚህ የወንጌላውያን መሪወች ሙሉ ትኩረት በተዋህዶ ላይ የሚሰነዝረውን ማጥቃት አጠናክሮ መቀጠል አለመቀጠሉ ላይ ብቻ ነው፡፡  በተዋህዶ ላይ የሚሰነዝረውን ጥቃት አጠናክሮ እስከቀጠለ ድረስ (ባማራና በሌሎች አልኦሮሞ ጦቢያውያን ላይ የሚፈጽመውንና የሚያስፈጽመውን ዘር-ተኮር ጭፍጨፋ አጠናክሮ ቢቀጥልም)፣ የሚሰጡትን ድጋፍ አጠናክረው ይቀጥላሉ፡፡

በርግጥም (ለመጣ ለሄደው እየሱስ፣ በየሱስ እያሉ ሰውን ሁሉ የሚያደነቁሩት) የኢትዮጵያ ወንጌላውያን መሪወች፣ በራስህ ላይ ሊደረግብህ የማትፈልገውን በሌላው ላይ አታድርግ (ማቴወስ 7፡12) የሚለውን የኢየሱስን ወርቃማ ሕግ (golden rule) የማያከብሩ ተመጻዳቂወች ናቸው፡፡  በደርግ ዘመን ከፍተኛ የሐይማኖት ጭቆና ደርሶብናል እያሉ ሲያላዝኑ እንዳልነበር፣ አሁን ግን (ሐይማኖታዊ ጭቆናው አምረረው በሚጠሏት በተዋህዶ ላይ ስለሆነ ብቻ) የትልቁ (ከግራኝ አሕመድ ቀጥሎ) የሐይማኖት ጨቋኝ የዐብይ አሕመድ ቀንደኛ ደጋፊወች ሆኑ፡፡

Email:   mesfin.arega@gmail.com

Filed in: Amharic