>

ምርጫ ቦርድ እነ እስክንድር ነጋን በዕጩነት ሊመዘግብ ነው ! (ባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ)

ምርጫ ቦርድ እነ እስክንድር ነጋን በዕጩነት ሊመዘግብ ነው !

ባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በወሰነው መሰረት በግፍ እስር ላይ የሚገኙት የባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ መሪዎች እስክንድር ነጋ፣ ስንታየሁ ቸኮል፣ አስቴር ስዩም እና አስካለ ደምሌ በመጭው ምርጫ በዕጩ ተወዳዳሪነት እንዲቀርቡ ለማድረግ ሥራዎችን መጀመሩን አስታውቋል። የቦርዱ ሰብሳቢ ወ/ሪት ብርቱካን ሚደቅሳ ግንቦት 26 ቀን 2013 ዓ.ም. የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት 1ኛ የምርጫ ጉዳዮች ችሎት ቀርዋል።
   ቦርዱ የፍርድ ቤቱን ትዕዛዝ እንደሚፈፅምም ተናግረዋል። የዕጩዎቹን ስም ዝርዝር እና በእነ ማን  እንደሚተኩ ለቦርዱ ያቀረበው ባልደራስ ለእነ እስክንድር ነጋ የዕጩነት ማረጋገጫ ሰነድ እንዲሰጠው መጠየቁን የፓርቲው የሕግና ሰብዓዊ መብት ጉዳዮች ሓላፊ ጠበቃ ሔኖክ አክሊሉ ተናግረዋል። ምርጫ ቦርድ ቀሪ ሥራዎችን አጠናቆ ሰነዱን ግንቦት 30 ቀን 2013 ዓ.ም. በፍርድ ቤቱ ፊት እንዲያቀርብም ቀጠሮ ተይዟል።
እንደ ቦርዱ ማብራሪያ ዕጩዎቹን ለማተካካት በተደረገው እንቅስቃሴ ታትሞ የነበረ 1.3 ሚሊዮን ወረቀት ተወግዷል። በዚህም ከ5 ሚሊዮን ብር በላይ ተጨማሪ ወጭ ተደርጓል።
Filed in: Amharic