>

 አገር ማለት ይህቺ ናት! (ሲናጋ አበበ)

  አገር ማለት ይህቺ ናት!

 ሲናጋ አበበ


   የሰይጣን ቁራጩ የባንዳው ልጅ መለስ ዜናዊ አገሪቱን በዘር ከፋፍሎ የቀድሞ የአባቶቹን ጌቶች የጣሊያን ሶላቶች ከፋፍሎ ለመግዛት እንዲያመቻቸው የዘረጉትን ፕሮግራም ተግባራዊ አደረገብን፡፡ አባቶቻቸው ኢትዮጵያን ለጠላት አሳልፈው የሰጡ እነ ወዳጆ አሊ መንፈሳቸው በልጆቻቸው ውሎ እንደ ክፍሌ ወዳጆ ያሉት ኢትዮጵያን ለማጥፋት የዛሬውን ሕገ መንግሥት ተብዬውን እራሳችን ላይ ጥለው በሠላም አብሮ የኖረውን ሕዝብ በተለይም ኦሮሞን ነጻ እናወጣለን ላለው ቡድን ዛሬ የበላይነቱን ይዞ በኢትዮጵ ምድር በታሪኩዋ በሠላማዊ ሕዝብ ላይ ታይቶ የማይታወቅ ጭፍጨፋ ሲፈጸም እያየን ነው፡፡ ከታሪክ እንደምንረዳው የአማራ ሕዝብ ከማንኛውም ብሄረሰብ በፊት በቅድሚያ ክርስትናን በመቀበልና የራሱን ፊደል ቀርጾ የሥልጣኔ ጮራ በማየቱና ይህንንም ሆነ ባህሉን በማሥፋፋቱ እንደ ወራሪ እንደ ጨቁዋኝ ተፈርጆ ዛሬ በጠላትነት የሚታየው እሱ ሆኑዋል፡፡ ዛሬ ለሆዳቸው ባደሩ ወገኖቹ/ያገሩ ልጆች ተከድቶ ስቃዩ ወደር ሊያጣ ችሉዋል፡፡

    መንግሥት የተባለው መዋቅር ህዝብን ፍትሃዊ አስተዳደር ሊጎናጽፈው ሲገባው የጨፍጫፊዎቹ ስንቅ አቀባይና ጥይት አጉራሽ ሆኖ በገሃድ ታይቱዋል፡፡ 

    አገር አማን ነው ብለው ልጆቻቸውን አስተምርው ይጦሩናል ብለው የሚገበገቡላቸውን  የአማራ ተወላጆች በመሆናቸው ብቻ ከደንቢዶሎ ዩኒቭረሲቲ በአገቾች ተነጥቀው መንግሥት ባለበት አገር የልጆቹ ደብዛ ከጠፋ እነሆ ለሁለት አመት አራት ወር ቀርቶታል፡፡

    የተማሪዎቹ እገታ ሲገርመን በቤን ሻንጉል፤ በወለጋ ወዘተ. የሚጨፈጨፉት ንብረታቸው የሚዘረፈው የሚፈናቀሉትና በየዱሩ ተከማችተው ያገር ያለህ የሚሉት ሳያነስ እነደ አጣዬ ከሚሴ እና አካባቢዎች ከተሞቻቸው ጨርሶ እስኪወድሙ መንግሥት ተብዬው ሊከላከልና በሠላም እንዲኖሩ ካላደረገ ምኑን አገር አለን እንላለን፡፡ አገራችን የአሕዛቦችና የሰው አውሬዎች እንዳሉበት የተገነዘብነው አሁን ገና ነው፡፡ ለዚህ ሁሉ ጭፍጨፋ ደደቢት በረሃ መለስና ጉዋደኞቹ አማራን ትልቁ ጠላታቸው አድርገው በመቅረጽ እንታገለዋለን ሲሉ በማነፌስታቸው የቀረጹትና እስከዛሬም ከማንፌስታቸው ያልወጣው ነው፡፡ ዛሬም የሕዋህት ጁንታ ከሞላ በጎደል ተደምስሶ ባለበት ተራፊዎቹ እነ ጌታቸው ረዳና ጻድቃን ወልደ ተንሳይ ዋናው ጠላታቸው አማራው ነው እያሉ ከመናገር አልተቆጠቡም፡፡ ይህ ሁሉ ግፍ በአማራው ላይ ሲከናወን የመንግሥት ትኩረቱ የዛፍ ተከላና ችግኝ ማጠጣት መሆኑን ስናይ በአገራችን ተስፋ እንድንቆርጥ ይገፋፋናል፡፡

  ስለሆነም ሕውሀትም ሆነ ብልጽግና አማራውን ጨፍጭፈው ለማጥፋት መንቀሳቀሳቸው በጉልህ ታይቱዋል፡፡ እጀግ የሚገርመው ደግሞ ከአማራ አብራክ ተገኘን ብለው ዓይናቸውን በጨው አጥበው አስተዳዳሪዊች መሆናቸው ነው፡፡ ከዚህም ባለፈ ደግሞ ለብልጽግና በእጩነት  የተመዘገቡ ለሆዳቸው የቆሙ ወደፊትም ተባባሪ በመሆን ሊያስጨፈጭፉ መዘጋጀታቸው የማይቀፋቸው ነው፡፡ ሁሉም አማራ በአሁኑ ሰዓት ለብልጽግና የቆመ ሁሉ ወገኑን ለሆዱ የሸጠ መሆኑን ልንገነዘብ ይገባል፡፡ የችግሩን ግዝፈት ላልተገነዘበ ሁሉ ማስገንዘብ የሁሉም አማራ ግዳጅ ነው፡፡ ለአማራው መብት የቆሙትን ሀቀኛ የአማራ ልጆች በአብን ሥር የተሰባሰቡ ስለሆነ እነሱን መምረጥ ለወገኑ ተቆርቆዋሪ የሆነ ሁሉ ሊገነዘብ ይገባል፡፡

     ጡዋት የተናገረውን በማግሥቱ የማይደግመው ጉደኛ እራስ ወዳድ ጠቅላይ ሚኒስትር ተብዬው ከበሻሻ መንደር  ወጥቶ በሦስት ዓመት ውስጥ ከኔ በላይ የህቺን አገር ሊመራት አይችልም ብሎ እራሱን አግዝፎ ሌላውን ማስፈራራት መጀምሩ እጅግ የሚገርምም የሚደንቅም ነው፡፡ ቀደም ሲል ዴሞክረሳዊ ሥርአት በመገንባት ላይ ነን በመጪው ምርጫ ተፎካካሪዎች ቢያሸንፉ ስለጣኔን በሀያ አራት ሰዓት ውስጥ አስረክባለሁ ብሎ የተናገረውን ጨርሶ ረስቶታል፡፡

      ምን ያህል እራሱን አግዝፎ እንደሚያይ ከዚህ ጋር ያለውን ቢል ቦርድ ላይ የተለጠፈውን ፎቶ ማየት ብቻ ይበቃል፡፡ ብዙ እራስ ወዳዶችን አይተናል የኛው ጉድ ግን በጣም አስፈሪም አሳፋሪም ነው፡፡ እንዴት በአንድ ሰሌዳ (ቢልቦርድ) ሁለት ጉርድ ፎቶዎችን አንዱ ፎቶግራፍ ሁልተኛው የእጅ ስእል ያስለጥፋል፡፡ 

 የኢትዮ 360 ሀቀኛ የፖለቲካ ተንታኞች አቶ ኤርሚያስና አቶ ሀብታሙ ደጋግመው እንደነገሩን ሁሉ ሰውዬው እራሱን እጅግ ከመውደዱም በላይ እራሱን በመስታዎት ተመልክቶ የሚጠግብ አይመስልም፡፡ ፈረንጆቹ እራስ ወዳድ  (Narcissistic) ብለው የሚጠሩት እንደዚህ ዓይነቱን ሰው ነው፡፡

 እንዲህ ዓይነት ሰው ነው ይህችን ታላቅ አገር የሚመራት፡፡ እግዜር እራሳችሁን ቻሉ ብሎ ይህችን የተቀደሰች አገር ሰጥቶናል እኛም ተፈጥሮዊ መብታችንን ልናስከብር ይገባናል፡፡ 

 አማራ የሆንክ ሁሉ ለህልወናህ  አብንን ምረጥ፡         

  ሲናጋ አበበ

Filed in: Amharic