>

ድንበር ተሻጋሪው ኦሮሙማ የኅልውናዋ አደጋ በመሆኑ  ጎረቤታችን ኬንያ የምንጊዜም ጠበቃችን ነበረች! (አቻምየለህ ታምሩ)

ድንበር ተሻጋሪው ኦሮሙማ የኅልውናዋ አደጋ በመሆኑ  ጎረቤታችን ኬንያ የምንጊዜም ጠበቃችን ነበረች!    
  አቻምየለህ ታምሩ

ሰልቃጩ ኦሮሞማ ድንበር ተሻግሮ በመታወኩ ምክንያት ዛሬ በኢትዮጵያ ላይ ፊቷን እንድታዞር የተገደደቸው ኬንያ በታላላቆቹ አባቶቻችን ዘመን በየአለማቀፉ መድረክ ሁሉ እየተገኘች ለኢትዮጵያ ጥብቅና የምትቆም አፍሪካዊት አገር ነበረች።
ከታች የምትመለከቱት ታሪካዊ  ፎቶ ግራፍ የኬንያ የመጀመሪያው ፕሬዝደንትና የዛሬ ኬንያን በፕሬዝደት እየመራ ያለው የኡሁሩ ኬንያታ አባት የሆኑት ጀሞ ኬንያታ ኬንያታ በወጣትነት ዘመኑ እ.ኤ.አ. በ1943 ዓ.ም. «ኢትዮጵያ የባሕር በር ያስፈልጋታል» ብሎ የኢትዮጵያን ሰንደቅ አላማ በማውለብለብ ኢትዮጵያ የባሕር በር ባለቤት እንድትሆን ከሎንዶን እስከ ኒዮርክ እየዞረ ለኢትዮጵያ ሲከራከር በነበረበት ወቅት የተነሳው ፎቶ ነው። ጀሞ ኬንያታ ያነገበው መፈክር “Ethiopia wants access to the sea” ይላል።  እነ ጀሞ ኬንያታ በዚህ መልክ የባሕር በር ባለቤት እንድትሆን የተከራከሩላት አገር ወደብ አልባ የሆነችው የሰው ዘር ጠላቶች የሆኑት የኦሮሞና የትግሬ ብሔርተኞች ወደብ እንዳይኖራት ባደረጉት የ17 ዓመታት ትግል ነው።
ለኢትዮጵያ ቀዳሚ ጠበቃ በመሆን ስትሟገትልን የኖረችው  ኬንያን ያህል ታማኝ የኢትዮጵያ የምንጊዜውም ወዳጅ ዛሬ ላይ በኢትዮጵያ ጀርባ ከኢትዮጵያ የምንጊዜም ጠላት ጋር የጦር ስምምነት ለመፈረም የተገደደችው ሰማዩንም ምድሩንም የኔ ነው የሚለው ኦሮሙማ በኢትዮጵያ ውስጥ የለመደውን ኬንያም ተሻግሮ ለማድረግ በመነሳቱና የኬንያ ክፍል የሆነውን ሞያሌን [የኢትዮጵያም  የኬንያም  ክፍል  የሆኑ  ሁለት ሞያሌዎች እንዳሉ ልብ ይሏል] በስመ ኦሮሞ ወደ ኦሮምያቸው ለመጠቅለል በመንቀሳቀሱ ኬንያም ይህንን ድንበር ተሻጋሪ የኦሮሙማ ወረራ የውሕዷ ኬንያ የኅልውና አደጋ አድርጋ በማየቷ ነው።
ኢትዮጵያ ሶስት ጊዜ ተረግማለች። ሶስት ጊዜ የተረገመችውም መደዴው መንግሥቱ ኃይለ ማርያም፣ ትንሹ መለስ ዜናዊና ኮልኮሌው ዐቢይ አሕመድ አገር ሊመሩ  በታላቁ አክሊሉ ሀብተ ወልድ ወንበር ላይ ሲቀመጡ ነው።
መንግሥቱ ኃይለ ማርያም፣ መለስ ዜናዊ፣ ዐቢይ አሕመድ — የክፋት ስሞች፤ የዝቅጠት ልኮች፤ የደንቁርና ምልክቶች፤ አገር እየገዙ ተግባራቸው ግን የተራ ወንጀለኛ — ድሀ ዘራፊና ገፋፊዎች፤ ብኩን መንፈሰ ደካማና የጨካኝ አረመኔ ተምሳሌት የሆኑ ርጉም ፍጡሮች።
ክብር ለአፍሪካ ኅብረት አርበኛውና ለኢትዮጵያ ጠበቃው ለኬያው የነጻነት መሪ  ለጀሞ ኬንያታ ይሁን!
Filed in: Amharic