>

ከ የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ ፓርቲ  ( አብን)  የተላለፈ መልዕክት !!

ከ የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ ፓርቲ

 ( አብን)  የተላለፈ መልዕክት !!

ለመላው የአዲስ አበባ ኗሪዎች፣ የንቅናቄያችን አባላት እና ደጋፊዎች በመሉ፦
 
የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ የትግል አምዶች  ፍትህ፣እኩልነት እና ነፃነት መሆናቸውንና በትግላችን ምንጊዜም ህዝብንና የህዝብን ጥያቄ  የምናስቀድም  መሆኑን ከአሁን በፊት የወሰድናቸው ፖለቲካዊ አቋሞቻችን የሚያረጋግጡት ሀቅ ነው ።
በተመሳሳይ ሁኔታ በአዲስ አበባ ጉዳይ ላይ የነዋሪዎችን መብት በተሟላ ቁመና ለማስከበር እውነተኛ የፍትህ እኩልነት እና ነፃነት ትግል እያደረገ ከሚገኘው ባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ ጋር የምርጫ ፉክክር ውስጥ መግባት የህዝብን ድምፅ መከፋፈል መሆኑን በማመን ንቅናቄያችን አስቀድሞ አቋሙን ይፋ ማድረጉ ይታወሳል። አዲስ አበባ የሚመጥናት የተመረጠ አስተዳደር እንደሚያስፈልጋት ብሎም የነዋሪዎች ማሕበራዊ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ተሳትፎ የሚረጋገጥበት መዋቅርና ሕግ እንደሚያስፈልጋት አብን በፅኑ ያምናል።
 በዚህም የአዲስ አበባን ስሪትና ስነ ልቦና የሚረዳ እና ለአዲስ አበቤነት በመታመንና ጥብቅና በመቆም ባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ በተግባር የተፈተነ ሀቀኛ ድርጅት መሆኑን እናምናለን። በመሆኑም የንቅናቄያችን አባላት እና ደጋፊዎቻችን እንዲሁም የተከበረው የአዲስ አበባ ነዋሪ ሰኔ 14 ቀን በሚካሄደው ምርጫ አዲስ አበባ ላይ ባልደራስን እንድትመርጡ በአክብሮት እንጠይቃለን።
አዲስ አበባን ማዳን ኢትዮጵያን ማዳን ነው!
Filed in: Amharic