>

የዐቃቤ ሕግ ምስክሮች በግልጽ ችሎት እንዲቀርቡ ተወሰነ ! (ባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ)

የዐቃቤ ሕግ ምስክሮች በግልጽ ችሎት እንዲቀርቡ ተወሰነ !

ባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ

    በእነ እስክንድር የክስ መዝገብ ጉዳዩን በዋነኛነት የያዘው የፌደራል ከፍተኛ  ፍ/ቤት አስቀድሞ በሰጠው ቀጠሮ መሰረት ፤ ዛሬ በዋለው ችሎት የምስክር አቀራረብ ሒደት ላይ የግራና ቀኝ የህግ ክርክር በመመርመር ፍ/ቤቱ ውሳኔ ሰጥቷል ።የፌደራል  ከፍተኛ ፍርድ ቤት ዐቃቤ ህግ በእነ እስክንድር ነጋ ላይ እንዲመሰክሩ  ያዘጋጃቸው 16 ምስክሮች በግልጽ ችሎች እንዲመሰክሩ ወስኗል
   የከፍተኛው ፍርድ ቤት አንደኛ የጸረ ሽብር እና ህገ መንግስታዊ ጉዳዮች ችሎት ዛሬ ማክሰኞ ሰኔ 22 ቀን 2013 ዓ.ም  ውሳኔውን ያሳለፈው፤  ምስክሮች “ለደህንነታቸው” ሲባል በዝግ ችሎት ከመጋረጃ ጀርባ እንዲሰሙ በዐቃቤ ህግ በኩል የቀረበውን ጥያቄ በተከሳሾች እና በደጋፊዎቻቸው በኩል ለዐቃቤ ሕግ ምስክሮች ምንም አይነት በቂ የሆነ በምክንያት  እና በእውነት  አስረጂ የሆኑ የደህንነት ስጋት አላገኘሁም ፤ በማለት ፍ/ቤቱ የዐቃቤ ሕግ የመጋረጃ ጀርባ ምስክርነት ጥያቄ ውድቅ አድርጓል ።
የዐቃቤ ሕግ ምስክሮች ሐምሌ 8 እና 9 እንዲሁም ሐምሌ 14፣15እና 16 በአምስት ቀናት ውስጥ እንደሚሰማ ፍርድ ቤቱ ትዕዛዝ ሰጥቷል ።
በዛሬው የችሎት ውሎ የፖለቲካ እስረኞች እነ እስክንድር  ያቀረቡት አቤቱታ እና ተያያዥ ጉዳዮችን በተመለከተ በዝርዝር እንመለስበታለን ።
ድል ለእውነተኛ ዲሞክራሲ! !

https://www.youtube.com/watch?app=desktop&v=n4JTnF5WN1E&feature=share

Filed in: Amharic