ተኩስ አቁም Ceasefire…!!!
አርአያ ተስፋ ማርያም
የተኩስ አቁም በሁለት በታጠቁ ሀይሎች መሀል በሚደረግ ፍልሚያ በመሀል ለአፍታ በስምምነትም ሆነ ያለ ስምምነት በተናጠል ወይም በሶስተኛ አካል እንደ UN Security Council ባሉ አካላት እገዛ ለተወሰነ ግዜ ጦርነቱን አቁሞ ሰላማዊ ህዝብ የሰብዓዊ እርዳታ እንዲያገኝ እንዳይራብ ደህንነቱ እንዲጠበቅ የሚደረግበት ሀላፊነት በሚሰማቸው የጦር አመራሮች የሚፈፀም ተግባር ነው።
የተኩስ አቁም በስምምነት ወይም በተናጠል ከተደረገ በውሃላ አብዛኛውን ግዜ በጦርነት የተያዙ ሰላማዊ ዜጎች ከሚኖሩባቸው ከተሞች ጦር በማስወጣት በቅርብ እርቀት ገዢ መሬቶችን ይዞ በመጠባበቅ ነው ተፈፃሚ የሚሆነው። በተጨማሪም የተኩስ አቁምን ተዋጊዎች ራሳቸውን በጦር በስነ ልቦናና በታክቲክ በተሻለ መልኩ ለማደራጀትም ይጠቀሙበታል ።
በመሆኑም ትላንት የኢትዮጵያ መንግስት በመቀሌ ያደረገው ለትግራይ ህዝባችን ሲባል ይህን መሰሉን ሀላፊነት የተሞላው የተሞላው ተግባር ነው ። እሱ ብቻ ሳይሆን መንግስት የእርሻ ወቅት እስኪያልፍ የሚል የገደብ ግዜም አስቀምጧል። ይህን ለህዝብ ሲባል የተወሰደውን እርምጃ ለሌላ አደገኛ ተግባር የሚያውል ካለ እርምጃ እንደሚወስድም አስጠንቅቋል ።
ታንኩም ባንኩ ጀቱም ድሮኑም ወታደሩም በእጁ ያለው መንግስት የተኩስ አቁም እርምጃውን በተናጠል ለመውሰድ የተገደደበት ምክንያት ህውሀት የሚባል ድርጅት ሙሉ በሙሉ እንዳያንሰራራ ተደርጎ ማወደም በመቻሉ ! ቅሪተ አካሉ ለድርድር የማይሆን አሸባሪ የሽፍታ ስብስብ፣ ለህዝብ እንደማያስብ በተደጋጋሚ ያረጋገጠ ፣ ስራው የትግራይ ህዝብ እርዳታና ሰላም እንዳያገኝ ሾፌርና የአስታደር ሰዎችን በመግደል በትግራይ ህዝብ እርሀብና ሞት እየተጠቀመ ነፍሱን በዋሻ ለማቆየት እየሰራ በመሆኑ ነው ርዝራዡ አቅም ኖሮት ከማ ተቆጣጥሮ አለመሆኑን ሁሉም ጤነኛ ኢትዮጵያዊ ሊገነዘብ ይገባል።
በቀጣይም ከተሞችን ከቦ በማቆየት የእርሻ ግዜ ሲጠናቀቅ በተጠናከረ መልኩ የቀሩትን ርዝራዦች ባጠረ በፈጠነ መልኩ የማስወገድና ለህግ የማቅረብ ስራ ይሰራል።
ይህ የመንግስት እርምጃ በአለም አቀፍ ማህበረሰብ በጥሩ እየታየለት የሚገኝ ሲሆን ለዲፕሎማሲያዊ አጀንዳም በእጅጉ የሚጠቅም ይሆናል።
ኢትዮጵያ ለዘልዓለም ትኑር