“አገዛዙ ትግራይን ለወያኔ አስረክቦ ለቆ ወጣ!”
አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው
በተራዬ ላሽሟጥባችሁ
አየ ወገኖቸ አልሰማኝ አላቹህ እንጅ እኔማ እኮ “ተው ‘ለውጥ!’ የሚባለውም፣ ‘ሕግን የማስከበር ጦርነት!’ የሚባለውም ድራማ ነው አትመኑ አትጃጃሉ፡፡ እነ ዐቢይ የወያኔ ፍጹም ታማኝ አገልጋዮች ናቸው፡፡ ትዕዛዝ የሚቀበሉት ከወያኔ ነው፡፡ ጦርነቱን እውነት ለማስመሰልና ሕዝብን ለማሳመን ተቃጥሎና ወድሞ በምታዩት አሮጌ ታንክና ተሽከርካሪዎች እንዲሁም የጦስ ዶሮ ተደርገው በግፍ በተገደሉ ወገኖቻችን ግድያ አትሸወዱ ሁሉም ነገር አማራን ለመፍጃ ሰበብ እንዲሆን የተፈጠረ ድራማ ነው…!” እያልኩ የአገዛዙን ሴራ በየጊዜው በጥልቀት እየተነተንኩና “ይሄ ቢሆን ይሄ ይሆን ነበረ ወይ? ይሄ ስላልሆነ አይደለም ወይ ይሄ የሆነው?” እያልኩ በአመክንዮ እየሞገትኩ ስነግራቹህ ብትሰሙኝና በጭፍኑ ባትጃጃሉ ኖሮ ዛሬ ድንጋጤ ይቀንስላቹህ ነበረ!!!
“ወያኔ ትግራይን ተቆጣጠረ!” በሚለው ወሬ አትደነቁ በቅርቡ አገልጋዮቹን እነ ዐቢይ አሕመድን ዞር አድርጎ በዐፄ ምኒልክ ቤተመንግሥት ጉብ ሲል ታዩታላቹህ!!!
መራሩ የአማራ ፍዳ፣ ሰቆቃና መከራ ወይም እልቂት ማለትም የዘር ማጥፋት ጭፍጨፋ ከዚህ በኋላ ነው በሰፊው የሚፈጸመው!!! በነገራችን ላይ በኤርትራ ስደተኞች ስም በሰሜን ጎንደር ወገራ አውራጃ ዳባት ከተማ ላይ ካምፕ ተሠርቶ ሊሰፍር የተዘጋጀው በመቶ ሽዎች የሚቆጠር ስደተኛ የቸባለው ሰፋሪ ስደተኛ ሳይሆን ወታደራዊ ሥልጠና የወሰደ የሸአቢያና የወያኔ ጦር ነው ከነትጥቁ ሲቭል ስደተኛ መስሎ በአማራ ላይ ጥቃት የሚፈጽሙበት ቀን እስኪደርስ ድረስ ሰፍሮ የሚቆየው!!! አንድ “ሀገሬ ወገራ ያለብሽ መከራ!” የሚባል ትንቢት አለ፡፡ የዚህ ትንቢት መፈጸሚያው ይሄ ሳይሆን አይቀርም!!!
“ተዉ ይሄን ጊዜ የወያኔን ቀኝ እጅ ፀረ አማራውን ብአዴንን እንዝመትበትና እናጥፋ!” ብል ማን ይስማኝ! ምድረ ጅል ብአዴን አማራን እንዲያጃጅል በፈጠረው አብን በሚባለው የካድሬዎች ጥርቅም ስትጃጃል ከረምክ!!!
እሽ አሁን እንግዲህ ምን ልታደርጉ ነው???
ወያኔ ቤተመንግሥት ከተመለሰ በኋላ ይሄንን ሁሉ ድራማ ለመተወን ምን እንዳስገደደው ምን ብሎ justify ለማድረግ እንደሚሞክር ታውቃላቹህ “ግብጽንና ሱዳንን እንዲሁም ከጀርባቸው ያሉ ሀገሮችን አዘናግቶ የዓባይን ግድብ ለመጨረስ ያለፈውን ሦስት ዓመት የተወንነውን ድራማ ሁሉ መተወን ድግ ነበረብን!” ብሎ ነው የኢትዮጵያን ሕዝብ ለማጃጃል የሚሞክረው!!!
ከዚያም በኋላ በለየለት ፈላጭ ቆራጭ አንባገነናዊ የአገዛዝ ሥርዓት ልክ እንደ ቻይና የአውራ ፓርቲ ሥርዓትን መሥርቶ ከዚህ በኋላ ያለውን ዘመን ለመግዛት ጥረት ያደርጋል፡፡ አልሆን ካለው ከዚህ ቀደም ሲያሳየን የነበረውን ምዕራብ ጎንደርን፣ የዓባይ ግድብ ያለበትን ስፍራ እስከ ጋምቤላ ድረስ ያለውን መሬት የትግራይ አካል አድርጎ ይገነጠላል!!!
አየ ወገን “ምከረው ምከረው እምቢ ካለ መከራ ይምከረው!” እንደተባለው ምክሬን አልሰማ ብለህ መከራ ሊመክርህ ነው እንግዲህ! እግዚአብሔር ይሁንሃ ሌላ ምን እላለሁ???