>

እኔ እና ቴዲ አፍሮ በርቀቶች ግን በመንፈስ ....!!! (ዳንኤል ገዛህኝ)

እኔ እና ቴዲ አፍሮ በርቀቶች ግን በመንፈስ Tale Pâté ….!!!

ዳንኤል ገዛህኝ

 

ከአመታቶች በአንዱ ድምጻዊ ቴዎድሮስ ካሳሁን ከማናጀሩ ጋር በሆላንድ አምስተርዳም ከበሳሉ ብዕረኛው ጋዜጠኛ ክንፉ አሰፋ ዘንድ በእንግድነት ይታደማል። እንግድነቱን ቋጭቶ ወደ ማረፍያው ሲመለስ ሌሊቱን የንባብ ልማዱን የሚወጣበትን መጽሀፍ ከጅሎ ኖሮ ጌቾ እና ክንፍሽ በአንድ አፍ “ማን ለብቻው ይታመማል  የዳንኤን ገዛኽኝን ሲዋን አንብብ” በማለት በጎንታ Asides ይጋብዙታል። በነገራችን ላይ ለዚህ መጽሀፍ የጀርባ ማስታወሻ Blurbs የጻፈው ጋዜጠኛ ክንፉ አሰፋ ነው። ቴዲ አላመነታም ወደ መኝታው ሲሄድ ሲዋንን ይዞ ገባ እናም እንቅልፉን ሰውቶ 297 ገጾች አጠናቆ አደረ። እናም አንድ ዘለግ ያለ ግጥም ያለው የሬጌ የሙዚቃ ስልት ያዘ የሙዚቃ ስራ ሰርቶ አደረ ከንባቡ ለጥቆ በታሪኩ ተጽእኖ።
ዘለግ ያሉ ወራቶች ተቆጠሩ። እኔም ከሲዋን ለንባብ መብቃት በሁዋላ ከመስመሩ ጠፋሁ መስል የጓደኛሞች የመገናኛ መረብ ላይ ክንፍሽ በሰደደው
 ጦማር ሰላምታ ላከልኝ፣ ለጥቆም አትላንታን ትቼ ሱፎልስ ሳውዝ ዳኮታ መክተሜን መስማቱን አወሳልኝ። ይህን ብቻ አይደለም በግዜው አንድ ያስደነገጠኝን ጉዳይ አወጋ! ቴዲ አፍሮ አምስተርድም ብቅ ባለ ጊዜ ሲዋንን አንብቦ የሲዋንን ልባቦት የደራሲና  ጋዜጠኛ፣ ገጣሚ ወሰንሰገድን ቃል ልዋስ እና የሲዋንን ልባቦት ስቃይ ቴዲ አንብቦ ተሰቃይቶ ዝም አላለም በሲዋን ስሜት ቴዲ Inspired ሆነ እንደ ክንፍሽ አባባል ። በሲዋን ኢንስፓየር ከቴዲ ምናብ “ኮርኩማ አፍሪካ ” ተወለደ።
ከአራት አመት ግድም በፊት ቴዲ አፍሮ ልደቱን በFM 97.1 ስቱድዮ እንዲያ ክብር ይጋበዛል። አዘጋጆቹ ኮሜድያኑ ኢምፕሬሽኒ ስት ዘለአለም ኩራባቸው እና ዝነኛው ዲጄ  ዳንኤል ግዛው የቴዲን ህይወት የሚዳስሱ በተለይም ስለ አባቱ አንጋፋው የሬድዮ ጋዜጠኛ ካሳሁን ግርማሞን (ዘ-ቻምፕ) የተመለከቱ የተለያዩ የተለያዩ ጥያቄዎች እያነሱ  ሲጨዋወቱ ቆይተው በሁዋላም አዘጋጆቹ በይደር ወዳቆዩት “ኮርኩማ አፍሪካ” መጡ። “ኮርኩማ አፍሪካ” እንዴት እንደተወለደ ቴዲ አከለ። በተለይም “ወጣቶች ሲዋን የሚባለውን መጽሀፍ ቢያነቡት ጥሩ ነው” ሲል አስቀድሞ መከረ እናም ሲዋንን አንብቦ የተወለደ ስራ ምስክርነቱን ሰጠ። ይኽው ሀሳብ በዩቱብ ሰፍሮ ይገኛል። በዚህ አጋጣሚ “ኮርኩማ አፍሪካ” የተሰኘውን ድንቅ ዜማ እንድታደምጡ ስጋብዝ ሲዋንን ያላነበባችሁ አሜይላችሁን ስደዱልኝ ከሶፍት ኮፒው አቋድሳችሁዋለሁ። ካሻችሁ ሁለት ድረገጾች ያለ እኔ እውቅና በዶላር እየቸበቸቡት ይገኛሉ ይመቻቸው።
ሐምሌ 7 ቀን የ45ኛ ዓመት የልደት በአልህን ለምታከብረው ተወዳጁ ድምጻዊ ቴዎድሮስ ካሳሁን ቴዲ አፍሮ መልካም ልደት ። እድሜ ጤና ያድልህ።
Filed in: Amharic